ወደ አምላክ መቅረብ የሚችሉት እንዴት ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ “ወደ አምላክ ቅረቡ፤ እሱም ወደ እናንተ ይቀርባል” በማለት ይናገራል። (ያዕቆብ 4:8) ሰዎች ከፈጣሪ ጋር የተቀራረበ ዝምድና መመሥረት እንደሚችሉ ይሰማዎታል? ለዚህ ጥያቄ መልስ ከመስጠትዎ በፊት ከዚህ ይበልጥ አስፈላጊ ለሆኑ ሌሎች ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ማግኘት ያስፈልግዎታል። ለምሳሌ ያህል፦
በእርግጥ አምላክ አለ?
አምላክ ካለ ሐሳቡን ለሰው ዘሮች ገልጿል? ይህንንስ ያደረገው በምን መንገድ ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ሐሳቡን ለሰዎች እንደገለጸ የሚያሳይ ማስረጃ ነው? ይህን እንዴት እናውቃለን?
እነዚህ ጥያቄዎች እስከ ዛሬ ካነሳናቸው ጥያቄዎች መካከል በጣም የጎላ ስፍራ የሚሰጣቸው ሲሆኑ “ወደ አምላክ መቅረብ የሚችሉት እንዴት ነው?” በሚለው የሕዝብ ንግግር ላይ መልስ ያገኛሉ። ይህ ንግግር ግንቦት ወር ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚጀምረውና ከዚያም በኋላ በሌሎች የዓለም ክፍሎች በሚካሄደው “ከይሖዋ ጋር ተቀራርባችሁ ኑሩ!” በተሰኘው የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባ ላይ ይቀርባል።
እርስዎም በአቅራቢያዎ በሚደረገው የአውራጃ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ በአክብሮት ጋብዘንዎታል። ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እባክዎን በአካባቢዎ ያሉትን የይሖዋ ምሥክሮች ያነጋግሩ፤ አሊያም ለዚህ መጽሔት አዘጋጆች ይጻፉ። በተጨማሪም ስብሰባው በኢትዮጵያ መቼና የት እንደሚካሄድ የሚገልጽ ፕሮግራም በመጋቢት 1, 2010 መጠበቂያ ግንብ ላይ ይገኛል።