የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • hf ክፍል 6 ገጽ 18-21
  • ልጅ መውለድ በትዳር ውስጥ የሚያመጣው ለውጥ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ልጅ መውለድ በትዳር ውስጥ የሚያመጣው ለውጥ
  • ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • 1 ልጅ መውለድ ሕይወታችሁን እንደሚለውጠው ተገንዘቡ
  • 2 ግንኙነታችሁን አጠናክሩ
  • 3 ሕፃን ልጃችሁን ማሠልጠን
  • ልጅ መውለድ በትዳር ላይ የሚያመጣው ለውጥ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ሕፃናት የሚያስፈልጋቸውና የሚፈልጉት
    ንቁ!—2004
  • ለልጆች የሚያስፈልጋቸውን ነገር ማሟላት
    ንቁ!—2004
  • ወደ ቀዝቃዛው ዓለም ሲመጡ!
    ንቁ!—2004
ለተጨማሪ መረጃ
ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
hf ክፍል 6 ገጽ 18-21
አንዲት ነርስ አራስ ልጃቸውን ለወላጆቹ ስትሰጥ

ክፍል 6

ልጅ መውለድ በትዳር ውስጥ የሚያመጣው ለውጥ

‘ልጆች የይሖዋ ስጦታ ናቸው።’—መዝሙር 127:3

አንድ ባልና ሚስት ልጅ ሲወልዱ በአንድ በኩል ደስታ በሌላ በኩል ደግሞ ጭንቀት ሊሰማቸው ይችላል። አዲስ ወላጆች እንደመሆናችሁ መጠን አብዛኛውን ጊዜያችሁንና ጉልበታችሁን የምታውሉት ልጃችሁን ለመንከባከብ እንደሆነ ስትገነዘቡ ትገረሙ ይሆናል። በቂ እንቅልፍ አለማግኘታችሁ፣ ስሜታችሁ ከመለዋወጡ ጋር ተዳምሮ በግንኙነታችሁ ላይ ጫና ሊፈጥር ይችላል። ልጃችሁን ለመንከባከብና በትዳራችሁ ደስተኛ ሆናችሁ ለመቀጠል ሁለታችሁም ማስተካከያዎች ማድረግ አለባችሁ። ታዲያ የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር እነዚህን ተፈታታኝ ሁኔታዎች እንድትወጡ ሊረዳችሁ የሚችለው እንዴት ነው?

1 ልጅ መውለድ ሕይወታችሁን እንደሚለውጠው ተገንዘቡ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው። . . . የራሱን ፍላጎት አያስቀድምም፣ በቀላሉ አይበሳጭም።” (1 ቆሮንቶስ 13:4, 5) አዲስ እናት በመሆንሽ ትኩረትሽ ሁሉ የሚያርፈው በሕፃን ልጅሽ ላይ ቢሆን የሚገርም አይሆንም። ይሁን እንጂ ባልሽ ችላ እንደተባለ ሊሰማው ስለሚችል ለእሱም ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግሽ አትርሺ። ታጋሽና ደግ በመሆን፣ እሱንም እንደምትፈልጊውና ልጃችሁን በመንከባከብ ረገድ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚችል እንዲሰማው ማድረግ ትችያለሽ።

አባት ልጁን ሲመግብ እንዲሁም ሌሊት ላይ ሲንከባከበው

“እናንተ ባሎች ከእነሱ ጋር በእውቀት አብራችሁ ኑሩ።” (1 ጴጥሮስ 3:7) ሚስትህ አብዛኛውን ጉልበቷን ልጃችሁን ለመንከባከብ እንደምታውል መረዳት ያስፈልግሃል። አሁን አዳዲስ ኃላፊነቶች ስላሉባት ውጥረት ይበዛባት፣ በድካም ትዝል አልፎ ተርፎም በጭንቀት ትዋጥ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ በአንተም ልትበሳጭ ትችላለች፤ አንተ ግን ‘ቶሎ የማይቆጣ ሰው ከኃያል ሰው እንደሚሻል’ በማስታወስ ለመረጋጋት ሞክር። (ምሳሌ 16:32) በዚህ ጊዜ አስተዋይ በመሆን የሚያስፈልጋትን ድጋፍ ስጣት።—ምሳሌ 14:29

ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • አባት፦ ሌሊትም ጭምር ሕፃኑን በመንከባከብ ሚስትህን አግዛት። ከሚስትህና ከሕፃን ልጅህ ጋር የበለጠ ጊዜ ማሳለፍ እንድትችል ለሌሎች እንቅስቃሴዎች የምታውለውን ጊዜ ቀንስ

  • እናት፦ ባለቤትሽ ሕፃኑን በመንከባከብ ረገድ እንዲረዳሽ ፍቀጅለት። ሥራውን ጥሩ አድርጎ ባይሠራ እንኳ እንዴት መሥራት እንዳለበት በደግነት አሳዪው እንጂ አትንቀፊው

2 ግንኙነታችሁን አጠናክሩ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።” (ዘፍጥረት 2:24) አዲስ የቤተሰብ አባል ብታገኙም አንተና የትዳር ጓደኛህ አሁንም “አንድ ሥጋ” መሆናችሁን አስታውስ። ግንኙነታችሁ ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል የቻላችሁትን ሁሉ ጥረት አድርጉ።

ሚስት ከሆንሽ ባልሽ ለሚያደርግልሽ እርዳታና ድጋፍ አመስጋኝ ሁኚ። ለባልሽ አድናቆትሽን መግለጽሽ “ፈውስ” ሊሆንለት ይችላል። (ምሳሌ 12:18) ባል ከሆንክ ደግሞ ሚስትህን ምን ያህል እንደምትወዳትና ከፍ አድርገህ እንደምትመለከታት ንገራት። ቤተሰቡን የምትንከባከብበትን መንገድ እንደምታደንቅ ግለጽላት።—ምሳሌ 31:10, 28

“እያንዳንዱ ሰው ምንጊዜም የራሱን ጥቅም ሳይሆን የሌላውን ሰው ጥቅም ይፈልግ።” (1 ቆሮንቶስ 10:24) ምንጊዜም ለትዳር ጓደኛችሁ የሚበጀውን ነገር አድርጉ። ባልና ሚስት እንደመሆናችሁ መጠን ለማውራት እንዲሁም አንዳችሁ ሌላውን ለማመስገንና ለማዳመጥ ጊዜ መድቡ። በፆታ ግንኙነት ረገድም ራስ ወዳድ አትሁኑ። የትዳር ጓደኛችሁን ፍላጎት ከግምት አስገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ “አንዳችሁ ለሌላው የሚገባውን አትከልክሉ” ይላል። (1 ቆሮንቶስ 7:3-5) ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ በሐቀኝነት ተወያዩ። ታጋሽና አስተዋይ መሆናችሁ ግንኙነታችሁ እንዲጠናከር ይረዳል።

ባልና ሚስት ልጃቸው ሲተኛ አብረው ሲጫወቱ

ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • ሁለታችሁ ብቻ አብራችሁ የምትሆኑበት ጊዜ መድቡ

  • የትዳር ጓደኛህ እንደምትወዳት እንዲሰማት የሚያደርጉ ነገሮችን ለምሳሌ አጭር መልእክት እንደ መላክ ወይም አነስተኛ ስጦታ እንደ መስጠት የመሳሰሉ ትናንሽ ነገሮችን አድርግ

3 ሕፃን ልጃችሁን ማሠልጠን

አንዲት ነርስ አራስ ልጃቸውን ለወላጆቹ ስትሰጥ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ለመዳን የሚያበቃ ጥበብ እንድታገኝ የሚያስችሉህን ቅዱሳን መጻሕፍት ከጨቅላነትህ ጀምሮ አውቀሃል።” (2 ጢሞቴዎስ 3:15) ሕፃኑን እንዴት እንደምታስተምሩት ዕቅድ አውጡ። ልጃችሁ ከመወለዱ በፊትም እንኳ አስገራሚ የሆነ የመማር ችሎታ አለው። ሕፃኑ በማህፀን ውስጥ እያለም ድምፃችሁን ለይቶ ሊያውቅ እንዲሁም የስሜታችሁ መለዋወጥ ተጽዕኖ ሊያሳድርበት ይችላል። ከጨቅላነቱ ጀምራችሁ አንብቡለት። የምታነቡለትን ነገር አሁን ማስተዋል ባይችልም እንዲህ ማድረጋችሁ ሲያድግ ማንበብ እንዲወድድ ሊረዳው ይችላል።

ለሕፃን ልጃችሁ ስለ አምላክ ለመናገር ዕድሜው ገና እንደሆነ ሊሰማችሁ አይገባም። ወደ ይሖዋ ስትጸልዩ ይስማችሁ። (ዘዳግም 11:19) ስታጫውቱትም ጭምር አምላክ ስለሠራቸው ነገሮች አውሩለት። (መዝሙር 78:3, 4) ልጃችሁ እያደገ ሲሄድ ይሖዋን እንደምትወዱ ሊያስተውልና እሱም ይሖዋን ሊወድድ ይችላል።

ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • ሕፃን ልጃችሁን ለማሠልጠን የሚያስፈልጋችሁን ጥበብ እንዲሰጣችሁ ወደ ይሖዋ ጸልዩ

  • ሕፃኑ እንዲያውቅ የምትፈልጓቸውን ቃላትና ሐሳቦች ገና ትንሽ እያለም ደጋግሙለት

ልጅ መውለድ ትዳራችሁን ሊያጠናክረው ይችላል

ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ሁለታችሁም የወላጅነት ኃላፊነታችሁን መወጣት ቀላል እየሆነላችሁና በራሳችሁ እየተማመናችሁ ትሄዳላችሁ። ልጅ ማሳደግ ይበልጥ አፍቃሪዎች፣ ታጋሾችና ደጎች እንድትሆኑ ሊረዳችሁ ይችላል። አብራችሁ የምትሠሩና እርስ በርስ የምትደጋገፉ ከሆነ ልጅ መውለዳችሁ ግንኙነታችሁን ይበልጥ ያጠናክረዋል። በመዝሙር 127:3 ላይ የሚገኘው “የማህፀንም ፍሬ ከእሱ የሚገኝ ስጦታ ነው” የሚለው ሐሳብ በሕይወታችሁ ውስጥ ሲፈጸም ታያላችሁ።

ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦

  • ባለቤቴ ለቤተሰቡ ለምታደርገው ነገር አመስጋኝ መሆኔን ለማሳየት ባለፈው ሳምንት ውስጥ ምን አድርጌያለሁ?

  • ከትዳር ጓደኛዬ ጋር ስለ ሕፃን ልጃችን ብቻ በመነጋገር ፋንታ ስለ ራሳችን ያወራነው መቼ ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ