የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g20 ቁጥር 3 ገጽ 8-9
  • የሌሎችን ጠንካራ ጎን ለማስተዋል ሞክር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሌሎችን ጠንካራ ጎን ለማስተዋል ሞክር
  • ንቁ!—2020
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እንዲህ አለማድረግ ምን ችግር አለው?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • ጭፍን ጥላቻ የሚያከትምበት ጊዜ
    ንቁ!—2004
  • ጭፍን ጥላቻ—አንተንም አጥቅቶህ ይሆን?
    ንቁ!—2020
  • ከጭፍን ጥላቻ የጸዳ ዓለም ይመጣ ይሆን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ጭፍን ጥላቻና መድሎ—መንስኤያቸውን ለይቶ ማወቅ
    ንቁ!—2009
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2020
g20 ቁጥር 3 ገጽ 8-9
1. እየተቻኮሉ ያሉ ባልና ሚስት አንዲት ማየት የተሳናት ሴት መንገድ ስለዘጋችባቸው ተበሳጭተው። 2. በኋላ ላይ እነዚያው ባልና ሚስት ያቺ ማየት የተሳናት ሴት በሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ቼሎ ስትጫወት በችሎታዋ ተደምመው ሲመለከቱ።

የሌሎችን ጠንካራ ጎን ለማስተዋል ሞክር

እንዲህ አለማድረግ ምን ችግር አለው?

ኩራት ጭፍን ጥላቻ እንዲያድርብን ሊያደርግ ይችላል። ኩሩ የሆነ ሰው ለራሱ የተጋነነ አመለካከት አለው። ራሱን ከሌሎች አስበልጦ የሚመለከት ሲሆን ከእሱ የተለዩ ሰዎች የእሱ የበታች እንደሆኑ አድርጎ ያስባል። ማንም ሰው በዚህ ወጥመድ ሊያዝ ይችላል። ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንዲህ ይላል፦ “መጠኑ ይነስ ይብዛ እንጂ አብዛኞቹ ባሕሎች የእነሱ ምግብ፣ አኗኗር፣ አለባበስ፣ ልማድ፣ አመለካከት፣ እሴት፣ ወዘተ ከሌሎች የተሻለ እንደሆነ ይሰማቸዋል።” ታዲያ እንዲህ ያለውን የተዛባ አስተሳሰብ ማስወገድ የምንችለው እንዴት ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ

“ሌሎች ከእናንተ እንደሚበልጡ በትሕትና አስቡ።”—ፊልጵስዩስ 2:3

ከዚህ ጥቅስ ምን ትምህርት እናገኛለን? ከልክ ያለፈ ኩራትን ለማስወገድ የእሱ ተቃራኒ የሆነውን ባሕርይ ማለትም ትሕትናን ማዳበር ያስፈልገናል። ትሕትና በአንዳንድ ነገሮች ሌሎች ከእኛ እንደሚበልጡ እንድንገነዘብ ይረዳናል። በሁሉም ዘርፍ የተሻለ ነው ተብሎ ሊፈረጅ የሚችል አንድ ቡድን ሊኖር አይችልም።

የሽቴፋንን ሁኔታ እንደ ምሳሌ እንመልከት። ሽቴፋን ያደገው በአንድ የኮሚኒስት አገር ውስጥ ሲሆን ኮሚኒስት ባልሆኑ አገሮች ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ጭፍን ጥላቻ ነበረው። በኋላ ላይ ግን ይህን ስሜቱን ማስወገድ ችሏል። እንዲህ ብሏል፦ “ጭፍን ጥላቻን ለማስወገድ የሚረዳው ትልቁ ነገር ሌሎች ከእናንተ እንደሚበልጡ አድርጎ ማሰብ እንደሆነ አምናለሁ። ሁሉንም ነገር አውቃለሁ ማለት አልችልም። ከእያንዳንዱ ሰው የሆነ ነገር መማር እችላለሁ።”

ምን ማድረግ ትችላለህ?

ስለ ራስህ ሚዛናዊ አመለካከት ለመያዝ ጥረት አድርግ። አንዳንድ ጉድለቶች እንዳሉብህ አትዘንጋ። አንተ ደካማ በሆንክባቸው አንዳንድ አቅጣጫዎች ሌሎች ጠንካራ ሊሆኑ እንደሚችሉ አምነህ ተቀበል። በአንድ ቡድን ውስጥ የሚካተቱ ሰዎች በሙሉ ተመሳሳይ ድክመት እንዳለባቸው አድርገህ አታስብ።

አንድ ሰው የሆነ ቡድን አባል ስለሆነ ብቻ ስለ እሱ አሉታዊ አመለካከት ከመያዝ ይልቅ ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

አንተ ደካማ በሆንክባቸው አንዳንድ አቅጣጫዎች ሌሎች ጠንካራ ሊሆኑ እንደሚችሉ አምነህ ተቀበል

  • ‘የዚህን ሰው አንዳንድ ባሕርያት የምጠላው በእርግጥ መጥፎ ስለሆኑ ነው ወይስ እኔ ከለመድኩት የተለዩ ስለሆኑ?’

  • ‘ይህ ሰው በእኔስ ላይ ጉድለት ሊያገኝ አይችልም?’

  • ‘ይህ ሰው ከእኔ የተሻለ የሆነባቸው አንዳንድ ነገሮች የትኞቹ ናቸው?’

ለእነዚህ ጥያቄዎች በሐቀኝነት መልስ መስጠትህ በውስጥህ ያለውን ማንኛውንም ዓይነት ጭፍን ጥላቻ እንድታስወግድ ብቻ ሳይሆን ስለዚያ ሰው የምታደንቃቸው አንዳንድ ነገሮች እንድታገኝም ይረዳሃል።

እውነተኛ ታሪክ፦ ኔልሰን (ዩናይትድ ስቴትስ)

“አብዛኛውን የልጅነት ሕይወቴን ያሳለፍኩት ተመሳሳይ ዘርና አስተዳደግ ያላቸው ሰዎች በሚኖሩበት አካባቢ ነው። አሥራ ዘጠኝ ዓመት ሲሞላኝ ግን በአንድ ፋብሪካ ውስጥ ለመሥራት ተለቅ ወዳለ ከተማ ተዛወርኩ። በዚያም የተለያየ ዘር፣ አስተዳደግና ባሕል ካላቸው ሰዎች ጋር አብሬ መሥራትና መኖር ጀመርኩ።

“የሥራ ባልደረቦቼን ይበልጥ እያወቅኳቸው ስሄድና ከእነሱ ጋር ጓደኝነት ስመሠርት ከሰዎች የቆዳ ቀለም፣ አፍ መፍቻ ቋንቋና ብሔር በመነሳት ሰዎቹ ምን ያህል ታታሪና እምነት የሚጣልባቸው እንደሆኑ ወይም ስለ አንድ ነገር ምን እንደሚሰማቸው ማወቅ እንደማይቻል ተገነዘብኩ።

“በኋላም ከእኔ የተለየ የትውልድ አገርና ዘር ካላት ሴት ጋር ትዳር መሠረትኩ። ለየት ያሉ ምግቦችን መቅመስና ሰምቼ የማላውቃቸውን ሙዚቃዎች ማዳመጥ ብዙ ደስታ አስገኝቶልኛል። ሕይወት ሁላችንም ጠንካራም ሆነ ደካማ ጎን እንዳለን አስተምሮኛል። እውነቱን ለመናገር ከእኔ በጣም የተለየ ዘርም ሆነ ባሕል ያላቸውን ሰዎች በጎ ጎኖች ማድነቅና መኮረጅ መቻሌ የተሻልኩ ሰው እንድሆን ረድቶኛል።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ