የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 1/14 ገጽ 14-15
  • ጣሊያንን እንጎብኝ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጣሊያንን እንጎብኝ
  • ንቁ!—2014
ንቁ!—2014
g 1/14 ገጽ 14-15
የጣሊያን የባሕር ዳርቻ

አገሮችና ሕዝቦች

ጣሊያንን እንጎብኝ

የጣሊያን ካርታ

ጣሊያን ከረጃጅም የባሕር ዳርቻዎች እስከ ሰንሰለታማ ተራራዎች፣ በስተ ደቡብ ካለው የበጋ ትኩሳት አንስቶ በስተ ሰሜን እስካለው በጣም ቀዝቃዛ የሆነ የክረምት ወቅት የተለያዩ ገጽታዎችን የተላበሰች አገር ነች። ጣሊያን እሳተ ገሞራ የሚበዛባት አገር ብትሆንም የመፈንዳት አዝማሚያ የሚታይባቸው እሳተ ገሞራዎች በጣም ጥቂት ናቸው፤ ከእነዚህም መካከል የስትሮምቦሊ ደሴትና የኤትና ተራራ ይገኙበታል።

ጣሊያን ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ካላቸው የአውሮፓ አገሮች አንዷ ነች። አረቦችን፣ ባይዛንታይኖችን፣ ግሪኮችን፣ ኖርማኖችንና ፊንቃውያንን ጨምሮ ብዙ ሕዝቦች ተመላልሰውባታል።

ቱሪስቶች በጎንዶላ ሲንሸራሸሩ

ቱሪስቶች በቬኒስ በሚገኙ በርካታ የውኃ መተላለፊያዎች ጎንዶላ በሚባሉ ጀልባዎች ይንሸራሸራሉ

አገሪቱ በታሪካዊ እሴቶችና በኪነ ጥበብ ውጤቶች የበለጸገች ናት። የጥንቶቹ ግሪካውያንና ሮማውያን የገነቧቸው ሕንፃዎች ፍርስራሽ ወይም እጅግ የተራቀቁ የኪነ ጥበብ ሥራዎችና የሬነሳንስ ኪነ ሕንፃዎች በበርካታ የጣሊያን ከተሞች ግርማ ሞገስ ተላብሰው ይታያሉ። የቀለም ቅብ ሥዕሎች፣ የእብነ በረድ ሐውልቶች እንዲሁም በከተሞች መካከል የተገነቡ የውኃ ፏፏቴዎች እንደ በርኒኒ፣ ሚካኤልአንጀሎና ራፋኤል ያሉትን ታላላቅ የኪነ ጥበብ ሰዎች ያስታውሱናል።

ምግብ በጣሊያናውያን የዕለት ተዕለት ኑሮ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሲሆን ከምግብ ጋር በተያያዘ ብዙ ልማዶች አሏቸው። ብዙ ጊዜ በመጀመሪያ የሚቀርበው ምግብ ፓስታ ሲሆን ከዚያ በኋላ ሥጋ ወይም ዓሣ ከአትክልት ጋር ይቀርባል። የወይራ ዘይት በከፍተኛ መጠን ስለሚመረት በብዛት ጥቅም ላይ ይውላል። ፒሳና ከሩዝ የሚዘጋጀው ሪዞቶ የተባለው ምግብ በጣም የታወቁ የጣሊያን ምግቦች ናቸው።

ፓስታ

ፓስታ የጣሊያናውያን ዋነኛ ምግብ ነው

ጣሊያናውያን በእንግዳ ተቀባይነታቸው፣ በሰው ወዳድነታቸውና በተጫዋችነታቸው ይታወቃሉ። ከሰዎች ጋር መግባባት እንደ ችሎታ ስለሚቆጠር በአደባባዮች ወይም ሰው በሚንሸራሸርባቸው ጎዳናዎች ሞቅ ባለ ስሜት የሚያወሩ ሰዎች መመልከት የተለመደ ነው።

አብዛኞቹ ጣሊያናውያን የሮም ካቶሊክ እምነት ተከታይ እንደሆኑ ይናገሩ እንጂ ቤተ ክርስቲያን የሚያዘወትሩት ጥቂቶች ናቸው። ከቅርብ አሥርተ ዓመታት ወዲህ ቤተ ክርስቲያኒቷ ያላት ተሰሚነት እየቀነሰ መጥቷል፤ ሕዝቡ ቤተ ክርስቲያኗ ውርጃንና ፍቺን በተመለከተ ለረጅም ዘመናት ስትከተለው የነበረውን አቋም ችላ እያለ መምጣቱ ይህን ያሳያል።

በጣሊያን የይሖዋ ምሥክሮች ቁጥር በጣም እየጨመረ ነው። በሕዝባዊ አገልግሎታቸው አማካኝነት መጽሐፍ ቅዱስን በማስተማርና የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያዎች ጠብቀው በመኖር በሰፊው ይታወቃሉ። በመላ አገሪቱ ከ3,000 የሚበልጡ የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች ያሉ ሲሆን ከእነዚህ ጉባኤዎች ብዙዎቹ ከጣሊያንኛ የተለየ ቋንቋ ለሚናገሩ ሰዎች ምሥራቹን ለማድረስ ጥረት ያደርጋሉ። ባለፈው አሥር ዓመት ውስጥ በጣሊያን የሚኖሩ የውጭ አገር ሰዎች ቁጥር በሦስት እጥፍ ማደጉ የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት በውጭ አገር ቋንቋዎች ማስተማር ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ያሳያል።

የዶሎማይት ተራራዎች

በሰሜናዊ ምሥራቅ ጣሊያን የሚገኙ የዶሎማይት ተራራዎች

ይህን ያውቁ ኖሯል?

የቫቲካን ከተማ የምትገኘው ሮም ውስጥ ቢሆንም ከ1929 ጀምሮ ራሷን የቻለች አገር ሆናለች፤ በዚህ ምክንያት ቫቲካን በጣሊያናውያን ዘንድ ሌላ አገር እንደሆነች ተደርጋ ትቆጠራለች።

አጭር መረጃ

  • የሕዝብ ብዛት፦ 61,000,000 ገደማ

  • ዋና ከተማ፦ ሮም

  • የአየር ንብረት፦ በስተ ደቡብ የአገሪቱ ክፍል በሜድትራንያን አካባቢ ያለው ዓይነት የአየር ንብረት ይኸውም ቅዝቃዜ የማይበረታበት ክረምትና ረዘም ያለ ሞቃታማ የበጋ ወቅት አለ፤ በስተ ሰሜን ደግሞ ደጋማ ሲሆን ክረምቱ ቀዝቃዛ ነው

  • አገር፦ አብዛኛው የአገሪቱ ክፍል ተራራማ ሲሆን ጣሊያን 7,500 ኪሎ ሜትር የሚደርስ የባሕር ዳርቻ አላት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ