የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g20 ቁጥር 3 ገጽ 14-15
  • ፍቱን መድኃኒት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ፍቱን መድኃኒት
  • ንቁ!—2020
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መፍትሔ የሚያመጣ መንግሥት
  • 1. የላቀ ትምህርት
  • 2. ፈውስ
  • 3. መልካም አስተዳደር
  • 4. አንድነት
  • ጭፍን ጥላቻ—አንተንም አጥቅቶህ ይሆን?
    ንቁ!—2020
  • ይሖዋና ኢየሱስ አንድ እንደሆኑ ሁላችንም አንድ እንሁን
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
  • ጭፍን ጥላቻ የሚያከትምበት ጊዜ
    ንቁ!—2004
  • ከጭፍን ጥላቻ የጸዳ ዓለም ይመጣ ይሆን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2020
g20 ቁጥር 3 ገጽ 14-15
የተለያየ ዕድሜና ዘር ያላቸው ሰዎች እየሳቁ።

ፍቱን መድኃኒት

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ቀደም ባሉት ርዕሶች ላይ የተጠቀሱትን ምክሮች ተግባራዊ ማድረጋቸው ጭፍን ጥላቻን በማስወገድ ረገድ ትልቅ ስኬት እንዲያገኙ ረድቷቸዋል። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን በራሳችን ጥረት ጭፍን ጥላቻን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ አንችልም። ታዲያ ጭፍን ጥላቻ ሊወገድ አይችልም ማለት ነው?

መፍትሔ የሚያመጣ መንግሥት

ሰብዓዊ መንግሥታት ጭፍን ጥላቻን በማስወገድ ረገድ እንዳልተሳካላቸው ታይቷል። ይህ ሲባል ታዲያ ጭፍን ጥላቻን ሊያስወግድ የሚችል መንግሥት የለም ማለት ነው?

አንድ መንግሥት ጭፍን ጥላቻን እንዲያስወግድ ከተፈለገ

  1. 1. ሰዎች ለሌሎች ያላቸውን አመለካከትና ስሜት እንዲለውጡ ሊያደርግ ይገባል።

  2. 2. ሰዎች ጭፍን ጥላቻ እንዲያድርባቸው የሚያደርገውን ስሜታዊ ቁስል ሊፈውስ ይገባል።

  3. 3. እያንዳንዱን ዜጋ በእኩል ዓይን የሚመለከቱ ጥሩ ገዢዎች ሊኖሩት ይገባል።

  4. 4. ሁሉንም ዓይነት ሰዎች አንድ ሊያደርግ ይገባል።

መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ እንዲህ ዓይነት መንግሥት እንዳቋቋመ ይናገራል። ይህ መንግሥት ‘የአምላክ መንግሥት’ በመባል ይታወቃል።—ሉቃስ 4:43

የአምላክ መንግሥት ምን ነገሮችን እንደሚያስገኝ እንመልከት።

1. የላቀ ትምህርት

“የምድሪቱ ነዋሪዎች ስለ ጽድቅ ይማራሉ።”—ኢሳይያስ 26:9

“የእውነተኛ ጽድቅ ውጤት ሰላም፣ የእውነተኛ ጽድቅ ፍሬም ዘላቂ ጸጥታና ደህንነት ይሆናል።”—ኢሳይያስ 32:17

ይህ ምን ማለት ነው? የአምላክ መንግሥት ትክክል የሆነው ነገር ምን እንደሆነ ለሰዎች ያስተምራል። ሰዎች ትክክልና ስህተት ማለትም ፍትሐዊ ስለሆነውና ስላልሆነው ነገር ሲማሩ አንዳቸው ለሌላው ያላቸው አመለካከት ይለወጣል። እያንዳንዱ ሰው ሁሉንም ዓይነት ሰው መውደድ እንዳለበት ይገነዘባል።

2. ፈውስ

አምላክ “እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም። ቀድሞ የነበሩት ነገሮች አልፈዋል።”—ራእይ 21:4

ይህ ምን ማለት ነው? የአምላክ መንግሥት የፍትሕ መዛባት ያስከተለውን ሥቃይ በሙሉ ያስወግዳል። ቀደም ሲል ኢፍትሐዊ ድርጊት የተፈጸመባቸው ሰዎች ጥላቻ እንዲያድርባቸው የሚያደርግ ምንም ምክንያት አይኖርም።

3. መልካም አስተዳደር

“ዓይኑ እንዳየ አይፈርድም ወይም ጆሮው በሰማው ነገር ላይ ብቻ ተመሥርቶ አይወቅስም። ለችግረኞች በትክክል ይፈርዳል፤ በምድር ላሉ የዋሆች ጥቅም ሲል ሌሎችን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ይወቅሳል።”—ኢሳይያስ 11:3, 4

ይህ ምን ማለት ነው? በሰማይ ያለው የአምላክ መንግሥት ንጉሥ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ምድርን ፍትሐዊና ከአድልዎ ነፃ በሆነ መንገድ ያስተዳድራል። ኢየሱስ አንዱን ብሔር ከሌላው የማያስበልጥ ከመሆኑም ሌላ በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች በሙሉ የእሱን የጽድቅ መሥፈርቶች እንዲታዘዙ ማድረግ ይችላል።

4. አንድነት

የአምላክ መንግሥት፣ ሰዎች ‘ፍጹም አንድነት ኖሯቸውና አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ይዘው በአንድ ሐሳብና በአንድ ፍቅር መኖር’ የሚችሉበትን መንገድ ያስተምራል።—ፊልጵስዩስ 2:2

ይህ ምን ማለት ነው? በአምላክ መንግሥት ዜጎች መካከል የሚኖረው አንድነት እንዲሁ ከላይ ከላይ የሚታይ ብቻ አይሆንም። አንዳቸው ሌላውን ከልብ ስለሚወዱ “ፍጹም አንድነት” ይኖራቸዋል።

እንዲህ ያለ መንግሥት ይመጣል ብሎ ማመን ምክንያታዊ ነው?

አዎ፣ ሆኖም እንዲህ ብሎ ለማመን በቅድሚያ ማስረጃዎቹን መመርመር ያስፈልጋል። ማስረጃዎቹን ለመመርመር የሚከተሉትን ሦስት አማራጮች እንድትጠቀም ግብዣ እናቀርብልሃለን፦

  • የአምላክ መንግሥት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት ተስፋዎች በቅርቡ እንዲፈጸሙ እንደሚያደርግ የሚጠቁሙ ማስረጃዎችን እንዲያሳይህ አንድን የይሖዋ ምሥክር ጠይቅ።

  • jw.org/am ላይ ገብተህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች > የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው > የአምላክ መንግሥት የሚለውን ተመልከት።

  • በአምላክ ሕዝቦች መካከል ያለውን ፍቅርና አንድነት ለማየት በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ ተገኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ