የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ነገሥት 2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ነገሥት የመጽሐፉ ይዘት

      • ዳዊት ለሰለሞን መመሪያ ሰጠው (1-9)

      • ዳዊት ሞተ፤ ሰለሞን ነገሠ (10-12)

      • አዶንያስ የጠነሰሰው ሴራ ሕይወቱን አሳጣው (13-25)

      • አብያታር ተባረረ፤ ኢዮዓብ ተገደለ (26-35)

      • ሺምአይ ተገደለ (36-46)

1 ነገሥት 2:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የምድርን ሁሉ መንገድ ልሄድ ነው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 31:6፤ ኢያሱ 1:6፤ 1ዜና 28:20
  • +1ነገ 3:7

1 ነገሥት 2:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 17:18-20፤ መክ 12:13

1 ነገሥት 2:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 6:5፤ 2ነገ 20:3፤ 23:3፤ 2ዜና 17:3፤ ማቴ 22:37
  • +2ሳሙ 7:12, 16፤ 1ነገ 8:25፤ 1ዜና 17:11፤ መዝ 132:11, 12

1 ነገሥት 2:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 3:27, 30
  • +2ሳሙ 17:25፤ 20:10፤ 1ዜና 2:17
  • +ዘኁ 35:33፤ 2ሳሙ 3:28

1 ነገሥት 2:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 3:29፤ 1ነገ 2:31-34

1 ነገሥት 2:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 19:31
  • +2ሳሙ 15:14
  • +2ሳሙ 17:27-29

1 ነገሥት 2:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 17:24
  • +2ሳሙ 16:5-7
  • +2ሳሙ 19:23

1 ነገሥት 2:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 22:28
  • +1ነገ 2:44, 46

1 ነገሥት 2:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 5:7፤ 1ዜና 11:7፤ 29:26, 27፤ ሥራ 2:29

1 ነገሥት 2:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 12:23
  • +2ሳሙ 5:4, 5

1 ነገሥት 2:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 7:8, 12፤ 1ዜና 29:23፤ 2ዜና 1:1፤ መዝ 89:36, 37፤ 132:12

1 ነገሥት 2:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ፊታቸውን ወደ እኔ አቅንተው እንደነበር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 1:5, 25
  • +1ዜና 22:9

1 ነገሥት 2:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 1:1, 3

1 ነገሥት 2:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 3:1, 2, 5
  • +2ሳሙ 16:21
  • +1ነገ 1:7
  • +2ሳሙ 8:16

1 ነገሥት 2:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የጠየቀው በገዛ ነፍሱ ፈርዶ ካልሆነ።”

1 ነገሥት 2:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሥርወ መንግሥት ባቋቋመልኝ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 22:9, 10
  • +2ሳሙ 7:11፤ 1ዜና 17:10
  • +1ነገ 1:51, 52

1 ነገሥት 2:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አዶንያስ ላይ ወደቀበት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 8:18፤ 1ነገ 1:8፤ 1ዜና 27:5

1 ነገሥት 2:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 22:20፤ 1ነገ 1:7
  • +ኢያሱ 21:8, 18፤ ኤር 1:1
  • +1ሳሙ 23:6፤ 2ሳሙ 15:24፤ 1ዜና 15:11, 12
  • +1ሳሙ 22:22, 23

1 ነገሥት 2:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 18:1
  • +1ሳሙ 2:31፤ 3:12

1 ነገሥት 2:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 18:14
  • +1ነገ 1:7
  • +1ዜና 21:29

1 ነገሥት 2:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 9:6፤ ዘፀ 21:14፤ ዘኁ 35:33፤ ዘዳ 19:13፤ 1ነገ 2:5

1 ነገሥት 2:32

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 2:8
  • +2ሳሙ 3:26, 27
  • +2ሳሙ 17:25
  • +2ሳሙ 20:10

1 ነገሥት 2:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 3:29

1 ነገሥት 2:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 11:24፤ 27:5
  • +1ሳሙ 2:35፤ 1ዜና 6:50, 53፤ 12:28፤ 16:37, 39፤ 24:3

1 ነገሥት 2:36

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 2:8

1 ነገሥት 2:37

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 15:23፤ 2ነገ 23:6፤ ዮሐ 18:1

1 ነገሥት 2:39

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 21:10፤ 27:2

1 ነገሥት 2:42

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 2:38

1 ነገሥት 2:44

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 16:5, 13
  • +መዝ 7:16፤ ምሳሌ 5:22

1 ነገሥት 2:45

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 21:6፤ 72:17

1 ነገሥት 2:46

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 2:8, 9
  • +2ዜና 1:1፤ ምሳሌ 16:12

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ነገ. 2:2ዘዳ 31:6፤ ኢያሱ 1:6፤ 1ዜና 28:20
1 ነገ. 2:21ነገ 3:7
1 ነገ. 2:3ዘዳ 17:18-20፤ መክ 12:13
1 ነገ. 2:4ዘዳ 6:5፤ 2ነገ 20:3፤ 23:3፤ 2ዜና 17:3፤ ማቴ 22:37
1 ነገ. 2:42ሳሙ 7:12, 16፤ 1ነገ 8:25፤ 1ዜና 17:11፤ መዝ 132:11, 12
1 ነገ. 2:52ሳሙ 3:27, 30
1 ነገ. 2:52ሳሙ 17:25፤ 20:10፤ 1ዜና 2:17
1 ነገ. 2:5ዘኁ 35:33፤ 2ሳሙ 3:28
1 ነገ. 2:62ሳሙ 3:29፤ 1ነገ 2:31-34
1 ነገ. 2:72ሳሙ 19:31
1 ነገ. 2:72ሳሙ 15:14
1 ነገ. 2:72ሳሙ 17:27-29
1 ነገ. 2:82ሳሙ 17:24
1 ነገ. 2:82ሳሙ 16:5-7
1 ነገ. 2:82ሳሙ 19:23
1 ነገ. 2:9ዘፀ 22:28
1 ነገ. 2:91ነገ 2:44, 46
1 ነገ. 2:102ሳሙ 5:7፤ 1ዜና 11:7፤ 29:26, 27፤ ሥራ 2:29
1 ነገ. 2:111ዜና 12:23
1 ነገ. 2:112ሳሙ 5:4, 5
1 ነገ. 2:122ሳሙ 7:8, 12፤ 1ዜና 29:23፤ 2ዜና 1:1፤ መዝ 89:36, 37፤ 132:12
1 ነገ. 2:151ነገ 1:5, 25
1 ነገ. 2:151ዜና 22:9
1 ነገ. 2:171ነገ 1:1, 3
1 ነገ. 2:221ዜና 3:1, 2, 5
1 ነገ. 2:222ሳሙ 16:21
1 ነገ. 2:221ነገ 1:7
1 ነገ. 2:222ሳሙ 8:16
1 ነገ. 2:241ዜና 22:9, 10
1 ነገ. 2:242ሳሙ 7:11፤ 1ዜና 17:10
1 ነገ. 2:241ነገ 1:51, 52
1 ነገ. 2:252ሳሙ 8:18፤ 1ነገ 1:8፤ 1ዜና 27:5
1 ነገ. 2:261ሳሙ 22:20፤ 1ነገ 1:7
1 ነገ. 2:26ኢያሱ 21:8, 18፤ ኤር 1:1
1 ነገ. 2:261ሳሙ 23:6፤ 2ሳሙ 15:24፤ 1ዜና 15:11, 12
1 ነገ. 2:261ሳሙ 22:22, 23
1 ነገ. 2:27ኢያሱ 18:1
1 ነገ. 2:271ሳሙ 2:31፤ 3:12
1 ነገ. 2:282ሳሙ 18:14
1 ነገ. 2:281ነገ 1:7
1 ነገ. 2:281ዜና 21:29
1 ነገ. 2:31ዘፍ 9:6፤ ዘፀ 21:14፤ ዘኁ 35:33፤ ዘዳ 19:13፤ 1ነገ 2:5
1 ነገ. 2:322ሳሙ 2:8
1 ነገ. 2:322ሳሙ 3:26, 27
1 ነገ. 2:322ሳሙ 17:25
1 ነገ. 2:322ሳሙ 20:10
1 ነገ. 2:332ሳሙ 3:29
1 ነገ. 2:351ዜና 11:24፤ 27:5
1 ነገ. 2:351ሳሙ 2:35፤ 1ዜና 6:50, 53፤ 12:28፤ 16:37, 39፤ 24:3
1 ነገ. 2:361ነገ 2:8
1 ነገ. 2:372ሳሙ 15:23፤ 2ነገ 23:6፤ ዮሐ 18:1
1 ነገ. 2:391ሳሙ 21:10፤ 27:2
1 ነገ. 2:421ነገ 2:38
1 ነገ. 2:442ሳሙ 16:5, 13
1 ነገ. 2:44መዝ 7:16፤ ምሳሌ 5:22
1 ነገ. 2:45መዝ 21:6፤ 72:17
1 ነገ. 2:461ነገ 2:8, 9
1 ነገ. 2:462ዜና 1:1፤ ምሳሌ 16:12
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
  • 38
  • 39
  • 40
  • 41
  • 42
  • 43
  • 44
  • 45
  • 46
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ነገሥት 2:1-46

አንደኛ ነገሥት

2 ዳዊት የሚሞትበት ቀን ሲቃረብ ልጁን ሰለሞንን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ 2 “እንግዲህ እኔ የምሞትበት ጊዜ ቀርቧል።* ስለሆነም በርታ፤+ ወንድ ሁን።+ 3 በሙሴ ሕግ ላይ በተጻፈው መሠረት በመንገዶቹ በመሄድ እንዲሁም ደንቦቹን፣ ትእዛዛቱን፣ ፍርዶቹንና ማሳሰቢያዎቹን በመጠበቅ ለአምላክህ ለይሖዋ ያለብህን ግዴታ ፈጽም፤+ ይህን ካደረግክ የምታከናውነው ሁሉ ይሳካልሃል፤ በምትሄድበትም ሁሉ ይቃናልሃል። 4 ይሖዋም እንዲህ በማለት የገባልኝን ቃል ይፈጽማል፦ ‘ልጆችህ፣ በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው*+ በፊቴ በታማኝነት በመመላለስ መንገዳቸውን ከጠበቁ ከዘር ሐረግህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው አይታጣም።’+

5 “የጽሩያ ልጅ ኢዮዓብ በእኔ ላይ ያደረገውን ነገር ይኸውም በሁለቱ የእስራኤል ሠራዊት አለቆች ማለትም በኔር ልጅ በአበኔርና+ በየቴር ልጅ በአሜሳይ+ ላይ ያደረገውን በሚገባ ታውቃለህ። ይህ ሰው እነዚህን ሰዎች በመግደል ጦርነት ሳይኖር በሰላሙ ጊዜ ደም አፍስሷል፤+ እንዲሁም በወገቡ ላይ የታጠቀው ቀበቶና በእግሩ ላይ ያደረገው ጫማ በጦርነት ጊዜ በሚፈሰው ደም እንዲበከል አድርጓል። 6 እንግዲህ እንደ ጥበብህ አድርግ፤ ሽበቱ በሰላም ወደ መቃብር* እንዲወርድ አታድርግ።+

7 “ሆኖም ለቤርዜሊ+ ልጆች ታማኝ ፍቅር አሳያቸው፤ እነሱም ከማዕድህ ከሚበሉ ሰዎች መካከል ይሁኑ፤ ምክንያቱም ከወንድምህ ከአቢሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ+ እነሱም ከጎኔ ቆመው ነበር።+

8 “በተጨማሪም ከባሁሪም የመጣው ቢንያማዊው የጌራ ልጅ ሺምአይ አብሮህ አለ። ወደ ማሃናይም በሄድኩበት ዕለት+ ከባድ እርግማን የረገመኝ እሱ ነው፤+ ሆኖም እኔን ለማግኘት ወደ ዮርዳኖስ በወረደ ጊዜ ‘በሰይፍ አልገድልህም’ ብዬ በይሖዋ ማልኩለት።+ 9 አንተ ጥበበኛ ስለሆንክና በእሱ ላይ ምን ማድረግ እንዳለብህ ስለምታውቅ ሳትቀጣ አትተወው፤+ ሽበቱ በደም ወደ መቃብር* እንዲወርድ አድርግ።”+

10 ከዚያም ዳዊት ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማም+ ተቀበረ። 11 ዳዊት በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ የገዛው ለ40 ዓመት ነበር። በኬብሮን+ ለ7 ዓመት፣ በኢየሩሳሌም ደግሞ ለ33 ዓመት ነገሠ።+

12 ከዚያም ሰለሞን በአባቱ በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀመጠ፤ ቀስ በቀስም ንግሥናው እየጸና ሄደ።+

13 ከጊዜ በኋላም የሃጊት ልጅ አዶንያስ ወደ ሰለሞን እናት ወደ ቤርሳቤህ መጣ። እሷም “የመጣኸው በሰላም ነው?” አለችው፤ እሱም “አዎ፣ በሰላም ነው” አላት። 14 ከዚያም “አንድ የምነግርሽ ጉዳይ አለኝ” አላት። እሷም “እሺ፣ ንገረኝ” አለችው። 15 እሱም እንዲህ አላት፦ “ንግሥናው የእኔ ሊሆን እንደነበረና እስራኤልም ሁሉ ይነግሣል ብለው ይጠብቁ እንደነበር* በሚገባ ታውቂያለሽ፤+ ይሁንና ንግሥናው የእኔ መሆኑ ቀርቶ የወንድሜ ሆነ፤ ምክንያቱም ይሖዋ ንግሥናው የእሱ እንዲሆን ወስኖ ነበር።+ 16 ሆኖም አሁን አንድ የምጠይቅሽ ነገር አለ። መቼም አታሳፍሪኝም።” እሷም “እሺ ንገረኝ” አለችው። 17 እሱም “እባክሽ፣ ንጉሥ ሰለሞን የጠየቅሽውን እንቢ ስለማይልሽ ሹነማዊቷን አቢሻግን+ እንዲድርልኝ ጠይቂው” አላት። 18 በዚህ ጊዜ ቤርሳቤህ “መልካም! ንጉሡን አነጋግርልሃለሁ” አለችው።

19 በመሆኑም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጉዳይ ልትነግረው ወደ ንጉሥ ሰለሞን ገባች። ንጉሡም ወዲያውኑ ሊቀበላት ተነሳ፤ ሰገደላትም። ከዚያም ዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ የንጉሡም እናት በቀኙ እንድትቀመጥ ዙፋን አስመጣላት። 20 እሷም “አንዲት ትንሽ ነገር ልጠይቅህ አስቤ ነበር። መቼም እንቢ አትለኝም” አለችው። ንጉሡም “እናቴ ሆይ፣ ንገሪኝ፤ የጠየቅሽኝን እንቢ አልልሽም” አላት። 21 እሷም “ሹነማዊቷ አቢሻግ ለወንድምህ ለአዶንያስ ትዳርለት” አለችው። 22 በዚህ ጊዜ ንጉሥ ሰለሞን ለእናቱ እንዲህ ሲል መለሰላት፦ “ለአዶንያስ ሹነማዊቷን አቢሻግን ብቻ ለምን ትጠይቂለታለሽ? ታላቅ ወንድሜ+ ስለሆነ ንግሥናም ጠይቂለት እንጂ፤+ ካህኑ አብያታርና የጽሩያ+ ልጅ ኢዮዓብም+ እየደገፉት ነው።”

23 ከዚያም ንጉሥ ሰለሞን እንዲህ ሲል በይሖዋ ማለ፦ “አዶንያስ ይህን በመጠየቁ ሕይወቱን ሳያጣ ቢቀር* አምላክ ይህን ያድርግብኝ፤ ከዚህ የከፋም ነገር ያምጣብኝ። 24 አሁንም በሚገባ ባጸናኝ፣+ በአባቴ በዳዊት ዙፋን ላይ ባስቀመጠኝና በገባው ቃል መሠረት ቤት በሠራልኝ*+ ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ አዶንያስ በዛሬዋ ዕለት ይገደላል።”+ 25 ንጉሥ ሰለሞንም ወዲያውኑ የዮዳሄን ልጅ በናያህን+ ላከው፤ እሱም ወጥቶ አዶንያስን መታው፤* እሱም ሞተ።

26 ንጉሡም ካህኑን አብያታርን+ እንዲህ አለው፦ “በአናቶት+ ወደሚገኘው እርሻህ ሂድ! አንተ ሞት የሚገባህ ሰው ነህ፤ ሆኖም በአባቴ በዳዊት ፊት የሉዓላዊውን ጌታ የይሖዋን ታቦት ስለተሸከምክና+ በአባቴ ላይ የደረሰውን መከራ ሁሉ ስለተጋራህ ዛሬ አልገድልህም።”+ 27 በመሆኑም ይሖዋ በሴሎ፣+ በኤሊ ቤት+ ላይ እንደሚደርስ የተናገረው ነገር ይፈጸም ዘንድ ሰለሞን አብያታርን የይሖዋ ካህን ሆኖ እንዳያገለግል አባረረው።

28 ኢዮዓብ ቀደም ሲል ከአቢሴሎም+ጋር ወግኖ ያልነበረ ቢሆንም አዶንያስን+ ደግፎ ስለነበር ይህን ወሬ ሲሰማ ወደ ይሖዋ ድንኳን+ በመሸሽ የመሠዊያውን ቀንዶች ያዘ። 29 ከዚያም ንጉሥ ሰለሞን “ኢዮዓብ ወደ ይሖዋ ድንኳን ሸሽቶ እዚያ በመሠዊያው አጠገብ ይገኛል” ተብሎ ተነገረው። በመሆኑም ሰለሞን የዮዳሄን ልጅ በናያህን “ሂድና ግደለው!” ብሎ ላከው። 30 ስለዚህ በናያህ ወደ ይሖዋ ድንኳን ሄዶ ኢዮዓብን “ንጉሡ ‘ና ውጣ!’ ብሎሃል” አለው። እሱ ግን “እዚሁ እሞታታለሁ እንጂ በፍጹም አልወጣም!” አለ። በዚህ ጊዜ በናያህ “ኢዮዓብ እንዲህ እንዲህ ብሏል፤ እንዲህም ሲል መልሶልኛል” በማለት ለንጉሡ ተናገረ። 31 ከዚያም ንጉሡ እንዲህ አለው፦ “በል ልክ እንዳለው አድርግ፤ ግደለውና ቅበረው፤ ኢዮዓብ አላግባብ ካፈሰሰውም ደም እኔንና የአባቴን ቤት አንጻ።+ 32 ኢዮዓብ አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ከእሱ ይልቅ ጻድቅና የተሻሉ የነበሩትን ሁለት ሰዎች ማለትም የእስራኤል ሠራዊት አለቃ+ የነበረውን የኔርን ልጅ አበኔርንና+ የይሁዳ ሠራዊት አለቃ+ የነበረውን የየቴርን ልጅ አሜሳይን+ በሰይፍ መትቶ በመግደሉ ይሖዋ ደሙን በራሱ ላይ ይመልስበታል። 33 ደማቸውም ለዘላለም በኢዮዓብ ራስና በዘሮቹ ራስ ላይ ይሆናል፤+ በዳዊት፣ በዘሮቹ፣ በቤቱና በዙፋኑ ላይ ግን የይሖዋ ሰላም ለዘላለም ይሁን።” 34 ከዚያም የዮዳሄ ልጅ በናያህ ወጥቶ ኢዮዓብን መትቶ ገደለው፤ እሱም በምድረ በዳ በሚገኘው በራሱ ቤት ተቀበረ። 35 ከዚያም ንጉሡ በኢዮዓብ ምትክ የዮዳሄን ልጅ በናያህን+ በሠራዊቱ ላይ ሾመው፤ በአብያታር ቦታ ደግሞ ካህኑን ሳዶቅን+ ሾመው።

36 ንጉሡም ሺምአይን+ አስጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ኢየሩሳሌም ውስጥ ቤት ሠርተህ በዚያ ኑር፤ ከዚያም ወጥተህ ወደ ሌላ ቦታ አትሂድ። 37 ከዚያ ወጥተህ የቄድሮንን ሸለቆ+ የተሻገርክ ቀን ግን እንደምትሞት እወቅ። ደምህ በራስህ ላይ ይሆናል።” 38 ሺምአይም ንጉሡን “ጥሩ ሐሳብ ነው። አገልጋይህ፣ ጌታዬ ንጉሡ እንዳለው ያደርጋል” አለው። ስለሆነም ሺምአይ በኢየሩሳሌም ለብዙ ጊዜ ተቀመጠ።

39 ሆኖም ከሦስት ዓመት በኋላ ከሺምአይ ባሪያዎች መካከል ሁለቱ የጌት ንጉሥ ወደሆነው ወደ ማአካ ልጅ ወደ አንኩስ+ ኮበለሉ። ሺምአይም “ባሪያዎችህ ያሉት ጌት ነው” ተብሎ ሲነገረው 40 ወዲያውኑ አህያውን ጭኖ ባሪያዎቹን ለመፈለግ በጌት ወዳለው ወደ አንኩስ አቀና። ሺምአይ ባሪያዎቹን ይዞ ከጌት ሲመለስ 41 ለሰለሞን “ሺምአይ ከኢየሩሳሌም ወጥቶ ወደ ጌት ሄዶ ነበር፤ አሁን ግን ተመልሷል” ተብሎ ተነገረው። 42 በዚህ ጊዜ ንጉሡ ሺምአይን አስጠርቶ እንዲህ አለው፦ “‘ከዚህ ወጥተህ ወደ ሌላ ቦታ በሄድክ ቀን እንደምትሞት እወቅ’ ብዬ በይሖዋ አስምዬህና አስጠንቅቄህ አልነበረም? አንተስ ብትሆን ‘ጥሩ ሐሳብ ነው፤ እንዳልከኝ አደርጋለሁ’ ብለኸኝ አልነበረም?+ 43 ታዲያ በይሖዋ ፊት የገባኸውን መሐላና የሰጠሁህን ትእዛዝ ያልጠበቅከው ለምንድን ነው?” 44 ከዚያም ንጉሡ፣ ሺምአይን እንዲህ አለው፦ “በአባቴ በዳዊት ላይ ያደረግከውን ክፉ ነገር ሁሉ ልብህ ያውቀዋል፤+ ይሖዋም ያደረግከውን ክፉ ነገር በራስህ ላይ ይመልስብሃል።+ 45 ንጉሥ ሰለሞን ግን ይባረካል፤+ የዳዊትም ዙፋን በይሖዋ ፊት ለዘላለም ይጸናል።” 46 ከዚያም ንጉሡ የዮዳሄን ልጅ በናያህን አዘዘው፤ እሱም ወጥቶ ሺምአይን መትቶ ገደለው።+

በዚህ መንገድ መንግሥቱ በሰለሞን እጅ ጸና።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ