የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 12/10 ገጽ 32
  • እናትየውም ትምህርት አግኝታበታለች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እናትየውም ትምህርት አግኝታበታለች
  • ንቁ!—2010
ንቁ!—2010
g 12/10 ገጽ 32

እናትየውም ትምህርት አግኝታበታለች

● ከባሏና ከሦስት ልጆቿ ጋር በኬንተኪ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የምትኖርና በ30ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የምትገኝ አንዲት እናት እንዲህ ብላ ጽፋለች፦ “እኔና ቤተሰቤ የይሖዋ ምሥክሮች ከሚያዘጋጇቸው ጽሑፎች ጥቅም አግኝተናል። በተለይ ለልጆቼ የምመርጠው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ የተባለውን መጽሐፍ ነው።” አክላም “እኔም ጭምር ትምህርት አግኝቼበታለሁ” ብላለች።

መጽሐፉ ማራኪ የሆኑ ሥዕላዊ መግለጫዎችን የያዘ ከመሆኑም በላይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን ታሪኮች በጊዜ ቅደም ተከተላቸው ይተርካል። ለምሳሌ ያህል፣ በክፍል 2 ውስጥ ከተካተቱት ታሪኮች መካከል “አንድ ክፉ ንጉሥ ግብፅን መግዛት ጀመረ፣” “ሕፃኑ ሙሴ ከሞት የዳነበት ሁኔታ፣” “ሙሴ የሸሸበት ምክንያት፣” “ሙሴና አሮን ፈርዖንን አነጋገሩት፣” “አሥሩ መቅሰፍቶች” እና “ቀይ ባሕርን መሻገር” የሚሉት ይገኙበታል።

“ኢየሱስ ከተወለደበት እስከሞተበት” የሚል ርዕስ ያለው ክፍል 6 ደግሞ ኢየሱስ ከተወለደበት ጊዜ አንስቶ እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ያሳለፈውን ሕይወት የሚተርኩ በርካታ ታሪኮችን ይዟል። ከእነዚህም መካከል “ኢየሱስ ጋጣ ውስጥ ተወለደ” እና “በኮከብ እየተመሩ የመጡ ሰዎች” የሚሉት ይገኙበታል። “በኮከብ እየተመሩ የመጡ ሰዎች” የሚለው ምዕራፍ “ጠቢባን” (ኮኮብ ቆጣሪዎች ናቸው) ኢየሱስን ለመጠየቅ በሄዱበት ጊዜ የገቡት “ወደ ቤት” እንጂ ወደተወለደበት ጋጣ እንዳልሆነ ይገልጻል። ሰዎቹ ቤቱ ውስጥ ሲገቡ “ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት።” ሄሮድስ ኢየሱስን ለመግደል ይፈልግ ስለነበር አምላክ ወደ ሄሮድስ ተመልሰው እንዳይሄዱ አስጠነቀቃቸው። ታዲያ ይህ ሁኔታ ለሰዎቹ ኮከብ የተባለውን ነገር ያሳያቸው ማን ስለመሆኑ ምን ይጠቁማል?—ማቴዎስ 2:1, 11, 12 አ.መ.ት.

እርስዎም የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ የተባለውን መጽሐፍ ለልጆችዎ ሲያነቡ ትምህርት ሊያገኙበት ይችላሉ። መጽሐፉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተጠቀሱ ሰዎችና በዚያን ጊዜ ስለተፈጸሙ ክንውኖች የሚናገሩ 116 ታሪኮች አሉት። የዚህን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

❑ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

❑ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ