የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ነገሥት 17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ነገሥት የመጽሐፉ ይዘት

      • ኤልያስ ድርቅ እንደሚከሰት ትንቢት ተናገረ (1)

      • ኤልያስን ቁራዎች መገቡት (2-7)

      • ኤልያስ በሰራፕታ ወደምትገኘው መበለት ሄደ (8-16)

      • የመበለቷ ልጅ ሞተ፤ ከዚያም ከሞት ተነሳ (17-24)

1 ነገሥት 17:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “አምላኬ ይሖዋ ነው” የሚል ትርጉም አለው።

  • *

    ቃል በቃል “ፊቱ በምቆመውና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 22:9
  • +1ነገ 17:15, 16, 22, 24፤ 18:36, 38, 46፤ 2ነገ 2:8, 11፤ ሉቃስ 1:17፤ ዮሐ 1:19, 21
  • +ዘዳ 28:15, 23፤ ኤር 14:22፤ ሉቃስ 4:25፤ ያዕ 5:17

1 ነገሥት 17:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ደረቅ ወንዝም።”

1 ነገሥት 17:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 37:25፤ ማቴ 6:11

1 ነገሥት 17:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ደረቅ ወንዝ።”

1 ነገሥት 17:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 11:23፤ መሳ 15:19

1 ነገሥት 17:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 18:5

1 ነገሥት 17:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 4:25, 26

1 ነገሥት 17:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 11:32, 37

1 ነገሥት 17:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 4:2

1 ነገሥት 17:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 34:10፤ 37:17, 19፤ ፊልጵ 4:19

1 ነገሥት 17:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 10:41, 42፤ ሉቃስ 4:25, 26

1 ነገሥት 17:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 4:19, 20

1 ነገሥት 17:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ?”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 13:26

1 ነገሥት 17:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 4:21, 32

1 ነገሥት 17:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 99:6

1 ነገሥት 17:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ ትመለስለት።”

1 ነገሥት 17:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ ተመለሰችለት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ያዕ 5:16
  • +ዘዳ 32:39፤ 1ሳሙ 2:6፤ 2ነገ 4:32, 34፤ 13:21፤ ሉቃስ 7:15፤ 8:54, 55፤ ዮሐ 5:28, 29፤ 11:44፤ ሥራ 9:40, 41፤ 20:9, 10፤ ሮም 14:9፤ ዕብ 11:17, 19

1 ነገሥት 17:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 11:35

1 ነገሥት 17:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 3:2

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ነገ. 17:1ኢያሱ 22:9
1 ነገ. 17:11ነገ 17:15, 16, 22, 24፤ 18:36, 38, 46፤ 2ነገ 2:8, 11፤ ሉቃስ 1:17፤ ዮሐ 1:19, 21
1 ነገ. 17:1ዘዳ 28:15, 23፤ ኤር 14:22፤ ሉቃስ 4:25፤ ያዕ 5:17
1 ነገ. 17:4መዝ 37:25፤ ማቴ 6:11
1 ነገ. 17:6ዘኁ 11:23፤ መሳ 15:19
1 ነገ. 17:71ነገ 18:5
1 ነገ. 17:9ሉቃስ 4:25, 26
1 ነገ. 17:10ዕብ 11:32, 37
1 ነገ. 17:122ነገ 4:2
1 ነገ. 17:14መዝ 34:10፤ 37:17, 19፤ ፊልጵ 4:19
1 ነገ. 17:15ማቴ 10:41, 42፤ ሉቃስ 4:25, 26
1 ነገ. 17:172ነገ 4:19, 20
1 ነገ. 17:18ኢዮብ 13:26
1 ነገ. 17:192ነገ 4:21, 32
1 ነገ. 17:20መዝ 99:6
1 ነገ. 17:22ያዕ 5:16
1 ነገ. 17:22ዘዳ 32:39፤ 1ሳሙ 2:6፤ 2ነገ 4:32, 34፤ 13:21፤ ሉቃስ 7:15፤ 8:54, 55፤ ዮሐ 5:28, 29፤ 11:44፤ ሥራ 9:40, 41፤ 20:9, 10፤ ሮም 14:9፤ ዕብ 11:17, 19
1 ነገ. 17:23ዕብ 11:35
1 ነገ. 17:24ዮሐ 3:2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ነገሥት 17:1-24

አንደኛ ነገሥት

17 በዚህ ጊዜ ከጊልያድ+ ነዋሪዎች አንዱ የሆነው ቲሽባዊው ኤልያስ*+ አክዓብን “በማገለግለውና* ሕያው በሆነው በእስራኤል አምላክ በይሖዋ እምላለሁ፣ በእኔ ትእዛዝ ካልሆነ በቀር በእነዚህ ዓመታት ጠል ወይም ዝናብ አይኖርም!” አለው።+

2 የይሖዋም ቃል እንዲህ ሲል ወደ እሱ መጣ፦ 3 “ከዚህ ተነስተህ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ሂድ፤ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በከሪት ሸለቆም* ተደበቅ። 4 ከጅረቱ ትጠጣለህ፤ ቁራዎችም እዚያ ምግብ እንዲያመጡልህ አዛለሁ።”+ 5 እሱም ወዲያውኑ ሄዶ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ፤ ሄዶም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በከሪት ሸለቆ* ተቀመጠ። 6 ቁራዎቹም ጠዋትና ማታ ምግብና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤ እሱም ከጅረቱ ይጠጣ ነበር።+ 7 ሆኖም በምድሪቱ ላይ ዝናብ ስላልዘነበ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ጅረቱ ደረቀ።+

8 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እሱ መጣ፦ 9 “ተነስተህ በሲዶና ወደምትገኘው ወደ ሰራፕታ ሂድ፤ እዚያም ተቀመጥ። እኔም በዚያ አንዲት መበለት እንድትመግብህ አዛለሁ።”+ 10 ኤልያስም ተነስቶ ወደ ሰራፕታ ሄደ። ወደ ከተማዋ መግቢያ በደረሰም ጊዜ አንዲት መበለት ጭራሮ ስትለቅም አገኘ። መበለቲቱንም ጠርቶ “እባክሽ የምጠጣው ትንሽ ውኃ በዕቃ ስጪኝ” አላት።+ 11 ልታመጣለት ስትሄድም ጠራትና “እባክሽ ቁራሽ ዳቦም ይዘሽልኝ ነይ” አላት። 12 በዚህ ጊዜ እንዲህ አለችው፦ “ሕያው በሆነው አምላክህ በይሖዋ እምላለሁ፣ በማድጋው ውስጥ ካለው አንድ እፍኝ ዱቄትና በማሰሮው ውስጥ ካለው ጥቂት ዘይት በስተቀር ምንም ዳቦ የለኝም።+ ለእኔና ለልጄ የሆነች ነገር ለማዘጋጀት ጭራሮ እየለቀምኩ ነው። እኛም እሷን ቀምሰን እንሞታለን።”

13 ከዚያም ኤልያስ እንዲህ አላት፦ “አይዞሽ ስጋት አይግባሽ። ወደ ቤት ገብተሽ እንዳልሽው አድርጊ። ብቻ በመጀመሪያ ከዚያችው ካለችሽ ላይ ትንሽ ቂጣ ጋግረሽ አምጪልኝ። ከዚያ በኋላ ለአንቺና ለልጅሽ የሆነ ነገር ማዘጋጀት ትችያለሽ። 14 ምክንያቱም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ይሖዋ በምድሪቱ ላይ ዝናብ እስከሚያዘንብበት ዕለት ድረስ ከማድጋው ዱቄት አይጠፋም፤ ከማሰሮውም ዘይት አያልቅም።’”+ 15 ስለሆነም ሄዳ ኤልያስ እንዳላት አደረገች፤ እሷም ሆነች እሱ እንዲሁም ቤተሰቧ ለብዙ ቀናት ሲመገቡ ቆዩ።+ 16 ይሖዋ በኤልያስ አማካኝነት በተናገረው ቃል መሠረት ከማድጋው ዱቄት አልጠፋም፤ ከማሰሮውም ዘይት አላለቀም።

17 ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ የቤቱ ባለቤት፣ ልጇ ታመመ፤ ሕመሙም እጅግ ስለጠናበት እስትንፋሱ ቀጥ አለ።+ 18 በዚህ ጊዜ ሴትየዋ ኤልያስን “የእውነተኛው አምላክ ሰው ሆይ፣ ምን አደረግኩህ?* የመጣኸው በደሌን ልታስታውሰኝና ልጄን ልትገድል ነው?” አለችው።+ 19 እሱ ግን “ልጅሽን ስጪኝ” አላት። ከዚያም ልጁን ከእቅፏ ወስዶ እሱ ወዳረፈበት በሰገነቱ ላይ ወዳለው ክፍል ይዞት ወጣ፤ ልጁንም በራሱ አልጋ ላይ አስተኛው።+ 20 እሱም “አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣+ እኔን ያሳረፈችኝ የዚህች መበለት ልጅ እንዲሞት በማድረግ በእሷም ላይ መከራ ታመጣባታለህ?” በማለት ወደ ይሖዋ ጮኸ። 21 ከዚያም ልጁ ላይ ሦስት ጊዜ ከተዘረጋበት በኋላ “አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ የዚህ ልጅ ሕይወት ይመለስለት”* ብሎ ወደ ይሖዋ ጮኸ። 22 ይሖዋም የኤልያስን ልመና ሰማ፤+ የልጁም ሕይወት ተመለሰለት፤* እሱም ሕያው ሆነ።+ 23 ከዚያም ኤልያስ ልጁን ይዞት ሰገነት ላይ ካለው ክፍል ወደ ቤት ከወረደ በኋላ ለእናቱ ሰጣት፤ ኤልያስም “ይኸው፣ ልጅሽ ሕያው ሆኗል” አላት።+ 24 በዚህ ጊዜ ሴትየዋ ኤልያስን “አንተ በእርግጥ የአምላክ ሰው+ እንደሆንክ በአንደበትህም ያለው የይሖዋ ቃል እውነት እንደሆነ አሁን አወቅኩ” አለችው።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ