የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g20 ቁጥር 3 ገጽ 4-5
  • ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ሞክር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ሞክር
  • ንቁ!—2020
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እንዲህ አለማድረግ ምን ችግር አለው?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ
  • ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • ጭፍን ጥላቻ—አንተንም አጥቅቶህ ይሆን?
    ንቁ!—2020
  • ከወገናዊነት የመነጨ ጥላቻ ደርሶብሃልን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ጭፍን ጥላቻ ዓለም አቀፍ ችግር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ከጭፍን ጥላቻ የጸዳ ዓለም ይመጣ ይሆን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2020
g20 ቁጥር 3 ገጽ 4-5
ሁለት ወንዶች በአንድ የመኪና ፋብሪካ ውስጥ ልትቀጠር ለመጣች ሴት ቃለ መጠይቅ ሲያደርጉላት። ሴትየዋ የፈራች ትመስላለች።

ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ሞክር

እንዲህ አለማድረግ ምን ችግር አለው?

ጭፍን ጥላቻ በአብዛኛው የሚመነጨው ከተሳሳተ መረጃ ነው። እስቲ የሚከተሉትን ምሳሌዎች ተመልከት፦

  • አንዳንድ አሠሪዎች ሴቶች ከሳይንስ ወይም ከቴክኒክ ጋር ለተያያዙ ሥራዎች ብቁ አይደሉም የሚል የተሳሳተ አመለካከት አላቸው።

  • አውሮፓ ውስጥ በመካከለኛው መቶ ዘመን፣ አይሁዶች በሽታ ያዛምታሉ እንዲሁም የውኃ ጉድጓዶችን ይመርዛሉ በሚል በሐሰት ተወንጅለው ነበር፤ በናዚ አገዛዝ ወቅትም ጀርመን ውስጥ የኢኮኖሚ ቀውስ እንዲከሰት አድርገዋል የሚል ክስ ተሰንዝሮባቸዋል። በሁለቱም አጋጣሚዎች አይሁዶች እንዲህ ያለ ክስ የተሰነዘረባቸው በጭፍን ጥላቻ ምክንያት ነው። ይህ ጭፍን ጥላቻ በዛሬው ጊዜም ሙሉ በሙሉ አልተወገደም።

  • ብዙ ሰዎች፣ የአካል ጉዳተኞች ደስታ የራቃቸውና በምሬት የተሞሉ ናቸው የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ አላቸው።

እንዲህ ያሉ የተሳሳቱ አመለካከቶች ያሏቸው ሰዎች ይህን አመለካከታቸውን ይደግፋሉ ብለው የሚያስቧቸውን ምሳሌዎች ወይም ማስረጃዎች ሊጠቅሱ ይችላሉ። ይባስ ብሎ ደግሞ በእነሱ ሐሳብ የማይስማሙ ሁሉ የግንዛቤ ጉድለት እንዳለባቸው ይሰማቸዋል።

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ

“እውቀት የሌለው ሰው ጥሩ አይደለም።”—ምሳሌ 19:2

ከዚህ ጥቅስ ምን ትምህርት እናገኛለን? ትክክለኛ መረጃ ከሌለን የተሳሳተ መደምደሚያ ላይ ልንደርስ እንችላለን። እውነታውን ሳናጣራ የምንሰማውን ነገር ብቻ የምናምን ከሆነ ሰዎችን በተሳሳተ መንገድ መፈረጃችን አይቀርም።

መጽሐፍ ቅዱስ ጭፍን ጥላቻን ይደግፋል?

አንዳንዶች መጽሐፍ ቅዱስ ጭፍን ጥላቻን የሚደግፍ ሐሳብ እንደያዘ ይሰማቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ምን ይላል?

  • የሰው ልጆች ሁሉ የተገኙት ከአንድ አባት ነው፦ አምላክ “የሰውን ወገኖች በሙሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ።”—የሐዋርያት ሥራ 17:26

  • አምላክ አያዳላም፦ “አምላክ እንደማያዳላ በእርግጥ አስተዋልኩ፤ ከዚህ ይልቅ ከየትኛውም ብሔር ቢሆን እሱን የሚፈራና ትክክል የሆነውን ነገር የሚያደርግ ሰው በእሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው።”—የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35

  • አምላክ የሚያተኩረው በውጫዊ ገጽታ ላይ ሳይሆን በውስጣዊ ማንነት ላይ ነው፦ “ሰው የሚያየው ውጫዊ ገጽታን ነው፤ ይሖዋ ግን የሚያየው ልብን ነው።”—1 ሳሙኤል 16:7a

a መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው የአምላክ ስም ይሖዋ ነው።

ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

ትክክለኛ መረጃ ካለን ስለ አንዳንዶች በስፋት የሚነገሩ ሆኖም የተሳሳቱ አመለካከቶችን የምንቀበልበት አጋጣሚ ጠባብ ይሆናል። ደግሞም ስለ አንድ ቡድን የተነገረን መረጃ ውሸት መሆኑን ከተገነዘብን ስለ ሌሎች ቡድኖች የተነገሩን ነገሮችም ትክክል ስለመሆናቸው ጥያቄ ማንሳታችን አይቀርም።

እውነተኛ ታሪክ፦ ዮቪትሳ (አውሮፓ)

በእነዚህ ተከታታይ ርዕሶች ላይ ቀደም ሲል የተጠቀሰው ዮቪትሳ ከልጅነቱ ጀምሮ ከአካባቢው ሰዎች፣ ከዜና ዘገባዎችና ከቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ስለ አንድ አናሳ ቡድን አሉታዊ ወሬዎችን ይሰማ ነበር። ዮቪትሳ እንዲህ ሲል ተናግሯል፦ “ለእነዚያ ሰዎች ጭፍን ጥላቻ አድሮብኝ ነበር። ደግሞም እንደዚያ የሚሰማኝ መሆኑ ትክክል እንደሆነ አስብ ነበር።

“ሆኖም ወታደር ቤት ሳለሁ የዚያ አናሳ ቡድን አባል ከሆኑ ወታደሮች ጋር ሳልወድ በግድ አብሬ መኖርና መሥራት ነበረብኝ። በጊዜ ሂደት ስለ እነሱ ብዙ ነገሮች አወቅኩ። ሌላው ቀርቶ ቋንቋቸውን መማርና የእነሱን ሙዚቃ ማዳመጥ ጀመርኩ። ከእነሱ ጋር ጥሩ ግንኙነት መመሥረት ቻልኩ። ለእነሱ ያለኝ አመለካከትም እየተለወጠ ሄደ። እርግጥ ካልተጠነቀቅኩ ቀደም ሲል የነበረኝ ጭፍን ጥላቻ ሊያገረሽ ይችላል። በመሆኑም ስለዚያ ጎሳ አሉታዊ ነገር ከሚናገሩ የዜና ዘገባዎች ለመራቅ ጥረት አደርጋለሁ። በተጨማሪም በእነሱ ላይ ሲሾፍ የሚያሳዩ ፊልሞችን ወይም የኮሜዲ ፕሮግራሞችን አልከታተልም። ጭፍን ጥላቻ ወደ መረረ ጥላቻና ንዴት ሊያድግ እንደሚችል አውቃለሁ።”

ምን ማድረግ ትችላለህ?

  • ሰዎች ስለ አንድ ቡድን ያላቸው አሉታዊ አመለካከት በዚያ ቡድን ውስጥ ያለውን እያንዳንዱን ሰው ይወክላል ማለት እንዳልሆነ አስታውስ።

  • ስለ ሌሎች ያለህ መረጃ ውስን ሊሆን እንደሚችል አምነህ ተቀበል።

  • ተአማኒነት ካለው ምንጭ መረጃ ለማግኘት ጥረት አድርግ።

በጥላቻ ላይ ድል ተቀዳጅተዋል

1. ሁለት ወንዶች እርስ በርስ እየተጨዋወቱ ሲጓዙ። 2. ከሁለቱ ወንዶች አንዱ በወዳጆቹ ተከቦ ሲስቅ።

አንድ ዓረብና አንድ አይሁዳዊ የነበረባቸውን ጭፍን ጥላቻ እንዲያሸንፉ የረዳቸው ምንድን ነው?

ታማኝ ፍቅር ጥላቻን ድል የሚያደርገው መቼ ነው? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት። የቪዲዮውን ርዕስ jw.org/am ላይ ፈልግ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ