የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 8/09 ገጽ 29
  • ከአንባቢዎቻችን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከአንባቢዎቻችን
  • ንቁ!—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መሳደብ መጥፎ የሆነው ለምንድን ነው?
    ንቁ!—2008
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2008
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • ከአንባቢዎቻችን
    ንቁ!—2007
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2009
g 8/09 ገጽ 29

ከአንባቢዎቻችን

የወጣቶች ጥያቄ . . . መሳደብ መጥፎ የሆነው ለምንድን ነው? (መጋቢት 2008) ያደግሁት በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ ቢሆንም መሳደብ ልማድ ሆኖብኝ ነበር። ይህን ልማድ ለማቆም ብዙ ጊዜ ጥረት ባደርግም ሊሳካልኝ አልቻለም። ይሁን እንጂ፣ ይህ ርዕሰ ትምህርት ራሴን መግዛት እንድችል ረድቶኛል። በርዕሱ ላይ እንደተጠቀሰው በስጦታ ያገኘሁትን የመናገር ችሎታ ያለአግባብ ልጠቀምበት አልፈልግም። በመሆኑም አሁን፣ አንድ ነገር ከመናገሬ በፊት በደንብ አስብበታለሁ። በጣም አመሰግናችኋለሁ።

ኬ. ፒ.፣ ብራዚል

የ12 ዓመት ልጅ ነኝ። ትምህርት ቤት ውስጥ የማይሳደብ ሰው ስለሌለ እኔም አንድ ቀን ሳላስበው የስድብ ቃል ከአፌ ይወጣል ብዬ እፈራለሁ። ስለ ስድብ የሚናገረው ንቁ! መጽሔት የደረሰኝ “የወጣቶች ጥያቄ” በተባለው ዓምድ ላይ ይህን ርዕሰ ጉዳይ የሚመለከት ጽሑፍ እንዲወጣ በደብዳቤ ለመጠየቅ እያሰብኩ እያለ ነበር። ጽሑፉ መሳደብ መጥፎ የሆነበትን ምክንያት እንዳስታውስ የረዳኝ ከመሆኑም በላይ እንዳልሳደብ አበረታቶኛል። እንዲህ ያሉ ርዕሰ ጉዳዮችን ማውጣታችሁን ቀጥሉ!

ኤ. ፒ.፣ ዩናይትድ ስቴትስ

እኔና ባለቤቴ የምንተዳደረው ቤት በማጽዳት ሥራ ነው። አንድ ቀን አንዲት ደንበኛችን በአዲሱ ዓመት ስድብ ለማቆም መቁረጧን አጫወተችን። አምላክ ይህን መጥፎ ልማድ እንድታቆም እንዲረዳት በየዕለቱ እንደምትጸልይ ነገረችን። እንዲሁም በዚህ ረገድ ሊረዳት የሚችል ጽሑፍ ካለ እንድሰጣት ጠይቃኝ ነበር። ስለ ጉዳዩ ጸለይኩና እንደ ልማዴ በቅርብ የወጡ መጽሔቶችን www.pr2711.com ከተባለው ድረ ገጽ ላይ በኤምፒስሪ ማጫወቻዬ ላይ ገለበጥኳቸው። በማግሥቱ የርዕስ ማውጫውን ሳዳምጠው ምን እንደተሰማኝ መገመት ትችላላችሁ። በጣም ነበር የተደሰትኩት! ርዕሰ ትምህርቱ በዋነኝነት የወጣው ለወጣቶች ቢሆንም ደንበኛችን ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ምክሮች እንደምታገኝበት እርግጠኛ ነበርኩ። ጽሑፉን እስካሳያት ድረስ በጣም ጓጉቼ ነበር።

ኤስ. ኬ.፣ ዩናይትድ ስቴትስ

የአየር ትራፊክ ቁጥጥር—ጉዞህ አስተማማኝ እንዲሆን የሚያደርገው እንዴት ነው? (ሚያዝያ 2008) ይህን ርዕሰ ትምህርት አንብቤ ከጨረስኩ በኋላ በአድናቆት “አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ አድርጎ ለበረራ ዝግጁ መሆን!” ብዬ ተናገርኩ። ንቁ! መጽሔት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ስለ ደህንነታችን እንደሚጨነቁ ስላሳወቀኝ የተበረታታሁ ከመሆኑም በላይ የበለጠ የመረጋጋት ስሜት ተሰማኝ። አመሰግናችኋለሁ።

ቲ. ኤስ.፣ ብራዚል

መልስህ ምንድን ነው? የ12 ዓመት ልጅ ስሆን የምኖረው በደቡብ አየርላንድ ነው። በንቁ! መጽሔት መጨረሻ ገጽ አካባቢ ለልጆች የሚሆን ለየት ያሉ ጥያቄዎችን ስለምታዘጋጁ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። እንዲህ ያሉ ጥያቄዎችን መጠቀማችሁ ጥሩ ነው። ምክንያቱም ልጆች መጽሔቱን እንዲያነቡት ያበረታታሉ። እባካችሁ ወደፊትም እንዲህ ማድረጋችሁን ቀጥሉ። በድጋሚ አመሰግናችኋለሁ።

ኤ. ኬ.፣ አየርላንድ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ