የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w13 4/15 ገጽ 32
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መሰብሰባችሁን አትተዉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • ሕዝበ ክርስትና የዚህ ዓለም ክፍል ለመሆን የበቃችው እንዴት ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ላይ እምነት ማሳደር ሕይወትን ያድናል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
w13 4/15 ገጽ 32

ይህን ያውቁ ኖሯል?

የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ከ70 ዓ.ም. በኋላ በድጋሚ ተገንብቶ ነበር?

ኢየሱስ የይሖዋ ቤተ መቅደስ የተገነባበት ድንጋይ፣ በድንጋይ ላይ እንደተካበ እንደማይቀር ተናግሮ የነበረ ሲሆን በቲቶ እየተመራ የመጣው የሮም ሠራዊት በ70 ዓ.ም. ኢየሩሳሌምን በደመሰሳት ጊዜ ይህ ትንቢት ተፈጽሟል። (ማቴ. 24:2) ከጊዜ በኋላ ንጉሠ ነገሥት ጁሊያን ቤተ መቅደሱን በድጋሚ ለመገንባት አቅዶ ነበር።

ጁሊያን የመጨረሻው የሮም አረማዊ ንጉሠ ነገሥት ተብሎ ተጠርቷል። የታላቁ ቆስጠንጢኖስ የወንድም ልጅ የሆነው ይህ ሰው የስመ ክርስትናን ትምህርት ተምሮ ነበር። ሆኖም በ361 ዓ.ም. ንጉሠ ነገሥት ሆኖ ከተሾመ በኋላ ይህን ትምህርትም ሆነ በዘመኑ የነበረውን ብልሹ የሆነ ክርስትና እንደማይፈልግና አረማዊነትን እንደሚመርጥ በይፋ ገለጸ። የታሪክ መጻሕፍት “ከሃዲው” በማለት ይጠቅሱታል።

ጁሊያን ክርስትናን በጣም ይጠላ ነበር። ለዚህ አንዱ ምክንያት ገና የስድስት ዓመት ልጅ ሳለ ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰዎች አባቱንና ዘመዶቹን ሲገድሉ ስለተመለከተ ሊሆን ይችላል። የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች እንደሚናገሩት ከሆነ ጁሊያን አይሁዶች ቤተ መቅደሳቸውን መልሰው እንዲገነቡ አበረታቷቸው ነበር፤ ይህን ያደረገው የቤተ መቅደሱ መገንባት ኢየሱስ ሐሰተኛ ነቢይ እንደነበረ ሊያረጋግጥ ይችላል የሚል እምነት ስለነበረው ነው።a

ጁሊያን ቤተ መቅደሱን መልሶ ለመገንባት አቅዶ የነበረ መሆኑ ፈጽሞ አያጠራጥርም። የታሪክ ምሁራንን የሚያከራክረው ጉዳይ የግንባታ ሥራውን ጀምሮ የነበረ መሆን አለመሆኑና ተጀምሮ ከነበረ ደግሞ ሥራው የተቋረጠው በምን ምክንያት እንደሆነ ነው። ይሁን እንጂ አንድ በእርግጠኝነት የሚታወቅ ነገር አለ፦ ጁሊያን ሥልጣን ከያዘ በኋላ ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ስለተገደለ ቤተ መቅደሱን የመገንባት ውጥኑም አብሮት ሞቷል።

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በኢየሱስ ዘመን የነበረው ቤተ መቅደስ በዛሬው ጊዜ ባለችው የኢየሩሳሌም ከተማ ላይ በቀድሞ ቦታው ተቀምጦ ሲታይ

a ኢየሱስ ቤተ መቅደሱ ይጠፋል አለ እንጂ መልሶ አይገነባም አላለም፤ በዚህ ትንቢት መሠረት ቤተ መቅደሱ በ70 ዓ.ም. ወድሟል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ