የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w24 የካቲት ገጽ 31
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ቅዱስ መሆን ያለብን ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ‘ትልቁን የእምነት ጋሻህን’ እያጠናከርከው ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • ሕይወትንና ደምን እንደ ቅዱስ ነገር አድርገህ ትይዛቸዋለህን?
    እውነተኛው አንድ አምላክ ያስገኘው የአምልኮ አንድነት
  • ለሕይወት የአምላክ ዓይነት አመለካከት አለህ?
    ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
w24 የካቲት ገጽ 31
ዕዝራ ጥቅልል ይዞ በሕዝቡ ፊት ይሖዋን ሲያወድስ።

ይህን ያውቁ ኖሯል?

መጽሐፍ ቅዱስ አንዳንድ ሐሳቦችን የሚደጋግመው ለምንድን ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች አንዳንድ ሐረጎችን ቃል በቃል የደጋገሙባቸው ጊዜያት አሉ። ለዚህ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ሦስት ነገሮችን እስቲ እንመልከት።

የተጻፈበት ዘመን። በጥንቷ እስራኤል አብዛኞቹ ሰዎች የሕጉ የግል ቅጂ አልነበራቸውም። ሕጉ ሲነበብ በዋነኝነት የሚሰሙት ብሔሩ በሙሉ በማደሪያ ድንኳኑ በሚሰበሰብበት ወቅት ነበር። (ዘዳ. 31:10-12) በዚያ ሁሉ ሕዝብ መሃል ለበርካታ ሰዓታት ቆመው ሲያዳምጡ ትኩረታቸውን የሚከፋፍሉባቸው ነገሮች እንደሚኖሩ ምንም ጥያቄ የለውም። (ነህ. 8:2, 3, 7) እንዲህ ባሉት ጊዜያት ቁልፍ ሐረጎች መደጋገማቸው ሕዝቡ ትምህርቱን እንዲያስታውሱና በሥራ ላይ እንዲያውሉት ይረዳቸዋል። አንዳንድ ቃላት መደጋገማቸው በተለይ በሕጉ ውስጥ ያሉትን ዝርዝር ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች እንዲያስታውሱ ይረዳቸዋል።—ዘሌ. 18:4-22፤ ዘዳ. 5:1

የተጻፈበት መንገድ። አሥር በመቶ ገደማ የሚሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የተጻፈው በመዝሙር መልክ ነው፤ ይህም የመዝሙር መጽሐፍን፣ መኃልየ መኃልይን እንዲሁም ሰቆቃወ ኤርምያስን ያካትታል። አንዳንድ ጊዜ መዝሙሮች ተደጋጋሚ ሐረጎች ይኖሯቸዋል። ይህም የመዝሙሩን ጭብጥ ለማጉላትና አድማጮች ቃላቱን እንዲያስታውሷቸው ለመርዳት ያገለግላል። ለምሳሌ ያህል በመዝሙር 115:9-11 ላይ ያሉትን ቃላት ልብ በል፦ “እስራኤል ሆይ፣ በይሖዋ ታመኑ፤ እሱ ረዳታቸውና ጋሻቸው ነው። የአሮን ቤት ሆይ፣ በይሖዋ ታመኑ፤ እሱ ረዳታቸውና ጋሻቸው ነው። እናንተ ይሖዋን የምትፈሩ፣ በይሖዋ ታመኑ፤ እሱ ረዳታቸውና ጋሻቸው ነው።” እነዚህ ቃላት መደጋገማቸው ወሳኝ እውነቶችን በዘማሪዎቹ ልብና አእምሮ ውስጥ ለመቅረጽ እንደሚረዳ አይሰማህም?

የተጻፈበት ምክንያት። የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች አንዳንድ ጊዜ ወሳኝ ሐረጎችን ይደጋግሙ ነበር። ለምሳሌ ይሖዋ፣ እስራኤላውያን ደም እንዳይበሉ ባዘዘበት ወቅት ሙሴ ምክንያቱን በተደጋጋሚ እንዲነግራቸው አድርጓል። አምላክ የሥጋ ሕይወት ያለው በደሙ ውስጥ እንደሆነ ማለትም ደም ሕይወትን እንደሚወክል ጎላ አድርጎ መግለጽ ፈልጎ ነበር። (ዘሌ. 17:11, 14) ከጊዜ በኋላ ሐዋርያትና በኢየሩሳሌም የነበሩት ሽማግሌዎች አምላክን ከማሳዘን መቆጠብ የሚቻልባቸውን ወሳኝ መንገዶች ሲዘረዝሩ ከደም የመራቅን አስፈላጊነት በድጋሚ ጎላ አድርገው ገልጸዋል።—ሥራ 15:20, 29

ይሖዋ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንዳንድ ሐረጎች በተደጋጋሚ እንዲጠቀሱ ቢያደርግም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳቦችን መደጋገም ሃይማኖታዊ ሥርዓት እንዲሆን አልፈለገም። ለምሳሌ ኢየሱስ “በምትጸልዩበት ጊዜ . . . አንድ ዓይነት ነገር ደጋግማችሁ አታነብንቡ” ብሏል። (ማቴ. 6:7) ከዚያም በጸሎታችን ውስጥ ልናካትታቸው የምንችላቸውን አንዳንድ ተገቢ ርዕሰ ጉዳዮች ጠቀሰ። (ማቴ. 6:9-13) ስለዚህ በምንጸልይበት ወቅት አንዳንድ ቃላትን ደጋግመን ማነብነብ ባይኖርብንም ስለ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ደጋግመን መጸለይ እንችላለን።—ማቴ. 7:7-11

በእርግጥም በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፈው ቃሉ አንዳንድ ቃላትንና ሐረጎችን የሚደጋግም መሆኑ ተገቢ ነው። ታላቁ አስተማሪያችን የሚጠቅመንን ነገር ከሚያስተምርባቸው የተለያዩ መንገዶች አንዱ ይህ ነው።—ኢሳ. 48:17, 18

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ