የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ነገሥት 14
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ነገሥት የመጽሐፉ ይዘት

      • አኪያህ ስለ ኢዮርብዓም የተናገረው ትንቢት (1-20)

      • ሮብዓም በይሁዳ ላይ የነገሠበት ጊዜ (21-31)

        • ሺሻቅ ያካሄደው ወረራ (25, 26)

1 ነገሥት 14:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 11:30, 31

1 ነገሥት 14:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 18:1፤ 1ሳሙ 4:3

1 ነገሥት 14:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አንተም እንዲህ እንዲህ ብለህ ንገራት።”

1 ነገሥት 14:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 11:30, 31፤ 12:20

1 ነገሥት 14:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:16
  • +1ነገ 15:5፤ ሥራ 13:22

1 ነገሥት 14:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቀልጠው የተሠሩ ሐውልቶችን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 27:15፤ 2ዜና 11:15
  • +ነህ 9:26፤ መዝ 50:17

1 ነገሥት 14:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ግንብ ላይ የሚሸናውን።” ወንዶችን የሚያናንቅ የዕብራይስጥ አገላለጽ ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 15:25-29

1 ነገሥት 14:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 15:25-29

1 ነገሥት 14:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ኤፍራጥስን ያመለክታል።

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 8:7-9፤ 29:28፤ ኢያሱ 23:15፤ 2ነገ 17:6
  • +ዘዳ 28:64፤ 2ነገ 15:29፤ 18:11
  • +ዘዳ 12:3

1 ነገሥት 14:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:28-30፤ 13:33, 34

1 ነገሥት 14:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 12:15፤ 13:3

1 ነገሥት 14:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የገዛባቸው ቀናት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 13:20
  • +1ነገ 15:25

1 ነገሥት 14:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:24፤ ዘዳ 12:5, 6፤ 1ነገ 8:16, 17
  • +መዝ 78:68፤ 132:13
  • +1ነገ 11:1፤ 2ዜና 12:13

1 ነገሥት 14:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 11:7፤ 2ዜና 12:1
  • +ኢሳ 65:2

1 ነገሥት 14:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 65:7
  • +ዘዳ 12:2, 3፤ ኢሳ 57:5፤ ኤር 2:20፤ ሆሴዕ 4:13
  • +ዘሌ 26:1

1 ነገሥት 14:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ግብረ ሰዶማውያን ሆነው የሴት ዓይነት ሚና ያላቸውን ወንዶች ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 23:17, 18፤ 1ነገ 15:11, 12፤ 22:46፤ 2ነገ 23:7፤ ሆሴዕ 4:14

1 ነገሥት 14:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 11:40
  • +2ዜና 12:2-4

1 ነገሥት 14:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 7:51፤ 15:18፤ 2ነገ 18:14, 15፤ 24:12, 13
  • +1ነገ 10:16, 17፤ 2ዜና 12:9-11

1 ነገሥት 14:27

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የሯጮቹ።”

1 ነገሥት 14:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 27:24፤ 2ዜና 12:15

1 ነገሥት 14:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 15:6

1 ነገሥት 14:31

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አቢያህ ተብሎም ይጠራል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 11:43
  • +1ነገ 11:1፤ 2ዜና 12:13
  • +1ዜና 3:10፤ ማቴ 1:7

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ነገ. 14:21ነገ 11:30, 31
1 ነገ. 14:4ኢያሱ 18:1፤ 1ሳሙ 4:3
1 ነገ. 14:71ነገ 11:30, 31፤ 12:20
1 ነገ. 14:81ነገ 12:16
1 ነገ. 14:81ነገ 15:5፤ ሥራ 13:22
1 ነገ. 14:9ዘዳ 27:15፤ 2ዜና 11:15
1 ነገ. 14:9ነህ 9:26፤ መዝ 50:17
1 ነገ. 14:101ነገ 15:25-29
1 ነገ. 14:141ነገ 15:25-29
1 ነገ. 14:15ዘዳ 8:7-9፤ 29:28፤ ኢያሱ 23:15፤ 2ነገ 17:6
1 ነገ. 14:15ዘዳ 28:64፤ 2ነገ 15:29፤ 18:11
1 ነገ. 14:15ዘዳ 12:3
1 ነገ. 14:161ነገ 12:28-30፤ 13:33, 34
1 ነገ. 14:192ዜና 12:15፤ 13:3
1 ነገ. 14:202ዜና 13:20
1 ነገ. 14:201ነገ 15:25
1 ነገ. 14:21ዘፀ 20:24፤ ዘዳ 12:5, 6፤ 1ነገ 8:16, 17
1 ነገ. 14:21መዝ 78:68፤ 132:13
1 ነገ. 14:211ነገ 11:1፤ 2ዜና 12:13
1 ነገ. 14:221ነገ 11:7፤ 2ዜና 12:1
1 ነገ. 14:22ኢሳ 65:2
1 ነገ. 14:23ኢሳ 65:7
1 ነገ. 14:23ዘዳ 12:2, 3፤ ኢሳ 57:5፤ ኤር 2:20፤ ሆሴዕ 4:13
1 ነገ. 14:23ዘሌ 26:1
1 ነገ. 14:24ዘዳ 23:17, 18፤ 1ነገ 15:11, 12፤ 22:46፤ 2ነገ 23:7፤ ሆሴዕ 4:14
1 ነገ. 14:251ነገ 11:40
1 ነገ. 14:252ዜና 12:2-4
1 ነገ. 14:261ነገ 7:51፤ 15:18፤ 2ነገ 18:14, 15፤ 24:12, 13
1 ነገ. 14:261ነገ 10:16, 17፤ 2ዜና 12:9-11
1 ነገ. 14:291ዜና 27:24፤ 2ዜና 12:15
1 ነገ. 14:301ነገ 15:6
1 ነገ. 14:311ነገ 11:43
1 ነገ. 14:311ነገ 11:1፤ 2ዜና 12:13
1 ነገ. 14:311ዜና 3:10፤ ማቴ 1:7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ነገሥት 14:1-31

አንደኛ ነገሥት

14 በዚህ ጊዜ የኢዮርብዓም ልጅ አቢያህ ታመመ። 2 በመሆኑም ኢዮርብዓም ሚስቱን እንዲህ አላት፦ “እባክሽ፣ ተነሺና የኢዮርብዓም ሚስት መሆንሽን እንዳያውቁ ራስሽን ለውጠሽ ወደ ሴሎ ሂጂ። ነቢዩ አኪያህ ያለው እዚያ ነው። እኔ በዚህ ሕዝብ ላይ ንጉሥ እንደምሆን የተናገረው እሱ ነው።+ 3 አሥር ዳቦና የተቀቡ ቂጣዎች እንዲሁም አንድ ገንቦ ማር ይዘሽ ወደ እሱ ሂጂ። እሱም በልጁ ላይ የሚደርሰውን ነገር ይነግርሻል።”

4 የኢዮርብዓምም ሚስት እንዳላት አደረገች። ተነስታ ወደ ሴሎ+ በመሄድ ወደ አኪያህ ቤት መጣች። አኪያህ ከማርጀቱ የተነሳ ማየት ተስኖት የነበረ ቢሆንም ዓይኖቹ ፊት ለፊት ትኩር ብለው ይመለከቱ ነበር።

5 ይሖዋ ግን አኪያህን እንዲህ አለው፦ “የኢዮርብዓም ሚስት ልጇ ስለታመመ ስለ እሱ ልትጠይቅህ እየመጣች ነው። እኔም ምን እንደምትላት እነግርሃለሁ።* እሷም እዚህ ስትደርስ ማንነቷ እንዳይታወቅ ራሷን ትለውጣለች።”

6 አኪያህም በሩ ጋ ስትደርስ የእግሯን ኮቴ ሰምቶ እንዲህ አላት፦ “የኢዮርብዓም ሚስት ግቢ። ማንነትሽ እንዳይታወቅ ራስሽን የለወጥሽው ለምንድን ነው? መጥፎ ዜና እንድነግርሽ ታዝዣለሁ። 7 ሂጂና ኢዮርብዓምን እንዲህ በዪው፦ ‘የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን ከሕዝብህ መካከል አስነሳሁህ።+ 8 ከዚያም መንግሥቱን ከዳዊት ቤት ላይ ቀድጄ ለአንተ ሰጠሁህ።+ አንተ ግን በፊቴ ትክክል የሆነውን ነገር ብቻ በማድረግ ትእዛዛቴን እንደጠበቀውና በሙሉ ልቡ እንደተከተለኝ እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት አልሆንክም።+ 9 ከዚህ ይልቅ ከአንተ በፊት ከነበሩት ሁሉ የከፋ ድርጊት ፈጸምክ፤ እኔንም ለማስቆጣት ለራስህ ሌላ አምላክና ከብረት የተሠሩ ምስሎችን* ሠራህ፤+ ጀርባህንም ሰጠኸኝ።+ 10 በዚህም የተነሳ በኢዮርብዓም ቤት ላይ ጥፋት አመጣለሁ፤ በእስራኤል ውስጥ የሚገኘውን ምስኪኑንና ደካማውን ጨምሮ የኢዮርብዓም የሆነውን ወንድ* ሁሉ ጠራርጌ አጠፋለሁ፤ አንድ ሰው ፋንድያን ሙልጭ አድርጎ በመጥረግ እንደሚያስወግድ ሁሉ እኔም የኢዮርብዓምን ቤት ሙልጭ አድርጌ እጠርጋለሁ!+ 11 ከኢዮርብዓም ወገን የሆነውን በከተማ ውስጥ የሚሞተውን ሁሉ ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳ ላይ የሚሞተውን ደግሞ የሰማይ አሞሮች ይበሉታል፤ ይሖዋ ይህን ተናግሯልና።”’

12 “እንግዲህ አሁን ተነስተሽ ወደ ቤትሽ ሂጂ። እግርሽ ከተማዋን እንደረገጠ ልጁ ይሞታል። 13 ከኢዮርብዓም ቤተሰብ መካከል በመቃብር ቦታ የሚቀበረው እሱ ብቻ ስለሆነ እስራኤል ሁሉ አልቅሰው ይቀብሩታል፤ ምክንያቱም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ከኢዮርብዓም ቤት ሁሉ አንድ መልካም ነገር ያገኘበት እሱን ብቻ ነው። 14 ይሖዋም ከዚያን ቀን ጀምሮ እንዲያውም አሁኑኑ፣ የኢዮርብዓምን ቤት+ የሚያስወግድ በእስራኤል ላይ የሚነግሥ ንጉሥ ለራሱ ያስነሳል። 15 ይሖዋ በውኃ ውስጥ እንደሚወዛወዝ ሸምበቆ እስራኤልን ይመታል፤ እንዲሁም እስራኤላውያንን ለአባቶቻቸው ከሰጣቸው ከዚህ መልካም ምድር ላይ ይነቅላቸዋል፤+ ከወንዙም* ማዶ ይበትናቸዋል፤+ ምክንያቱም የማምለኪያ ግንዶችን*+ ለራሳቸው በማቆም ይሖዋን አስቆጥተውታል። 16 እሱም ኢዮርብዓም በሠራው ኃጢአትና እስራኤላውያን እንዲሠሩ ባደረገው ኃጢአት የተነሳ እስራኤልን ይተዋል።”+

17 በዚህ ጊዜ የኢዮርብዓም ሚስት ተነስታ በመሄድ ወደ ቲርጻ መጣች። ቤቱ ደጃፍ ላይ ስትደርስም ልጁ ሞተ። 18 ይሖዋ በአገልጋዩ በነቢዩ አኪያህ አማካኝነት በተናገረውም መሠረት ቀበሩት፤ እስራኤልም ሁሉ አለቀሰለት።

19 ኢዮርብዓም ስላደረገው ውጊያና+ ስለ አገዛዙ የሚናገረው የቀረው ታሪኩ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፏል። 20 ኢዮርብዓም የገዛበት የጊዜ ርዝመት* 22 ዓመት ነበር፤ ከዚያም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤+ በእሱም ምትክ ልጁ ናዳብ ነገሠ።+

21 ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰለሞን ልጅ ሮብዓም በይሁዳ ላይ ነግሦ ነበር። ሮብዓም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 41 ዓመት ነበር፤ እሱም ይሖዋ ስሙ እንዲኖርባት+ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል በመረጣት ከተማ+ በኢየሩሳሌም ሆኖ ለ17 ዓመት ገዛ። እናቱም ናዕማ የተባለች አሞናዊት+ ነበረች። 22 ይሁዳም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ፤+ እነሱም በፈጸሙት ኃጢአት የተነሳ ከአባቶቻቸው ይበልጥ አስቆጡት።+ 23 እነሱም ቢሆኑ በእያንዳንዱ ኮረብታ+ ላይና በእያንዳንዱ የለመለመ ዛፍ+ ሥር ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችን፣ የማምለኪያ ዓምዶችንና የማምለኪያ ግንዶችን*+ ለራሳቸው ሠሩ። 24 ሌላው ቀርቶ በምድሪቱ ላይ የቤተ መቅደስ ቀላጮች* ነበሩ።+ ይሖዋ ከእስራኤላውያን ፊት አባሮ ያስወጣቸው ብሔራት ይፈጽሟቸው የነበሩትን አስጸያፊ ነገሮች በሙሉ አደረጉ።

25 ንጉሥ ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብፁ ንጉሥ ሺሻቅ+ ኢየሩሳሌምን ለመውጋት መጣ።+ 26 እሱም በይሖዋ ቤት የነበሩትን ውድ ንብረቶችና በንጉሡ ቤት* የነበሩትን ውድ ንብረቶች ወሰደ።+ ሰለሞን የሠራቸውን የወርቅ ጋሻዎች ጨምሮ ሁሉንም ነገር ወሰደ።+ 27 በመሆኑም ንጉሥ ሮብዓም በእነሱ ምትክ የመዳብ ጋሻዎችን ሠርቶ የንጉሡን ቤት በር ለሚጠብቁት የዘብ* አለቆች ሰጣቸው። 28 ዘቦቹም ንጉሡ ወደ ይሖዋ ቤት በመጣ ቁጥር ጋሻዎቹን ያነግቡ ነበር፤ ከዚያም ወደ ዘቦቹ ክፍል ይመልሷቸው ነበር።

29 የቀረው የሮብዓም ታሪክና ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?+ 30 በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከል የማያቋርጥ ጦርነት ነበር።+ 31 በመጨረሻም ሮብዓም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማም+ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ። እናቱ ናዕማ የተባለች አሞናዊት+ ነበረች። በእሱም ምትክ ልጁ አብያም*+ ነገሠ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ