የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g25 ቁጥር 1 ገጽ 6-9
  • ገንዘብህን በጥበብ ተጠቀም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ገንዘብህን በጥበብ ተጠቀም
  • ንቁ!—2025
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • በአነስተኛ ገቢ መኖር የምትችለው እንዴት ነው?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • 2 | መተዳደሪያህ
    ንቁ!—2022
  • አባካኝ ከመሆን መቆጠብ የምችለው እንዴት ነው?
    ንቁ!—2006
  • ገንዘብህን በአግባቡ መጠቀም የምትችለው እንዴት ነው?
    ንቁ!—2011
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2025
g25 ቁጥር 1 ገጽ 6-9
ምስሎች፦ 1. አንድ ባልና ሚስት የምግብ ጠረጴዛቸው ጋ ሆነው ስለ ወጪና ገቢያቸው ይወያያሉ፤ ልጃቸው በአቅራቢያቸው ባለው ኩሽና ውስጥ ነች። 2. የካልኩሌተር አፕሊኬሽን የተከፈተበት ስልክ በክፍያ መጠየቂያዎች እና በደረሰኞች ላይ ተቀምጧል።

የኑሮ ውድነትን መቋቋም

ገንዘብህን በጥበብ ተጠቀም

የዋጋ ንረት ለሁላችንም ተፈታታኝ ነው። ሆኖም ሁኔታው ሙሉ በሙሉ ከቁጥጥርህ ውጭ እንደሆነ ሊሰማህ አይገባም። ሁኔታህን ለማሻሻል ማድረግ የምትችላቸው ነገሮች አሉ።

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ገንዘብህን በአግባቡ ለመጠቀም ጥረት ካላደረግህ ያለህበት ሁኔታ እየተባባሰ ሊሄድ ይችላል፤ ይህም ጭንቀትና ስጋት ይጨምርብሃል። ገቢህ የተወሰነ ቢሆንም እንኳ ገንዘብህን አብቃቅተህ ለመኖር ማድረግ የምትችላቸው የተለያዩ ነገሮች አሉ።

ምን ማድረግ ትችላለህ?

እንደ አቅምህ ኑር። ይህን ማድረግህ የገንዘብ ሁኔታህ በመጠኑም ቢሆን በቁጥጥርህ ሥር እንደሆነ እንዲሰማህ ያደርጋል፤ ያልተጠበቁ ወጪዎች ቢያጋጥሙህም ያን ያህል አትሰጋም።

እንደ አቅምህ ለመኖር እንዲያግዝህ በጀት አውጣ፤ በጀቱ ላይ ገቢና ወጪዎችህን አስፍር። በጀትህን ስትገመግም የግድ የሚያስፈልጉህን ነገሮች በጥንቃቄ ለይ። ከዚያም ያወጣኸውን በጀት በጥብቅ ለመከተል ጥረት አድርግ። ገቢህ ወይም የሸቀጦች ዋጋ ሲቀየር በጀትህ ላይ አስፈላጊውን ማስተካከያ አድርግ። ያገባህ ከሆንክ ማንኛውንም ውሳኔ ስታደርግ ከባለቤትህ ጋር ተማከር።

እንዲህ ለማድረግ ሞክር፦ በዱቤ ከመግዛት ይልቅ ከተቻለ በጥሬ ገንዘብ ክፈል። አንዳንዶች እንዲህ ማድረጋቸው በጀታቸውን መከተል ቀላል እንዲሆንላቸው አድርጓል፤ ብሎም ዕዳ ውስጥ ከመግባት ጠብቋቸዋል። በተጨማሪም የባንክ ሒሳብ መግለጫህን ለመገምገም ጊዜ መድብ። ምን ያህል ገንዘብ እንዳለህ ማወቅህ ጭንቀትህን ሊቀንስልህ ይችላል።

እንደ አቅምህ መኖር ከባድ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ተግባራዊ ሊሆን የሚችልና በደንብ የታሰበበት በጀት ማውጣትህ ትልቅ እገዛ ያደርግልሃል። ደግሞም ሁኔታው በመጠኑም ቢሆን በቁጥጥርህ ሥር እንደሆነ እንዲሰማህ ያደርጋል።

‘ወጪውን አስላ።’—ሉቃስ 14:28


የገቢ ምንጭህን ላለማጣት የምትችለውን አድርግ። ሥራህን ላለማጣት የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ፦ ሰዓት አክባሪ ሁን። ለሥራህ አዎንታዊ አመለካከት ይኑርህ። ተነሳሽነት ይኑርህ እንዲሁም ጠንክረህ ሥራ። ሰው አክባሪ ሁን። መመሪያዎችን ተከትለህ ለመሥራትና ክህሎትህን ለማሻሻል ጥረት አድርግ።


ገንዘብህን አታባክን። ‘ውድ ነገሮች ላይ ገንዘብ የማጥፋት እንዲሁም የአባካኝነት ልማድ አለኝ?’ እያልክ ራስህን ጠይቅ። ለምሳሌ ብዙ ሰዎች ለፍተው ያገኙትን ገንዘብ ዕፅ በመውሰድ፣ በቁማር፣ በማጨስ ወይም ከልክ በላይ በመጠጣት ያጠፉታል። እነዚህ ልማዶች ከጤንነታቸውና ከሥራቸው አንጻርም ዋጋ ሊያስከፍሏቸው ይችላሉ።

“ጥበብን የሚያገኝ . . . ደስተኛ ነው፤ ጥበብን ማግኘት ብርን ከማግኘት የተሻለ ነው።”—ምሳሌ 3:13, 14


ለክፉ ጊዜ የሚሆን ገንዘብ አስቀምጥ። የምትችል ከሆነ ላልተጠበቁ ወይም ለድንገተኛ ወጪዎች በትንሽ በትንሹ ገንዘብ አስቀምጥ። አንተ ወይም አንድ የቤተሰብህ አባል በድንገት ብትታመሙ፣ ሥራህን ብታጣ ወይም ሌላ ያልተጠበቀ ሁኔታ ቢያጋጥምህ እንዲህ ያለው ተቀማጭ በመጠኑም ቢሆን ዋስትና ይሆንሃል።

‘ሁላችንም መጥፎ ጊዜና ያልተጠበቁ ክስተቶች ያጋጥሙናል።’—መክብብ 9:11

ገንዘብ ለመቆጠብ የሚረዱ ሐሳቦች

ሳንቲሞች የተጠራቀሙበት ጠርሙስ።

ምግብህን ቤትህ ለማዘጋጀት ጥረት አድርግ።

አዘውትሮ ውጭ መመገብ ወይም የተዘጋጁ ምግቦችና መጠጦችን መግዛት ብዙ ሊያስወጣህ ይችላል። ቤት ውስጥ ምግብ ማዘጋጀት ጊዜና ጥረት እንደሚጠይቅ የታወቀ ነው፤ የሚቆጥብልህ ገንዘብ ግን የሚናቅ አይደለም። ጥራት ያለው ምግብ ለመመገብም ያስችልሃል።

በብልሃት ሸምት።

  • የአስቤዛህን ዝርዝር አዘጋጅ፤ እንዲሁም በዚያው መሠረት ሸምት። ከዕቅድህ ውጭ አትሸምት።

  • በጀትህ የሚፈቅድልህ ከሆነ አንዳንድ ነገሮችን በብዛት በመግዛት ቅናሽ ለማግኘት ሞክር። ሆኖም ሊበላሹ የሚችሉ ነገሮችን ማስቀመጥ የምትችልበት ቦታ መኖሩን አረጋግጥ።

  • ምክንያታዊ በሆነ ደረጃ ጥራቱን የጠበቀ እስከሆነ ድረስ ቅናሽ ከሚገኝባቸው ሱቆች ለመግዛት ሞክር።

  • በምትኖርበት አካባቢ ኢንተርኔት ላይ መሸመት ይቻላል? ኢንተርኔት ላይ መሸመትህ የዋጋ ቅናሽ ሊያስገኝልህ፣ በአካል መሄድ ከሚያስከትላቸው ያልታቀዱ ግዢዎች ሊያድንህ እንዲሁም ወጪዎችህን ለመቆጣጠር ሊረዳህ ይችላል።

  • የቅናሽ ማስታወቂያዎችን ተከታተል፤ አካባቢህ ላይ የሚሠራበት ከሆነ ኩፖኖችንም ተጠቀም። ዋጋዎችን አወዳድር፤ ይህም ለአካባቢህ የሚሠራ ከሆነ ለኤሌክትሪክና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚከፈለውን ዋጋም ይጨምራል።

ዕቃዎችን በአዲስ ሞዴል ለማስቀየር አትቸኩል።

የስልክ ወይም የሌሎች ዕቃዎች አምራቾች በየጊዜው አዳዲስ ሞዴሎችን የሚያወጡት ለትርፋቸው ብለው ነው። ስለዚህ ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ዕቃውን በአዲስ ሞዴል መቀየሬ በእርግጥ ይጠቅመኛል? አሁን ላይ ማስቀየር ያስፈልገኛል? ማስቀየር ቢያስፈልገኝ እንኳ የግድ የቅርቡ ሞዴል መሆን አለበት?’

ዕቃዎችህን ጠግነህ ተጠቀም።

ዕቃዎችህን በአግባቡ የምትይዝ ከሆነ ረዘም ያለ ጊዜ ያገለግሉሃል፤ ሲበላሽብህ ደግሞ ብዙ ወጪ የማያስወጣህ ከሆነ ጠግነህ ተጠቀም። ያገለገሉ ዕቃዎች መግዛትም ገንዘብ ሊቆጥብልህ ይችላል።

የራስህን ምግብ አምርት።

የራስህን ምግብ ለማምረት የሚያስችል ቦታ ማመቻቸት ትችል ይሆን? ይህን ማድረግህ የአስቤዛ ወጪህን ከመቀነስ ባሻገር ለሌሎች የምትሸጠው ወይም የምታጋራው ነገር እንድታገኝ ያስችልሃል።

“የትጉ ሰው ዕቅድ ለስኬት ያበቃዋል።”—ምሳሌ 21:5

የዱቤ ካርዶች።

“የዕቃዎች ዋጋ ምን ላይ እንደደረሰ በየጊዜው እንከታተላለን። በዱቤ ካርድ አጠቃቀም ረገድም ጠንቃቆች ነን።”—ማይልዝ፣ እንግሊዝ

ማስታወሻ ደብተር፣ እስክሪብቶ እና የመኪና ቁልፎች።

“እኔና ቤተሰቤ አስቤዛችንን ከመግዛታችን በፊት፣ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ዝርዝር እናዘጋጃለን።”—ጀረሚ፣ ዩናይትድ ስቴትስ

የቀን መቁጠሪያ ያለው ማስታወሻ ደብተርና ካልኩሌተር።

“እንደ ገበያው ሁኔታ የቤተሰባችንን በጀት በየጊዜው እናስተካክላለን፤ ላልታሰቡ ወጪዎችም የተወሰነ ገንዘብ እናስቀምጣለን።”—ያኤል፣ እስራኤል

ተስተካካይ ኪያቬ መፍቻ እና የብሎን መፍቻ።

“ዕቃ ሲበላሽ አዲስ ከመግዛት ይልቅ ጠግነው መጠቀም እንዲችሉ ልጆቻችንን አስተምረናቸዋል። ይህም መኪናችንን እና የቤት ዕቃዎቻችንን ያጠቃልላል። በተጨማሪም እኔና ባለቤቴ፣ አዲስ ወጣ የተባለውን ሞዴል ሁሉ ከመግዛት እንቆጠባለን።”—ጄፍሪ፣ ዩናይትድ ስቴትስ

“ጓሮዬን በማልማትና ዶሮ በማርባት ወጪዎቼን ለመቀነስ እሞክራለሁ። በዚህም የተነሳ ራሴ ያለማሁትን አትክልት ለሌሎች ማጋራትም ችያለሁ።”—ሆኖ፣ ምያንማር

ከአትክልት ቦታው የተለያዩ አትክልቶችን የሚሰበስብ ሰው።
    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ