የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 4/15 ገጽ 8-9
  • ሆንዱራስን እንጎብኝ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሆንዱራስን እንጎብኝ
  • ንቁ!—2015
ንቁ!—2015
g 4/15 ገጽ 8-9
የሆንዱራስ የባሕር ዳርቻ

አገሮችና ሕዝቦች

ሆንዱራስን እንጎብኝ

የሆንዱራስ ካርታ

ሆንዱራስ በስፓንኛ ቋንቋ “ጥልቆች” ማለት ሲሆን ክሪስቶፈር ኮሎምበስ አገሪቷ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ጋር በምትዋሰንበት አካባቢ ያለውን ውኃ ጥልቀት ለመግለጽ የተጠቀመበት ቃል ሳይሆን አይቀርም። ሆንዱራስ ስሟን ያገኘችው በዚህ መንገድ እንደሆነ አንዳንዶች ይናገራሉ።

የሆንዱራስ ተወላጆች ለቤተሰብ ታማኝ መሆንን እንዲሁም ተባብሮ መሥራትን ከፍ አድርገው ይመለከታሉ። ለምሳሌ ያህል፣ ከቤት ወጪዎች ወይም ከልጆች ትምህርት ጋር የተያያዙ ትላልቅ ውሳኔዎች ብዙውን ጊዜ የሚደረጉት ባልና ሚስት ተመካክረው ነው።

አብዛኞቹ የሆንዱራስ ነዋሪዎች የአገሬው ተወላጆችና የአውሮፓውያን ክልሶች (ሜስቲዞ ተብለው ይጠራሉ) ናቸው። አንዳንዶቹ የአገሬው ተወላጆች እስከ ዛሬም ድረስ አሉ፤ ከእነዚህ መካከል ቾርቲ የተባለው ጎሳ አባላት ይገኙበታል። እንደ ጋሪፉና ያሉት ሌሎቹ የአገሬው ተወላጆች ደግሞ ከሌላ አካባቢ ከመጡ ሕዝቦች የተገኙ ናቸው።

የጋሪፉና ጎሳ አባል የሆነ ሙዚቀኛ በጠንካራ እንጨት የተሠራ ከበሮ ሲጫወት

የጋሪፉና ጎሳ አባል የሆነ አንድ ሙዚቀኛ በጠንካራ እንጨት በተሠራ ከበሮ ሲጫወት

የጋሪፉና ጎሳ አባላት የአፍሪካውያንና በሴንት ቪንሰንት ደሴት ላይ የሚኖሩ የአሜሪካ ሕንዳውያን ዝርያ ናቸው። የጋሪፉና ሕዝቦች በ1797 ገደማ ወደ ኢዝላስ ዴ ላ ባዪያ (ቤይ ደሴቶች) መጡ። ቆየት ብሎም የማዕከላዊ አሜሪካ ክፍል በሆነው በካሪቢያን የባሕር ዳርቻ ሰፈሩ። ከጊዜ በኋላ ወደ ሌሎች ማዕከላዊና ሰሜን አሜሪካ ክፍሎች ተሰራጩ።

የጋሪፉና ጎሳ አባላት ከጠንካራ እንጨቶች የተሠሩ ከበሮዎችን ምት እየተከተሉ መጨፈር ያስደስታቸዋል። ባሕላዊ ልብሳቸው በብሩህ ቀለማት ያሸበረቀ ሲሆን ተረት የማውራት ልማድም አላቸው፤ በተጨማሪም ኤሬባ የተባለውን ከካሳቫ ሥር የሚዘጋጅ ትልቅና ስስ ቂጣ ጨምሮ ሌሎች ባሕላዊ ምግቦች አሏቸው።

በሆንዱራስ 400 የሚያህሉ የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች አሉ። ስብሰባዎች የሚካሄዱት በዋነኝነት በስፓንኛ ቢሆንም በሆንዱራስ የምልክት ቋንቋ፣ በሚስኪቶ፣ በማንደሪን ቻይንኛ፣ በእንግሊዝኛ እና በጋሪፉና ቋንቋዎች የሚካሄዱም አሉ።

ኤሬባ

ኤሬባ የተባለው ከካሳቫ ሥር የሚዘጋጅ ትልቅና ስስ ቂጣ

አጭር መረጃ

  • የሕዝብ ብዛት፦ 8,111,000

  • ዋና ከተማ፦ ዲጉሲጋልፓ

  • የአስተዳደር ዓይነት፦ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ

  • ቋንቋ፦ ስፓንኛ

  • የአየር ንብረት፦ ደረቅና ሞቃታማ፣ በተራሮች አካባቢ ግን ለስለስ ያለ የአየር ጠባይ

  • መልክዓ ምድር፦ ከ75 በመቶ በላይ የሚሆነው የአገሪቱ ክፍል ተራራማ ነው። ረባዳ የሆኑ የባሕር ዳርቻዎችና ደሴቶችም አሉ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ