የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 12/10 ገጽ 13-31
  • ቤተሰብ የሚወያይበት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቤተሰብ የሚወያይበት
  • ንቁ!—2010
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጥሩ ውሳኔ ነበር?
  • ስለ ሐዋርያው ጴጥሮስ ምን የምታውቀው ነገር አለ?
  • ከዚህ እትም
  • ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
  • በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2010
  • መልስህ ምንድን ነው?
    ንቁ!—2009
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2010
  • መልስህ ምንድን ነው?
    ንቁ!—2008
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2010
g 12/10 ገጽ 13-31

ቤተሰብ የሚወያይበት

ጥሩ ውሳኔ ነበር?

ዘኍልቍ 13:1, 2, 25-33ን እና 14:3, 6-12ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ።

1. አብዛኞቹ ሰላዮች መጥፎ ወሬ ያሰራጩት ለምን ነበር?

․․․․․

2. አሥሩ ሰላዮች መጥፎ ወሬ ማሰራጨታቸው ምን አስከተለ?

ፍንጭ፦ ዘኍልቍ 14:26-38ን አንብብ።

․․․․․

3. ኢያሱና ካሌብ ድል እንደሚያደርጉ እርግጠኞች የነበሩት ለምንድን ነው?

․․․․․

ለውይይት፦

በቤተሰብህ ውስጥ ችግሮች ሲከሰቱ እንደ አሥሩ ሰላዮች ከመሆን ይልቅ ኢያሱንና ካሌብን መምሰል የምትችለው እንዴት ነው?

ስለ ሐዋርያው ጴጥሮስ ምን የምታውቀው ነገር አለ?

4. ጴጥሮስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠራባቸው አራት የተለያዩ ስሞች የትኞቹ ናቸው?

ፍንጭ፦ ማቴዎስ 10:2ን፤ 16:16ን እና ዮሐንስ 1:42ን አንብብ።

․․․․․

5. ጴጥሮስ አግብቶ ነበር?

ፍንጭ፦ 1 ቆሮንቶስ 9:5ን አንብብ።

․․․․․

ለውይይት፦

ስለ ጴጥሮስ ከሚገልጸው ታሪክ ውስጥ የምትወደውን ተናገር። ጴጥሮስ ከነበሩት ባሕርያት መካከል የትኞቹን ማንጸባረቅ ትፈልጋለህ? ይህንን ማድረግ የምትችለውስ እንዴት ነው?

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 7 ከባልንጀሮቻችን ጋር ምን መነጋገር አለብን? ኤፌሶን 4:․․․

ገጽ 8 እውነትን ማወቅህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል? ዮሐንስ 8:․․․

ገጽ 11 የመጨረሻው ጠላት ምን ይሆናል? 1 ቆሮንቶስ 15:․․․

ገጽ 24 ከምን ነገር መሸሽ ይኖርብሃል? 1 ቆሮንቶስ 6:․․․

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

● መልሶቹ በገጽ 13 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. በፍርሃት ስለተሸነፉና በይሖዋ ላይ የነበራቸው እምነት ስለጠፋ።—ዘኍልቍ 14:3, 11

2. ከካሌብና ከኢያሱ በስተቀር 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ወንዶች በሙሉ በምድረ በዳ ሞቱ።

3. ይሖዋ ከእነሱ ጋር እንደሆነ እምነት ስለነበራቸው።—ዘኍልቍ 14:9

4. ስምዖን፣ ጴጥሮስ፣ ስምዖን ጴጥሮስ (ሁለቱ ስሞች በአንድ ላይ) እና ኬፋ።

5. አዎ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ