የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g20 ቁጥር 3 ገጽ 10-11
  • ከተለያዩ ሰዎች ጋር ጓደኝነት መሥርት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከተለያዩ ሰዎች ጋር ጓደኝነት መሥርት
  • ንቁ!—2020
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እንዲህ አለማድረግ ምን ችግር አለው?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ
  • ከተለያዩ ሰዎች ጋር ጓደኝነት መመሥረት ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • የጭፍን ጥላቻን ግድግዳ ማፍረስ ችለዋል
    ንቁ!—2020
  • ፍቅር ለማሳየት ጥረት አድርግ
    ንቁ!—2020
  • ተጨማሪ ጓደኞችን ማፍራት ይኖርብኝ ይሆን?
    የወጣቶች ጥያቄ
  • ጓደኛ የማግኘት ፍላጎታችንን ማሟላት
    ንቁ!—2005
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2020
g20 ቁጥር 3 ገጽ 10-11
የተለያየ ዘር ያላቸው አራት ሴቶች እያወሩና እየተሳሳቁ፤ ከበስተጀርባ ልጆቻቸው አብረው ሲጫወቱ ይታያል።

ከተለያዩ ሰዎች ጋር ጓደኝነት መሥርት

እንዲህ አለማድረግ ምን ችግር አለው?

በአሉታዊ መንገድ ከምንመለከታቸው ሰዎች ራሳችንን የምናገል ከሆነ ጭፍን ጥላቻችን ይበልጥ ሥር እየሰደደ ሊሄድ ይችላል። በተጨማሪም ከእኛ ጋር ከሚመሳሰሉ ሰዎች ጋር ብቻ ጓደኝነት የምንመሠርት ከሆነ ተቀባይነት ያለው የእኛ አስተሳሰብ፣ ስሜትና ድርጊት ብቻ እንደሆነ አድርገን ማሰብ ልንጀምር እንችላለን።

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ

“ልባችሁን ወለል አድርጋችሁ ክፈቱ።”—2 ቆሮንቶስ 6:13

ከዚህ ጥቅስ ምን ትምህርት እናገኛለን? “ልብ” የሚለው አገላለጽ የአንድን ሰው ስሜት ያመለክታል። ከእኛ ጋር የሚመሳሰሉ ሰዎችን ብቻ የምንወድ ከሆነ ልባችን ዝግ ወይም ጠባብ ሊሆን ይችላል። ይህን ችግር ለማስወገድ ከእኛ ጋር ከማይመሳሰሉ ሰዎችም ጋር ጓደኝነት ለመመሥረት ፈቃደኞች መሆን አለብን።

ከተለያዩ ሰዎች ጋር ጓደኝነት መመሥረት ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

ሰዎችን በግለሰብ ደረጃ ስናውቃቸው አንዳንድ ነገሮችን ከእኛ በተለየ መንገድ የሚያደርጉት ለምን እንደሆነ መረዳት እንጀምራለን። ደግሞም ይበልጥ እየቀረብናቸው ስንሄድ ከእኛ የተለዩ መሆናቸውን እንኳ ጨርሶ ልንረሳው እንችላለን። ለእነሱ ያለን አክብሮት የሚጨምር ከመሆኑም ሌላ የደስታቸውም ሆነ የሐዘናቸው ተካፋዮች እንሆናለን።

የናዛሬን ሁኔታ እንደ ምሳሌ እንመልከት። በአንድ ወቅት ለስደተኞች ጭፍን ጥላቻ ነበራት። የነበረባትን ጭፍን ጥላቻ ለማስወገድ የረዳት ምን እንደሆነ ስትናገር እንዲህ ብላለች፦ “ከእነሱ ጋር ጊዜ ማሳለፍና አብሬ መሥራት ጀመርኩ። ይህም ሌሎች ከሚያስቧቸው ፈጽሞ የተለዩ ሰዎች እንደሆኑ እንዳስተውል ረድቶኛል። ከእናንተ የተለየ ባሕል ካላቸው ሰዎች ጋር መቀራረብ ሁሉንም በአንድ ከመፈረጅ እንድትርቁ ይረዳችኋል። ለእነሱ በግለሰብ ደረጃ ፍቅርና አክብሮት ማዳበር ትጀምራላችሁ።”

መጠንቀቅ ያለብህ ነገር

አንዳንድ ሰዎች ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች ጎጂ የሆነ የአኗኗር ዘይቤና ልማድ አላቸው። በመሆኑም ከተለያዩ ሰዎች ጋር ጓደኝነት ለመመሥረት ጥረት ብናደርግም በጓደኛ ምርጫ ረገድ ጠንቃቆች መሆን አለብን። ሥነ ምግባር ከጎደላቸው ወይም መጥፎ ባሕርይ ካላቸው ሰዎች ጋር ጓደኝነት ከመመሥረት መራቅ እንደ ጭፍን ጥላቻ ሊቆጠር አይችልም። ከአንተ የተለየ የሥነ ምግባር መሥፈርት ያላቸውን ሰዎች ለመጉዳት ወይም መብታቸውን ለመጋፋት መሞከር ተገቢ ባይሆንም ከእነሱ ጋር ጓደኝነት ከመመሥረት መቆጠብ ጥበብ ነው።—ምሳሌ 13:20

ምን ማድረግ ትችላለህ?

ከሌላ አገር ከመጡ አሊያም ከአንተ የተለየ ዘር ወይም ቋንቋ ካላቸው ሰዎች ጋር የምትነጋገርበት አጋጣሚ ፈልግ። ለምሳሌ የሚከተሉትን ነገሮች ልታደርግ ትችላለህ፦

  • ስለ ራሳቸው አንዳንድ ነገሮችን እንዲነግሩህ ጠይቃቸው።

  • አብረውህ እንዲመገቡ ጋብዛቸው።

  • ስለ ራሳቸው ሲያወሩ በትኩረት በማዳመጥ ትልቅ ቦታ ስለሚሰጡት ነገር ለማወቅ ጥረት አድርግ።

ያሳለፉት ሕይወት ማንነታቸውን የቀረጸው እንዴት እንደሆነ ለመረዳት መሞከርህ ለእነሱም ሆነ የዚያ ቡድን አባል ለሆኑ ሌሎች ሰዎች አዎንታዊ አመለካከት ለማዳበር ይረዳሃል።

እውነተኛ ታሪክ፦ ካንዳሳሚ እና ሱካማ (ካናዳ)

“ያደግነው ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በአፓርታይድ ዘመን ነው። የተለያየ ዘር ያላቸው ሰዎች አብረው እንዲኖሩ አይፈቀድላቸውም ነበር። ይህም በሰዎች መካከል ጭፍን ጥላቻ እንዲቀሰቀስ አድርጓል። እኛ ነጮች አይደለንም፤ ደግሞም ነጮቹ የእነሱ የበታች አድርገው ስለሚመለከቱን እንጠላቸው ነበር። በወቅቱ ጭፍን ጥላቻ እንዳለብን አይሰማንም ነበር። እንዲያውም የጭፍን ጥላቻ ሰለባ እንደሆንን አድርገን ነበር የምናስበው።

“አመለካከታችንን መቀየር ስለፈለግን የተለያየ ዘርና አስተዳደግ ካላቸው ሰዎች ጋር ጓደኝነት ለመመሥረት ጥረት አደረግን። ከነጮች ጋር ጊዜ ማሳለፍ ስንጀምር በእኛና በእነሱ መካከል ያን ያህል ልዩነት እንደሌለ ተገነዘብን። ሁላችንም በሕይወት ውስጥ የሚያጋጥሙን ነገሮችና ተፈታታኝ ሁኔታዎች ተመሳሳይ ናቸው።

“በተጨማሪም አንድ ነጭ ባልና ሚስት ረዘም ላለ ጊዜ ቤታችን በእንግድነት እንዲያርፉ ተቀበልን። ይህም እነሱን በደንብ ለማወቅ አጋጣሚ ሰጠን። አንዳችን ከሌላው እንደማንበልጥ መገንዘብና በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥሩ ወዳጅነት መመሥረት ቻልን። አሁን ለነጮች ጥሩ አመለካከት አለን።”

እውነተኛ ወንድማማቾች

ጆኒና ጊዲየን ከይሖዋ ምሥክሮች የስብሰባ አዳራሽ ውጭ ቆመው ልጆችን ሰላም ሲሉ።

ጆኒና ጊዲየን ከተለያየ ዘር የመጡና የተለያየ ፖለቲካዊ አመለካከት የነበራቸው ቢሆንም ከጊዜ በኋላ የቅርብ ወዳጆች መሆን ችለዋል።

ጆኒና ጊዲየን፦ ከጠላትነት ወደ ወንድማማችነት የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት። የቪዲዮውን ርዕስ jw.org/am ላይ ፈልግ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ