የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 9/11 ገጽ 18
  • “ለአንቶን ጻፉለት!”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ለአንቶን ጻፉለት!”
  • ንቁ!—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2011
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2003
  • የተሳካላቸው ቤተሰቦች
    ንቁ!—2012
  • የደብዳቤ አጻጻፍ
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2011
g 9/11 ገጽ 18

“ለአንቶን ጻፉለት!”

● በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኝ አንቶን የተባለ አንድ የይሖዋ ምሥክር በሩሲያ ስታቭሮፖል ክራይ ውስጥ በጣም ርቃ በምትገኘው ሼልካን የምትባል መንደር ውስጥ ይኖር ነበር። አንቶን ገና በልጅነቱ ዱሼን በሚባል የጡንቻ በሽታ ተይዞ ነበር፤ ይህ በሽታ ጡንቻን በፍጥነት በማልፈስፈስ ታማሚው በአብዛኛው 20 ዓመት ሳይሞላው ለሞት የሚዳርግ የማይድን በሽታ ነው። አንቶን ዘጠኝ ዓመት በሆነው ጊዜ መራመድም ሆነ ከተቀመጠበት መነሳት አይችልም ነበር።

የቭጌኒ ከሚስቱ ከዲያና ጋር ሆኖ አንድን የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤ በሚጎበኝበት ጊዜ አንቶንን አገኘው። “አንቶን እጅግ ሲበዛ አቅም የለሽ ሆኖ ነበር” በማለት ዲያና ትገልጻለች። “ይሁን እንጂ በመንፈሳዊ ጠንካራ ነበር። ታላቅ ወንድሙ በተመሳሳይ በሽታ በ19 ዓመቱ ስለሞተ አንቶንም የቀረው ጊዜ አጭር እንደሆነ ያውቅ ነበር። ያም ሆኖ ደስተኛና ብሩህ አመለካከት ያለው ወጣት ነበር።”

ዲያናና ባሏ ርቀው በሚገኙ ሌሎች መንደሮች ለሚኖሩ ሰዎች ደብዳቤ በመጻፍ ምሥራቹን በመስበክ የሚያሳልፈውን ጊዜ ከፍ እንዲያደርግ አንቶንን አበረታቱት። በ2005 አንቶን 500 የሚያህሉ ደብዳቤዎችን ጽፎ በአቅራቢያው ባሉ መንደሮች ለሚገኙ ነዋሪዎች በአድራሻቸው ላከላቸው። ይሁን እንጂ የሚያሳዝነው ነገር አንድም ምላሽ አላገኘም። አንቶን የተስፋ መቁረጥ ስሜት ቢያድርበትም ደብዳቤ መጻፉን አላቋረጠም፤ እንዲሁም አሁን ባለበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ምሥራቹን በመስበክ ረገድ ውጤታማ መሆን የሚችልበትን መንገድ ይሖዋ እንዲያሳየው አጥብቆ ጸለየ።

አንድ ቀን አንቶን ጋዜጣ እያነበበ ሳለ መጽናኛ ማግኘት የምትፈልግ አንዲት ታማሚ ሴት የጻፈችውን ደብዳቤ ተመለከተ። አንቶን ለዚህች ሴት ደብዳቤ የጻፈላት ሲሆን የደብዳቤው ሐሳብ በከፊል በዚያው ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወጣ፤ በደብዳቤው ላይ እንዲህ ብሎ ነበር፦ “የያዘኝ በሽታ የማይድን ቢሆንም መጽሐፍ ቅዱስን ማንበቤ የወደፊቱን ጊዜ በተመለከተ እርግጠኛ ተስፋ እንዲኖረኝ ረድቶኛል። ሰዎች ደብዳቤ ቢጽፉልኝ በጣም ደስ ይለኛል፤ ካሁን ካሁን ደብዳቤ ይደርሰኛል ብዬ ሁልጊዜ በጉጉት እጠብቃለሁ።”

ሴትየዋ በደብዳቤው ልቧ ስለተነካ ለዚያው ጋዜጣ ደብዳቤ ጻፈች። ደብዳቤዋም “ለአንቶን ጻፉለት!” በሚል ርዕስ ታትሞ ወጣ። ሴትየዋ አንቶን በደብዳቤው ላይ ለገለጻቸው መንፈሳዊ ሐሳቦች ያላትን አድናቆት የገለጸች ሲሆን አክላም እንዲህ ብላለች፦ “አንቶንን ልንረዳው ይገባል! ሲጽፍላችሁ መልሳችሁ ጻፉለት። ይህ ወጣት የሚያጽናኑ ሐሳቦችን ማግኘት ያስፈልገዋል!” በጋዜጣው ላይ የአንቶን አድራሻም ወጥቶ ነበር።

ከዚያም አንቶን በመንደሩ በምትገኘው ትንሽ ፖስታ ቤት በኩል በየቀኑ እስከ 30 የሚደርሱ ደብዳቤዎች ይጎርፉለት ጀመር! ደብዳቤዎቹ የሚመጡለት ከመላው ሩሲያ እንዲሁም ከባልቲክ አገሮችና ከጀርመን ሌላው ቀርቶ ከፈረንሳይ ጭምር ነበር። አንቶን ጋዜጣውን ከሚያነቡ ሰዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ደብዳቤዎች ደረሱት። ዲያና እንዲህ በማለት ታስታውሳለች፦ “አንቶን የተሰማው ደስታ ወደር አልነበረውም! አሁን ደብዳቤ ሊጽፍላቸውና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ እምነቱን ሊያካፍላቸው የሚችል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሉ።”

አንቶን ደብዳቤ ከሚልኩለት ሰዎች ጋር ከአንድ ዓመት በላይ የተጻጻፈ ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለእነሱ ማካፈል ችሏል። እያደር እጆቹ እየደከሙ ሲሄዱ የሚልካቸውን ደብዳቤዎች ሰዎች እንዲጽፉለት ማድረግ ጀመረ። አንቶን መስከረም 2008 በ20 ዓመቱ ሞተ። ምንም እንኳ አንቶን እጅግ ሲበዛ አቅም የለሽ የነበረ ቢሆንም እምነቱና ለስብከቱ ሥራ የነበረው ፍቅር በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ሰዎችን ልብ ለመንካት አስችሎታል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ