የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w08 9/15 ገጽ 32
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በልሳናት መናገር
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
  • በልሳን የመናገር ስጦታ የእውነተኛ ክርስትና ክፍል ነውን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • መጽሐፍ ቅዱስ በልሳን ስለ መናገር ምን ይላል?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • በልሳን መናገር ከአምላክ የሚገኝ ስጦታ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
w08 9/15 ገጽ 32

የአንባቢያን ጥያቄዎች

ሐዋርያው ጳውሎስ ለዕብራውያን ክርስቲያኖች በጻፈው ደብዳቤ ላይ “እጆችን ስለ መጫን” ተናግሯል። ጳውሎስ ሽማግሌዎችን ስለ መሾም መግለጹ ነበር ወይስ ስለ ሌላ ነገር መናገሩ?—ዕብ. 6:2

ስለዚህ ጉዳይ ሙሉ በሙሉ እርግጠኞች መሆን ባይቻልም ጳውሎስ እጆችን በመጫን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ስለማስተላለፍ የተናገረ ይመስላል።

እርግጥ ነው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎችን ለቲኦክራሲያዊ ሥራዎች ከመሾም ጋር በተያያዘ እጆችን ስለ መጫን ይናገራል። ሙሴ፣ ኢያሱን የእሱ ተተኪ እንዲሆን ሲሾመው “እጆቹን ጭኖበት ነበር።” (ዘዳ. 34:9) በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ደግሞ ብቃት ያላቸው አንዳንድ ወንድሞች የተሾሙት እጆችን በመጫን ነበር። (ሥራ 6:6፤ 1 ጢሞ. 4:14) ጳውሎስም በአንድ ሰው ላይ እጅ ለመጫን መቸኮል ተገቢ እንዳልሆነ የሚገልጽ ምክር ሰጥቷል።—1 ጢሞ. 5:22

ይሁን እንጂ ጳውሎስ፣ የዕብራውያን ክርስቲያኖችን ‘የመጀመሪያውን ትምህርት’ አልፈው ስለመጡ ‘ወደ ብስለት እንዲሄዱ’ አሳስቧቸዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ‘ከሞተ ሥራ ንስሓ መግባትንና በአምላክ ማመንን እንዲሁም ጥምቀቶችንና እጆችን መጫንን’ ጠቅሷል። (ዕብ. 6:1, 2) ታዲያ ክርስቲያኖች ወደ ብስለት ለመሄድ ሊያልፏቸው ከሚገቡት የመጀመሪያ ትምህርቶች መካከል ሽማግሌዎችን መሾምም ሊካተት ይችላል? በፍጹም አይችልም። የጉባኤ ሽማግሌ የሚሆኑት የበሰሉ ወይም የጎለመሱ ወንድሞች በመሆናቸው ሽማግሌዎችን መሾም እንደ መጀመሪያ ነገር ሊታይ አይችልም።—1 ጢሞ. 3:1

ሆኖም እጆችን መጫን ሌላም ነገር ለማመልከት ተሠርቶበታል። በመጀመሪያው መቶ ዘመን ይሖዋ፣ ሥጋዊ እስራኤላውያንን እንደ ሕዝቡ አድርጎ መመልከቱን በመተው ትኩረቱን ወደ መንፈሳዊ እስራኤል ማለትም ወደ ቅቡዓን ክርስቲያኖች ጉባኤ አዞረ። (ማቴ. 21:43፤ ሥራ 15:14፤ ገላ. 6:16) በልሳን እንደ መናገር ያሉት ተአምራዊ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ይሖዋ ትኩረቱን ወደ መንፈሳዊ እስራኤል እንዳዞረ የሚያሳዩ ማስረጃዎች ነበሩ። (1 ቆሮ. 12:4-11) ቆርኔሌዎስና ቤተሰቡ አማኞች በሆኑበት ወቅት ‘በልሳን መናገር’ መጀመራቸው መንፈስ ቅዱስ እንደወረደባቸው የሚያሳይ ነበር።—ሥራ 10:44-46

አንዳንድ ጊዜ ተአምራዊ ስጦታዎች ወደ ሌሎች ሰዎች የሚተላለፉት እጆችን በመጫን ነበር። ፊልጶስ በሰማርያ ምሥራቹን ከሰበከ በኋላ ብዙ ሰዎች ተጠመቁ። ከዚያም የበላይ አካሉ፣ ሐዋርያው ጴጥሮስንና ሐዋርያው ዮሐንስን ወደ ሰማርያ ላካቸው። የተላኩት ለምን ነበር? ዘገባው “[ሁለቱ ሐዋርያት] እጃቸውን [በቅርቡ በተጠመቁት ሰዎች ላይ] ጫኑባቸው፤ እነርሱም መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ” ይላል። ይህ ሲባል እነዚህ አማኞች የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ማለትም ሌሎች በግልጽ የሚያዩአቸውን ችሎታዎች ተቀብለዋል ማለት ነው። ይህን እንዴት እናውቃለን? ጠንቋይ የነበረው ሲሞን እጆችን በመጫን መንፈስ ቅዱስ ወደ ሰዎች እንደሚተላለፍ ሲመለከት እሱም፣ ለሌሎች ሰዎች መንፈስ ቅዱስን በመስጠት ተአምር መፈጸም እንዲችሉ ለማድረግ ፈለገ፤ በመሆኑም መንፈስ ቅዱስን የመስጠት ችሎታን ከሐዋርያቱ በገንዘብ ለመግዛት ሞከረ። (ሥራ 8:5-20) ቆየት ብሎ በኤፌሶን 12 ሰዎች ተጠመቁ። መጽሐፍ ቅዱስ “ጳውሎስም እጁን በላያቸው በጫነ ጊዜ፣ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው፤ በሌሎች ቋንቋዎች ተናገሩ፤ ትንቢትም ተናገሩ” ይላል።—ሥራ 19:1-7፤ ከ2 ጢሞቴዎስ 1:6 ጋር አወዳድር።

ከዚህ ለማየት እንደምንችለው በዕብራውያን 6:2 ላይ ጳውሎስ እጆችን በመጫን ለአዲስ አማኞች የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ስለማስተላለፍ የተናገረ ይመስላል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ