የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • scl ገጽ 56-57
  • ቤተሰብ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቤተሰብ
  • ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት
ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት
scl ገጽ 56-57

ቤተሰብ

የቤተሰብ መሥራች ይሖዋ ነው

ኤፌ 3:14, 15

ወላጆች

“ወላጆች” የሚለውን ተመልከት

አባቶች

“አባቶች” የሚለውን ተመልከት

እናቶች

“እናቶች” የሚለውን ተመልከት

ባሎች፣ ሚስቶች

“ትዳር” የሚለውን ተመልከት

ወንዶች እና ሴቶች ልጆች

በቤተሰብ ውስጥ ልጆች ምን ይጠበቅባቸዋል?

ዘሌ 19:3፤ ምሳሌ 1:8፤ 6:20፤ ኤፌ 6:1

በተጨማሪም ምሳሌ 4:1⁠ን ተመልከት

ልጆች ወላጆቻቸውን መታዘዝ ያለባቸው ለምንድን ነው?

ኤፌ 6:1-3፤ ቆላ 3:20

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • መዝ 78:1-8—እስራኤላውያን የቀድሞ አባቶቻቸውን ተግባር ለልጆቻቸው ይተርኩላቸው ነበር፤ ይህን የሚያደርጉት ልጆቻቸው በአምላክ እንዲታመኑና ታዛዦች እንዲሆኑ ነበር

    • ሉቃስ 2:51, 52—ፍጹም የሆነው ኢየሱስ በልጅነቱ ፍጹም ያልሆኑ ወላጆቹን ምንጊዜም ይታዘዛቸው ነበር

ልጆች ወላጆቻቸውን ማክበር ሊከብዳቸው የሚችለው ለምንድን ነው?

ሮም 12:1, 2፤ 2ጢሞ 3:1, 2, 5

አምላክ ዓመፀኛ ልጆችን እንዴት ይመለከታቸዋል?

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘዳ 21:18-21—እልኸኛ፣ ዓመፀኛና ሰካራም የሆነ እንዲሁም የተሰጠውን እርማት ለመቀበል አሻፈረኝ የሚል ልጅ የሞት ቅጣት እንዲበየንበት የሙሴ ሕግ ይደነግጋል

    • 2ነገ 2:23, 24—የተወሰኑ ልጆች በነቢዩ ኤልሳዕ ላይ አፌዙበት፤ አምላክ ለሾመው ሰው እንዲህ ያለ ከፍተኛ ንቀት በማሳየታቸው ሁለት ድቦች ቦጫጨቋቸው

ወላጆች ልጅ የማሳደግ መብታቸውን እንዴት ሊመለከቱት ይገባል?

መዝ 127:3፤ 128:3

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘሌ 26:9—በእስራኤላውያን ዘመን፣ ልጅ መውለድ የይሖዋ በረከት እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠር ነበር

    • ኢዮብ 42:12, 13—ኢዮብ በከባድ መከራ ውስጥ ንጹሕ አቋሙን በመጠበቁ ይሖዋ አሥር ተጨማሪ ልጆች በመስጠት እሱንና ሚስቱን ባርኳቸዋል

ይሖዋ፣ ወንድማማቾችና እህትማማቾች አንዳቸው ሌላውን እንዴት እንዲይዙ ይጠብቅባቸዋል?

መዝ 34:14፤ ምሳሌ 15:23፤ 19:11

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 27:41፤ 33:1-11—ያዕቆብ ለወንድሙ ለኤሳው አክብሮት በማሳየት እርቅ ለመፍጠር ጥረት አድርጓል፤ ኤሳውም ለዚህ ጥረቱ በጎ ምላሽ ሰጥቷል

ለአካለ መጠን የደረሱ ልጆች ለወላጆቻቸውና ለአያቶቻቸው ምን የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው?

ምሳሌ 23:22፤ 1ጢሞ 5:4

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 11:31, 32—አብርሃም ዑርን ለቅቆ ሲወጣ አባቱን ታራን ይዞት ሄዷል፤ እስከሞተበት ጊዜ ድረስም ተንከባክቦታል

    • ማቴ 15:3-6—ኢየሱስ፣ ለአካለ መጠን የደረሱ ልጆች አስፈላጊ ሲሆን ለወላጆቻቸው ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው የሙሴን ሕግ ጠቅሶ ተናግሯል

አማቶች

“አማቶች” የሚለውን ተመልከት

አያቶች

“አያቶች” የሚለውን ተመልከት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ