የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 4/14 ገጽ 12-13
  • ካምቦዲያን እንጎብኝ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ካምቦዲያን እንጎብኝ
  • ንቁ!—2014
ንቁ!—2014
g 4/14 ገጽ 12-13
በካምቦዲያ የሚገኝ የሩዝ እርሻ

አገሮችና ሕዝቦች

ካምቦዲያን እንጎብኝ

የካምቦዲያ ካርታ

ካምቦዲያን የሚጎበኝ አንድ ሰው ተንሳፋፊ መንደሮችን፣ ትርምስ የበዛባቸውን ገበያዎች እንዲሁም ከዶሮ አንስቶ እስከ ማቀዝቀዣ ድረስ በጫኑ ሞተር ብስክሌቶች የተጨናነቁ መንገዶችን ማየቱ አይቀርም።

የካምቦዲያ ሕዝቦች ሞቅ ያሉ ብሎም ሰው ወዳድና የተሳሰረ ማኅበራዊ ግንኙነት ያላቸው በመሆናቸው ይታወቃሉ። በአክብሮት መጠሪያ መጠቀም የግድ በማይሆንበት ጊዜ እርስ በርሳቸው ሲጠራሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኙት ሰው ቢሆንም ወንድም፣ እህት፣ አክስት፣ አጎት፣ ወይም አያት መባባላቸው የተለመደ ነው።

በረጃጅም ምሰሶዎች አማካኝነት ከመሬት ከፍ ተደርገው ውኃ ላይ የተሠሩ ቤቶች

አንዳንድ ካምቦዲያውያን በጀልባ ቤቶች ላይ ሲኖሩ ሌሎች ደግሞ በረጃጅም ምሰሶዎች አማካኝነት ከመሬት ከፍ ተደርገው በተሠሩ ቤቶች ውስጥ ይኖራሉ። ትምህርት ቤቶች፣ ክሊኒኮች፣ ገበያዎችና የነዳጅ ማደያዎች ሳይቀሩ በውኃ ላይ ይሠራሉ

የድራጎን ፍሬ

የድራጎን ፍሬ በካምቦዲያ በጣም ተወዳጅ የሆነ የፍራፍሬ ዓይነት ነው

ዋነኛው የካምቦዲያውያን ምግብ ሩዝ ነው። አብዛኛውን ጊዜ በአንድ ገበታ ላይ ሦስት ወይም አራት የምግብ ዓይነቶች ይቀርባሉ፤ ብዙ ጊዜ ሾርባ አይጠፋም። ዓሣም ተወዳጅ ምግብ ነው። በአንድ ገበታ ላይ ጣፋጭ፣ የሚኮመጥጡና ጨዋማ የሆኑ ምግቦችን ማቅረብ የተለመደ ነው።

ከሁለት ሺህ ዓመታት ገደማ በፊት የሕንድ ነጋዴዎችና ሌሎች መንገደኞች ወደ ቻይና በሚጓዙበት ወቅት እግረ መንገዳቸውን ወደ ካምቦዲያ የባሕር ዳርቻዎች ጎራ በማለት ሐር እና ብረታ ብረቶችን በቅመማ ቅመሞች፣ ጥሩ መዓዛ ባላቸው እንጨቶች፣ በዝሆን ጥርስና በወርቅ መለወጥ ጀመሩ። ከጊዜ በኋላ የካምቦዲያ ሕዝቦች የሕንድን እና የቻይናን ባሕል በመላመዳቸው የሂንዱይዝምና የቡድሂዝም ሃይማኖት በአገሪቱ ተስፋፋ። በዛሬው ጊዜ፣ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት ነዋሪዎች ቡድሂስቶች ናቸው።

የይሖዋ ምሥክሮች በካምቦዲያ የመጽሐፍ ቅዱስን ተስፋ ለሰዎች ያካፍላሉ። ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? በተባለው መጽሐፍ አማካኝነት በርካታ ሰዎችን ረድተዋል። ይህ መጽሐፍ ካምቦዲያኛን ጨምሮ በ250 ገደማ ቋንቋዎች ይገኛል።

የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ተስፋ ለአንድ ካምቦዲያዊ ሲያካፍሉ

በካምቦዲያ ከ1,500 የሚበልጡ ሰዎች ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መጽሐፍ ቅዱስ በማጥናት ላይ ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስን በመማራቸው “ሙታን የት ናቸው?” እና “አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?” እንደሚሉት ላሉ ጥያቄዎች መልስ አግኝተዋል

አጭር መረጃ

  • የሕዝብ ብዛት፦ 14 ሚሊዮን ገደማ

  • ዋና ከተማ፦ ፕኖም ፔን

  • የአየር ንብረት፦ ዝናባማና ደረቅ ወቅቶች ያሉ ሲሆን የአየሩ ጠባይም ከሞቃት እስከ ሐሩር

  • የወጪ ምርት፦ አልባሳት፣ እንጨት፣ ጎማ፣ ሩዝ

ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለው መጽሐፍ በካምቦዲያኛ

በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀው ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለው መጽሐፍ በካምቦዲያኛ ቋንቋ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ