የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g24 ቁጥር 1 ገጽ 13-15
  • ለራስ አክብሮት ማሳየት ቀረ እንዴ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለራስ አክብሮት ማሳየት ቀረ እንዴ?
  • ንቁ!—2024
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለራስ አክብሮት ማሳየት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • ምን ጥረት እያደረግን ነው?
  • እርዳታ ማግኘት ትችላለህ
    ንቁ!—2020
  • ለቤተሰብ አክብሮት ማሳየት ቀረ እንዴ?
    ንቁ!—2024
  • ራሴን የማልወደው ለምንድን ነው?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች
  • በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ መገኘትህ የሚጠቅምህ እንዴት ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2024
g24 ቁጥር 1 ገጽ 13-15
በሐዘን የተዋጠች አንዲት ሴት ራሷን በመስታወት እያየች።

ለራስ አክብሮት ማሳየት ቀረ እንዴ?

ለራስ አክብሮት ማሳየት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ለራሳቸው አክብሮት ያላቸው ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን ተፈታታኝ ሁኔታዎች በልበ ሙሉነት መጋፈጥ ይችላሉ። በቀላሉ ተስፋ አይቆርጡም።

  • አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ ለራሳቸው ጥሩ አመለካከት የሌላቸው ሰዎች ለጭንቀት፣ ለድባቴና ለአመጋገብ መዛባት የመጋለጣቸው አጋጣሚ ሰፊ ነው። በተጨማሪም የመጠጥና የዕፅ ሱሰኛ የመሆናቸው አጋጣሚ ይጨምራል።

  • ለራሳቸው አክብሮት ያላቸው ሰዎች ራሳቸውን ከሌሎች ጋር አያወዳድሩም፤ ይህም በዙሪያቸው ካሉት ሰዎች ጋር ተስማምቶ መኖርና ጠንካራ ወዳጅነት መመሥረት ቀላል እንዲሆንላቸው ያደርጋል። በሌላ በኩል ደግሞ፣ ለራሳቸው አክብሮት የሌላቸው ሰዎች ተቺ የመሆን ዝንባሌ አላቸው፤ ይህም ከሌሎች ጋር ያላቸውን ወዳጅነት ሊያበላሸው ይችላል።

  • ለራሳቸው አክብሮት ያላቸው ሰዎች የሚያጋጥማቸውን ተፈታታኝ ሁኔታ በጽናት መቋቋም ይችላሉ፤ ያጋጠማቸው እንቅፋት ግባቸው ላይ ከመድረስ እንዲያግዳቸው አይፈቅዱም። በአንጻሩ ግን፣ ለራሳቸው አክብሮት የሌላቸው ሰዎች ያጋጠሟቸውን ትናንሽ እንቅፋቶች አግዝፈው የማየት ዝንባሌ አላቸው። ይህ ደግሞ በቀላሉ ተስፋ እንዲቆርጡ ሊያደርጋቸው ይችላል።

ምን ማድረግ ትችላለህ?

የሚያበረታቱ ጓደኞችን ምረጥ። አክብሮት ከሚያሳዩህ፣ ደህንነትህ ከልብ ከሚያሳስባቸው እንዲሁም ከሚያበረታቱህ ሰዎች ጋር ተቀራረብ።

“እውነተኛ ወዳጅ ምንጊዜም አፍቃሪ ነው፤ ደግሞም ለመከራ ቀን የተወለደ ወንድም ነው።”—ምሳሌ 17:17

ሌሎችን እርዳ። ለሌሎች ደግነት ስታሳይ እንዲሁም ውለታ ሊመልሱልህ የማይችሉ ሰዎችን ጨምሮ ለሌሎች መልካም ነገር ስታደርግ በመስጠት የሚገኘውን እውነተኛ ደስታ ታጣጥማለህ። ላከናወንከው መልካም ሥራ ባትመሰገንም እንኳ ሌሎችን መርዳትህ አንተን ይጠቅምሃል።

“ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል።”—የሐዋርያት ሥራ 20:35

ልጆችህ ለራሳቸው አክብሮት እንዲያዳብሩ እርዳቸው። ይህን ማድረግ የምትችልበት አንዱ መንገድ ያጋጠሟቸውን ችግሮች አቅማቸው በፈቀደ መጠን በራሳቸው እንዲፈቱ ማድረግ ነው። እንዲህ ማድረግህ፣ ልጆችህ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መቋቋምና ማሸነፍ የሚቻልበትን መንገድ እንዲማሩ ይረዳቸዋል። ልጆችህ ይህን ትምህርት ማግኘታቸው ለራሳቸው አክብሮት እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል፤ አዋቂ ከሆኑ በኋላም ይጠቅማቸዋል።

“ልጅን ሊሄድበት በሚገባው መንገድ አሠልጥነው፤ በሚያረጅበት ጊዜም እንኳ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።”—ምሳሌ 22:6

አንዲት የይሖዋ ምሥክር ሻይ ቤት ውስጥ አንዲትን ሴት መጽሐፍ ቅዱስ ስታስጠና።
አንዲት የይሖዋ ምሥክር ሻይ ቤት ውስጥ አንዲትን ሴት መጽሐፍ ቅዱስ ስታስጠና።

ምን ጥረት እያደረግን ነው?

ስብሰባዎቻችንና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮግራማችን ሰዎች ሕይወታቸውን እንዲያሻሽሉ ብሎም ለራሳቸው ያላቸውን አክብሮት እንዲያሳድጉ ይረዷቸዋል።

ሳምንታዊ ስብሰባዎቻችን

በሳምንታዊ ስብሰባዎቻችን ላይ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ንግግሮችን እናዳምጣለን። በእነዚህ ንግግሮች አማካኝነት፣ ለራሳችን አክብሮት ማዳበር የምንችልበትን መንገድ እንማራለን። በስብሰባዎቻችን ላይ ማንም ሰው መገኘት ይችላል፤ እንዲሁም መግቢያ በነፃ ነው። በስብሰባዎቻችን ላይ እንደሚከተሉት ያሉ ትምህርቶችን ታገኛለህ፦

  • አምላክ በግለሰብ ደረጃ ከቁም ነገር ይቆጥርሃል?

  • የሕይወትን ዓላማ ማወቅ የሚቻለው እንዴት ነው?

  • ጠንካራና ዘላቂ ጓደኝነት መመሥረት የሚቻለው እንዴት ነው?

‘እርስ በርስ የሚተሳሰቡ’ እውነተኛ ጓደኞችም ታገኛለህ።—1 ቆሮንቶስ 12:25, 26

ስለ ስብሰባዎቻችን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በስብሰባ አዳራሻችን ውስጥ ምን ይከናወናል? የሚለውን አጭር ቪዲዮ jw.org ላይ ፈልግ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ፕሮግራማችን

ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን መጽሐፍ ተጠቅመን አሳታፊ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በነፃ እንሰጣለን። ይህ መጽሐፍ ቁልፍ ጥቅሶችን፣ ግልጽ ማብራሪያዎችን፣ ውጤታማ ጥያቄዎችን፣ ልብ የሚነኩ ቪዲዮዎችንና ማራኪ ሥዕሎችን ይዟል። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ፕሮግራማችን ሰዎች ለራሳቸው አክብሮት እንዲያዳብሩና ሕይወታቸውን እንዲያሻሽሉ ይረዳቸዋል።

ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትህ የሚጠቅምህ እንዴት እንደሆነ ለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው? የሚለውን አጭር ቪዲዮ jw.org ላይ ፈልግ።

ኢዝሬል ማርቲኔዝ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት

ኢዝሬል ማርቲኔዝ በዝቅተኛ የኑሮና የትምህርት ደረጃው የተነሳ የበታችነት ስሜት ይሰማው ነበር። በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ መገኘቱና መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናቱ ለራሱ አክብሮት እንዲያዳብር የረዳው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ “አሁን በራሴ አላፍርም” የሚለውን ርዕስ jw.org ላይ ፈልግ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ