የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 11/12 ገጽ 11
  • የዝንቦች ሃልቲር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የዝንቦች ሃልቲር
  • ንቁ!—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2012
  • ፍሩት ፍላይ የተባለችው ዝንብ አስደናቂ የበረራ ችሎታ
    ንድፍ አውጪ አለው?
  • አስገራሚው የሦስት አፅቄዎች ዓለም
    ንቁ!—2000
  • የበራሪ ፍጥረታት ክንፍ
    ንቁ!—2009
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2012
g 11/12 ገጽ 11

ንድፍ አውጪ አለው?

የዝንቦች ሃልቲር

ዝንቦች በአየር ላይ እንደ ልባቸው ለመገለባበጥና አቅጣጫቸውን ለመቀየር የሚያስችላቸው ምንድን ነው? ኃይለኛ ነፋስ ቢነፍስባቸውም አቅጣጫቸውን ሳይለቁ ጉዟቸውን መቀጠል እንዲችሉ የሚረዳቸው ምንድን ነው? ለዚህ በተወሰነ መጠን አስተዋጽኦ የሚያደርጉት ከሁለቱም ክንፎቻቸው ጀርባ የሚገኙት ሃልቲር የሚባሉ ትናንሽ የአካላቸው ክፍሎች ናቸው።a

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ሃልቲር እንደ ክብሪት እንጨት ከታቹ ቀጭን ሆኖ ጫፉ አካባቢ ወፈር ይላል። ዝንቦች በሚበርሩበት ጊዜ ሃልቲሮቻቸው ከክንፎቻቸው ጋር እኩል በሆነ ፍጥነት ሆኖም በተቃራኒ አቅጣጫ ወደ ላይና ወደ ታች ይርገበገባሉ። የሳይንስ ሊቃውንት፣ ዝንቦች በሚበርሩበት ጊዜ ሚዛናቸውን ጠብቀው እንዲንቀሳቀሱ የሚረዷቸው ሃልቲሮቻቸው እንደሆኑ ማወቅ ችለዋል።

ኢንሳይክሎፒዲያ ኦቭ አዳፕቴሽንስ ኢን ዘ ናቹራል ወርልድ የተባለው መጽሐፍ እንደሚገልጸው ወፈር ያለው የሃልቲሮች ጫፍ “እንደ ሰዓት ፔንዱለም በአንድ የተወሰነ አቅጣጫ ብቻ ይንቀሳቀሳል።” ኢንሳይክሎፒዲያው እንደገለጸው አንድ ዝንብ በሚበርበት ጊዜ ፈልጎም ይሁን ነፋስ ሲነፍስበት ድንገት ቢገለበጥ “ሃልቲሩም ተጠምዝዞ አቅጣጫውን ይቀይራል። በሃልቲሩ ላይ የሚገኙት በርካታ ነርቮች የሃልቲሩን እንቅስቃሴ ወደ አንጎል ያስተላልፋሉ፤ በዚህ ወቅት ዝንቡ . . . አቅጣጫውን እንዳይስት የሚያስችለውን እርምጃ ይወስዳል።” በዚህ ምክንያት ዝንቦች በሚበሩበት ጊዜ እንደ ልባቸው መገለባበጥ የሚችሉ ከመሆኑም ሌላ በቀላሉ አይያዙም።

መሐንዲሶች ከሮቦቶችና ከመንኮራኩሮች እንዲሁም የነፍሳትን የበረራ ዘዴ በመኮረጅ ከሚሠሩ ሮቦቶች ጋር በተያያዘ የሃልቲርን አሠራር በብዙ መንገዶች ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚቻል ይሰማቸዋል። የበረራ ቴክኖሎጂ ተመራማሪ የሆኑት ራፋል ዝቢኮቭስኪ “እንደ ዝንብ ካለች ትንሽና ብዙም የማትስብ ፍጥረት ይህ ሁሉ ትምህርት ይገኛል ብሎ ማን ያስባል?” ሲሉ ጽፈዋል።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? የዝንብ ሃልቲር በዝግመተ ለውጥ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

a ሃልቲር እንደ ዝንብና ቢንቢ ባሉት ባለ ሁለት ክንፍ ነፍሳት ክንፍ ላይ ተቀጥሎ የሚገኝ ነገር ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ