የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 9/10 ገጽ 23
  • የሬዘር ክላም የመቆፈር ችሎታ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሬዘር ክላም የመቆፈር ችሎታ
  • ንቁ!—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2010
  • ከዓለም አካባቢ
    ንቁ!—2009
  • ከዓለም አካባቢ
    ንቁ!—2014
  • ሙልጭ አድርጎ መላጨት
    ንቁ!—2000
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2010
g 9/10 ገጽ 23

ንድፍ አውጪ አለው?

የሬዘር ክላም የመቆፈር ችሎታ

● ሬዘር ክላም የተባለው የባሕር ፍጥረት፣ አሸዋ ቦርቡሮ ለመግባት አቅም የሌለው ይምሰል እንጂ ጥብቅ የሆነን አሸዋ በመቆፈር ረገድ እጅግ ፈጣን በመሆኑ በፍጥነታቸው ታዋቂ ከሆኑ የውድድር መኪኖች ጋር ተነጻጽሯል። ይህ የባሕር ፍጥረት ተመራማሪዎችን አስደንቋል። በማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑ አኔት ሆሶዪ “አንድ የሆነ ብልሃት እንዳላቸው ተረድተን ነበር” ብለዋል። ታዲያ ሬዘር ክላም በፍጥነት መቆፈር የቻለበት ሚስጥር ምንድን ነው?

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ሬዘር ክላም እግሩን እያነቃነቀ አሸዋውን በመቦርቦር አነስተኛ ጉድጓድ ይሠራል፤ ወዲያው ጉድጓዱ በውኃና በአሸዋ ይሞላል። ከዚያም መላ አካሉን ወደ ላይና ወደ ታች ያንቀሳቅሳል እንዲሁም ሰውነቱን የሚሸፍነውን ጠንካራ ቅርፊት ከፈት ዘጋ ያደርጋል። በዚህ መንገድ አሸዋውን ከውኃ ጋር በመቀላቀል በቀላሉ ለመቆፈር የሚመች እንዲሆን ያደርገዋል። ሬዘር ክላም በሴኮንድ አንድ ሴንቲ ሜትር እየቆፈረ እስከ 70 ሴንቲ ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ መቆፈር ይችላል። ሬዘር ክላም በሰረሰረው ጉድጓድ ውስጥ መሬቱን ቆንጥጦ ከያዘ በኋላ አላቆ ማውጣት በጣም አስቸጋሪ ነው። እንዲያውም መሬቱን ቆንጥጦ ከመያዝ አቅሙና ይህን ለማድረግ ከሚያጠፋው ጉልበት አንጻር ሲታይ የሚያባክነው ኃይል፣ በጣም ጥሩ ከሚባለው ሰው ሠራሽ መልሕቅ በአሥር እጅ ያንሳል።

መሐንዲሶች፣ ሬዘር ክላም መሬቱን የሚሰረስርበትን መንገድ ማጥናታቸው የተራቀቀ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም መልሕቅ ለመሥራት አነሳስቷቸዋል። ይህ የተራቀቀ መልሕቅ “ልክ እንደ ክላም ቅርፊት የሚከፈትና የሚዘጋ ከመሆኑም ሌላ ወደ ላይና ወደ ታች ይንቀሳቀሳል” ይላሉ ሆሶዪ። እንዲህ ያለው ኃይል ቆጣቢና ጠንካራ መልሕቅ ለባሕር ሰርጓጅ የምርምር መርከቦች፣ ባሕር ላይ ለሚንሳፈፉ የነዳጅ ማውጫ ጣቢያዎችና ፈንጂዎችን ለሚያመክኑ የመቆፈሪያ መሣሪዎች በጣም ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? የሬዘር ክላም የመቆፈር ችሎታ እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[በገጽ 23 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]

ለሙከራ የተሠራው ይህ የተራቀቀ መልሕቅ ሬዘር ክላም መሬት የሚቦረቡርበትን ዘዴ በመኮረጅ የተሠራ ነው

[ምንጮች]

Razor clams: © Philippe Clement/naturepl.com; “smart” anchor: Courtesy of Donna Coveney, Massachusetts Institute of Technology

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ