የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • hf ክፍል 3 ገጽ 9-11
  • ችግሮችን መፍታት የሚቻለው እንዴት ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ችግሮችን መፍታት የሚቻለው እንዴት ነው?
  • ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • 1 ችግሩን ተወያዩበት
  • 2 አዳምጡ እንዲሁም አስተውሉ
  • 3 ውሳኔያችሁን ተግባራዊ አድርጉ
  • ችግሮችን መፍታት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የትዳር ጓደኛችሁን በአክብሮት መያዝ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • አንዳችሁ ለሌላው ታማኝ ሁኑ
    ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
  • ትዳራችሁ አስደሳች እንዲሆን የአምላክን መመሪያ ተከተሉ
    ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
ለተጨማሪ መረጃ
ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
hf ክፍል 3 ገጽ 9-11
ባል ሚስቱ ስሜቷን አውጥታ ስትናገር በትኩረት ሲያዳምጣት

ክፍል 3

ችግሮችን መፍታት የሚቻለው እንዴት ነው?

“ከሁሉም በላይ አንዳችሁ ለሌላው የጠለቀ ፍቅር ይኑራችሁ፤ ምክንያቱም ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናል።”—1 ጴጥሮስ 4:8

ከትዳር ጓደኛችሁ ጋር አብራችሁ መኖር ስትጀምሩ የተለያዩ ችግሮች ያጋጥሟችኋል። ይህ የሚሆነው የሁለታችሁ አስተሳሰብ፣ ስሜትና ስለ ሕይወት ያላችሁ አመለካከት ስለሚለያይ ሊሆን ይችላል። አለዚያም ለችግሮቹ ምክንያት የሚሆኑት ሌሎች ነገሮች ወይም ያልተጠበቁ ክስተቶች ይሆናሉ።

ችግሮች ሲያጋጥሙ እውነታውን ለመሸሽ እንፈተን ይሆናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ የሚመክረን ግን ችግሮቻችንን ተጋፍጠን እንድንፈታቸው ነው። (ማቴዎስ 5:23, 24) የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያዎች በሥራ ላይ ብታውሉ ለችግሮቻችሁ የተሻሉ መፍትሔዎች ታገኛላችሁ።

1 ችግሩን ተወያዩበት

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? ‘ለመናገር ጊዜ አለው።’ (መክብብ 3:1, 7) ስለተፈጠረው ችግር ጊዜ ወስዳችሁ ተነጋገሩ። ስለ ጉዳዩ ምን እንደሚሰማችሁና ምን እንደምታስቡ ለትዳር ጓደኛችሁ በሐቀኝነት አሳውቁ። ከትዳር ጓደኛችሁ ጋር ምንጊዜም “እውነትን ተነጋገሩ።” (ኤፌሶን 4:25) ስሜታችሁን መቆጣጠር ከባድ በሚሆንባችሁ ጊዜም እንኳ ከትዳር ጓደኛችሁ ጋር ጭቅጭቅ ውስጥ ላለመግባት ጥረት አድርጉ። በተረጋጋ መንፈስ መልስ መስጠት፣ ቀላል የሆነው ጉዳይ ተጋግሎ ወደ ጠብ እንዳያመራ ያደርጋል።—ምሳሌ 15:4፤ 26:20

በውይይቱ ላይ የሐሳብ ልዩነት በሚኖራችሁ ጊዜም ጭምር አነጋገራችሁ ደግነት የሚንጸባረቅበት ይሁን፤ ለትዳር ጓደኛችሁ ፍቅርና አክብሮት ማሳየት እንዳለባችሁ ፈጽሞ አትርሱ። (ቆላስይስ 4:6) ችግሩን በተቻለ ፍጥነት ለመፍታት ጥረት አድርጉ፤ ደግሞም አትኮራረፉ።—ኤፌሶን 4:26

ባልና ሚስት ለአንድ ችግር መፍትሔ ለማግኘት ሲወያዩ

ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • በችግሩ ላይ ለመወያየት ተስማሚ የሆነ ጊዜ መድቡ

  • የትዳር ጓደኛህ ስትናገር ሳታቋርጣት አዳምጥ። አንተም ተራህ ሲደርስ ትናገራለህ

2 አዳምጡ እንዲሁም አስተውሉ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ። አንዳችሁ ሌላውን ለማክበር ቀዳሚ ሁኑ።” (ሮም 12:10) የምታዳምጡበት መንገድ ትልቅ ልዩነት ያመጣል። የትዳር ጓደኛችሁን አመለካከት ለመረዳት ጣሩ፤ ይህን ለማድረግም “የሌላውን ስሜት የምትረዱ ሁኑ፣ . . . [እንዲሁም] ትሑታን ሁኑ” የሚለውን ምክር በተግባር አውሉ። (1 ጴጥሮስ 3:8፤ ያዕቆብ 1:19) የምታዳምጡ ለመምሰል አትሞክሩ። ለትዳር ጓደኛችሁ ሙሉ ትኩረት ለመስጠት እንዲያመቻችሁ የሚቻል ከሆነ የምትሠሩትን ነገር አቋርጡ፤ አለዚያም ጉዳዩን ሌላ ጊዜ ልትወያዩበት ትችሉ እንደሆነ ሐሳብ አቅርቡ። የትዳር ጓደኛችሁን እንደ ጠላት ሳይሆን እንደ አጋር አድርጋችሁ የምትመለከቱ ከሆነ ‘ለቁጣ አትቸኩሉም።’—መክብብ 7:9

ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • የትዳር ጓደኛህ የምትናገረው ነገር ባያስደስትህም እንኳ አእምሮህን ክፍት አድርገህ አዳምጣት

  • ባለቤትህ ከምትናገረው ነገር በስተጀርባ ያለውን መልእክት ለመረዳት ሞክር። የትዳር ጓደኛህ የምትጠቀምባቸውን አካላዊ መግለጫዎችና የድምፅዋን ቃና ልብ በል

3 ውሳኔያችሁን ተግባራዊ አድርጉ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “በትጋት ያከናወኑት ነገር ሁሉ ጥቅም ያስገኛል፤ እንዲሁ ማውራት ግን ችግር ላይ ይጥላል።” (ምሳሌ 14:23) ስለ ችግሩ ተወያይታችሁ ጥሩ መፍትሔ ላይ መድረሳችሁ ብቻውን በቂ አይደለም። ሁለታችሁም የወሰናችሁትን ነገር ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋችኋል። ይህም ልፋትና ብዙ ጥረት የሚጠይቅ ቢሆንም አያስቆጭም። (ምሳሌ 10:4) ተባብራችሁ በጋራ የምትሠሩ ከሆነ ለልፋታችሁ “ጥሩ ውጤት” ታገኛላችሁ።—መክብብ 4:9

ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • ችግራችሁን ለመፍታት እያንዳንዳችሁ ምን እርምጃዎችን እንደምትወስዱ ወስኑ

  • ያደረጋችሁትን መሻሻል በየጊዜው ገምግሙ

ችግሮችን ተባብራችሁ ፍቱ

ተባብራችሁ የምትሠሩ ከሆነ ትዳራችሁ ችግርና ምሬት የሞላበት ሳይሆን ደስታ የሰፈነበትና ጠንካራ ይሆናል። (ምሳሌ 24:3) ያለፉ ችግሮችን ደጋግማችሁ ከማንሳት ይልቅ ወደፊት ተመልከቱ። (ምሳሌ 17:9) እርስ በርስ ስትተባበሩና የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያዎች ተግባራዊ ስታደርጉ ማንኛውንም ችግር መወጣት ትችላላችሁ።

ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦

  • ከትዳር ጓደኛዬ ጋር ልወያይበት የምፈልገው በጣም አስቸኳይ ችግር ምንድን ነው?

  • የትዳር ጓደኛዬ ስለ አንድ ችግር ምን እንደሚሰማት በትክክል ለመረዳት ምን ማድረግ እችላለሁ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ