የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 3/14 ገጽ 10-11
  • ኤል ሳልቫዶርን እንጎብኝ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኤል ሳልቫዶርን እንጎብኝ
  • ንቁ!—2014
ንቁ!—2014
g 3/14 ገጽ 10-11
ኤል ሳልቫዶርን የሚያሳይ ፎቶግራፍ

አገሮችና ሕዝቦች

ኤል ሳልቫዶርን እንጎብኝ

የኤል ሳልቫዶር ካርታ

ከአምስት መቶ ዓመታት ገደማ በፊት ስፔናውያን አሁን ኤል ሳልቫዶር ተብላ ወደምትጠራው አገር ከመስፈራቸው በፊት የአገሪቱ ዋነኛ ጎሣ አባላት አገሪቱን ኩስካትላን በማለት ይጠሯት ነበር፤ ትርጉሙም “ዕንቁዋ ምድር” ማለት ነው። ዛሬ አብዛኛው የኤል ሳልቫዶር ሕዝብ የጥንታዊዎቹ ጎሣዎችና የአውሮፓ ሰፋሪዎች ዝርያ ናቸው።

ሳልቫዶራውያን ታታሪዎችና ተግባቢዎች በመሆናቸው ይታወቃሉ። በተጨማሪም ጨዋዎችና ሰው አክባሪዎች ናቸው። ወሬ ከመጀመራቸው በፊት ወይም በሚገበያዩበት ወቅት “ቡዌኖስ ዲያስ” (እንዴት አደራችሁ?) ወይም “ቡዌናስ ታርዴስ” (እንዴት ዋላችሁ?) ይላሉ። እንዲያውም በገጠራማው አካባቢና በትናንሽ ከተሞች የሚኖሩ ሳልቫዶራውያን በመንገድ የሚያልፈውን ሰው ሰላምታ ሳይሰጡ ማለፍን እንደ ነውር ይቆጥሩታል።

ቡና የምትለቅም ሴት

የቡና እርሻ በኤል ሳልቫዶር ታሪክ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል

ሳልቫዶራውያን በጣም ከሚወዷቸው ምግቦች አንዱ ፑፑሳ ይባላል፤ ይህ ምግብ ከበቆሎ ወይም ከሩዝ ዱቄት የተሠራ ቂጣ ሆኖ መሃሉ ላይ ቺዝና ባቄላ እንዲሁም የአሳማ ሥጋና ሌሎች ነገሮች ይኖሩታል። ብዙ ጊዜ ከፑፑሳ ጋር የቲማቲም ወጥ እንዲሁም ጎመን፣ ካሮትና ቀይ ሽንኩርት በተቀመመ ኮምጣጤ ተለውሶ የሚዘጋጅ ኩርቲዶ የተባለ ምግብ ይቀርባል። አንዳንድ ሰዎች ቢላዋና ሹካ የሚጠቀሙ ቢሆንም ፑፑሳ በባሕላዊው መንገድ የሚበላው በእጅ ነው።

ፑፑሳ

ከኤል ሳልቫዶር ተወዳጅ ምግቦች አንዱ ፑፑሳ ነው

ሎስ ቴርስዮስ ፏፏቴ

በሱቺቶቶ የሚገኘው ሎስ ቴርስዮስ ፏፏቴ

ይህን ታውቅ ነበር? ኤል ሳልቫዶር የእሳተ ገሞራዎች አገር ተብላ ትጠራለች። በአገሪቱ ከ20 የሚበልጡ እሳተ ገሞራዎች ያሉ ሲሆን አንዳንዶቹ ንቅ እሳተ ገሞራ ማለትም አሁንም በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኙ ናቸው። ሎስ ቴርስዮስ የሚባለው ፏፏቴ በእሳተ ገሞራ አማካኝነት በተፈጠሩ ባለ ስድስት ማዕዘን ቅርጽ ባላቸው ረጃጅም የድንጋይ ዓምዶች ላይ ቁልቁል ይወረወራል።

በኤል ሳልቫዶር፣ ወደ 700 በሚጠጉ ጉባኤዎች የተደራጁ ከ38,000 የሚበልጡ የይሖዋ ምሥክሮች አሉ። በስፓንኛ፣ በእንግሊዝኛ እንዲሁም በሳልቫዶርኛ ምልክት ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስን 43,000 ለሚያህሉ ሰዎች ያስተምራሉ።

አጭር መረጃ

  • የሕዝብ ብዛት፦ 6,267,000

  • ዋና ከተማ፦ ሳን ሳልቫዶር

  • የሥራ ቋንቋ፦ ስፓንኛ

  • የአየር ንብረት፦ በባሕር ዳርቻዎችና በመሃል አገር ባሉ ዝቅተኛ አካባቢዎች እጅግ ሞቃታማ ሲሆን ከፍታ ባላቸው አካባቢዎች ደግሞ ቀዝቀዝ ያለ ነው

  • መልክዓ ምድር፦ አብዛኛው ክፍል ተራራማ ሲሆን በተራሮቹ መሃል አምባ ምድር ይገኛል

እውቀትህን ፈትሽ

እውነት ወይም ሐሰት ብለህ መልስ።

  1. ሀ. ከማዕከላዊ አሜሪካ አገሮች ትንሿ ኤል ሳልቫዶር ናት።

  2. ለ. በማዕከላዊ አሜሪካ ውስጥ የኤል ሳልቫዶርን ያህል ሕዝብ በብዛት የሚኖርበት አገር የለም።

  3. ሐ. አብዛኞቹ የሳልቫዶራውያን ምግቦች በጣም ያቃጥላሉ።

  4. መ. የቡና እርሻ በኤል ሳልቫዶር ታሪክ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል።

መልሶች፦ ‘1’፣ ‘2’ እና ‘4’ እውነት ሲሆኑ ‘3’ ግን ሐሰት ነው። አብዛኞቹ ጎብኚዎች የሳልቫዶራውያን ምግቦች ያን ያህል እንደማያቃጥሉ ይናገራሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ