የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ነገሥት 22
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ነገሥት የመጽሐፉ ይዘት

      • ኢዮሳፍጥ ከአክዓብ ጋር ግንባር ፈጠረ (1-12)

      • ሚካያህ ትንቢት ተናገረ (13-28)

        • አንድ መንፈስ አክዓብን እንደሚያሞኘው ተናገረ (21, 22)

      • አክዓብ ራሞትጊልያድ ላይ ተገደለ (29-40)

      • ኢዮሳፍጥ በይሁዳ ላይ የነገሠበት ጊዜ (41-50)

      • አካዝያስ በእስራኤል ላይ ነገሠ (51-53)

1 ነገሥት 22:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 15:24
  • +2ዜና 18:2, 3

1 ነገሥት 22:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 20:8, 9፤ 1ነገ 4:7, 13

1 ነገሥት 22:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 3:7፤ 2ዜና 19:2

1 ነገሥት 22:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 18:4, 5
  • +ዘኁ 27:21

1 ነገሥት 22:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 3:11፤ 2ዜና 18:6, 7

1 ነገሥት 22:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 18:4
  • +1ነገ 21:20፤ 2ዜና 36:16፤ ኢሳ 30:9, 10፤ ኤር 38:4

1 ነገሥት 22:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 18:8-11

1 ነገሥት 22:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 13:2, 3

1 ነገሥት 22:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ትገፋቸዋለህ።”

1 ነገሥት 22:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 18:12-16

1 ነገሥት 22:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:15, 25

1 ነገሥት 22:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 18:17

1 ነገሥት 22:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 6:1፤ ሕዝ 1:26
  • +2ዜና 18:18-22፤ ኢዮብ 1:6፤ ዳን 7:9, 10፤ ማቴ 18:10፤ ራእይ 5:11

1 ነገሥት 22:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አንድ መልአክ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 104:4፤ ዕብ 1:7, 14

1 ነገሥት 22:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 22:6

1 ነገሥት 22:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 14:9
  • +1ነገ 20:42

1 ነገሥት 22:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 18:23-27

1 ነገሥት 22:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 11:32, 36

1 ነገሥት 22:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 16:28, 29

1 ነገሥት 22:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 18:28-32

1 ነገሥት 22:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 35:22

1 ነገሥት 22:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 20:1

1 ነገሥት 22:34

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሳያስብ።”

  • *

    ቃል በቃል “ከሰፈሩ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 18:33, 34

1 ነገሥት 22:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 20:42

1 ነገሥት 22:36

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 22:17

1 ነገሥት 22:38

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “እነሱም የጦር ሠረገላውን ዝሙት አዳሪዎች ገላቸውን በሚታጠቡበት በሰማርያ ኩሬ ባጠቡት ጊዜ ይሖዋ በተናገረው መሠረት ውሾች ደሙን ላሱት” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 21:18, 19

1 ነገሥት 22:39

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥትና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 10:22፤ ሕዝ 27:15

1 ነገሥት 22:40

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 16:28
  • +2ነገ 1:2፤ 2ዜና 20:35

1 ነገሥት 22:41

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 3:10፤ 2ዜና 17:1፤ 20:31፤ ማቴ 1:8

1 ነገሥት 22:43

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 15:11፤ 2ዜና 14:11፤ 15:8
  • +2ዜና 17:3
  • +ዘዳ 12:14፤ 1ነገ 14:23፤ 15:14

1 ነገሥት 22:44

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 18:1፤ 19:2

1 ነገሥት 22:46

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ግብረ ሰዶማውያን ሆነው የሴት ዓይነት ሚና ያላቸውን ወንዶች ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 15:11, 12
  • +ዘዳ 23:17, 18፤ 1ነገ 14:24

1 ነገሥት 22:47

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 36:1, 9
  • +2ሳሙ 8:14፤ 2ነገ 8:20-22፤ መዝ 108:9

1 ነገሥት 22:48

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 10:22
  • +1ነገ 9:26፤ 2ዜና 20:35-37

1 ነገሥት 22:50

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 2:10
  • +2ነገ 8:16፤ 2ዜና 21:1, 5

1 ነገሥት 22:51

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 1:2

1 ነገሥት 22:52

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 16:30
  • +1ነገ 21:25
  • +1ነገ 12:28-30፤ 13:33

1 ነገሥት 22:53

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 16:31, 32፤ 2ነገ 1:2
  • +ዘፀ 20:3፤ 34:14

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ነገ. 22:21ነገ 15:24
1 ነገ. 22:22ዜና 18:2, 3
1 ነገ. 22:3ኢያሱ 20:8, 9፤ 1ነገ 4:7, 13
1 ነገ. 22:42ነገ 3:7፤ 2ዜና 19:2
1 ነገ. 22:52ዜና 18:4, 5
1 ነገ. 22:5ዘኁ 27:21
1 ነገ. 22:72ነገ 3:11፤ 2ዜና 18:6, 7
1 ነገ. 22:81ነገ 18:4
1 ነገ. 22:81ነገ 21:20፤ 2ዜና 36:16፤ ኢሳ 30:9, 10፤ ኤር 38:4
1 ነገ. 22:92ዜና 18:8-11
1 ነገ. 22:10ሕዝ 13:2, 3
1 ነገ. 22:132ዜና 18:12-16
1 ነገ. 22:17ዘዳ 28:15, 25
1 ነገ. 22:182ዜና 18:17
1 ነገ. 22:19ኢሳ 6:1፤ ሕዝ 1:26
1 ነገ. 22:192ዜና 18:18-22፤ ኢዮብ 1:6፤ ዳን 7:9, 10፤ ማቴ 18:10፤ ራእይ 5:11
1 ነገ. 22:21መዝ 104:4፤ ዕብ 1:7, 14
1 ነገ. 22:221ነገ 22:6
1 ነገ. 22:23ሕዝ 14:9
1 ነገ. 22:231ነገ 20:42
1 ነገ. 22:242ዜና 18:23-27
1 ነገ. 22:27ዕብ 11:32, 36
1 ነገ. 22:28ዘኁ 16:28, 29
1 ነገ. 22:292ዜና 18:28-32
1 ነገ. 22:302ዜና 35:22
1 ነገ. 22:311ነገ 20:1
1 ነገ. 22:342ዜና 18:33, 34
1 ነገ. 22:351ነገ 20:42
1 ነገ. 22:361ነገ 22:17
1 ነገ. 22:381ነገ 21:18, 19
1 ነገ. 22:391ነገ 10:22፤ ሕዝ 27:15
1 ነገ. 22:401ነገ 16:28
1 ነገ. 22:402ነገ 1:2፤ 2ዜና 20:35
1 ነገ. 22:411ዜና 3:10፤ 2ዜና 17:1፤ 20:31፤ ማቴ 1:8
1 ነገ. 22:431ነገ 15:11፤ 2ዜና 14:11፤ 15:8
1 ነገ. 22:432ዜና 17:3
1 ነገ. 22:43ዘዳ 12:14፤ 1ነገ 14:23፤ 15:14
1 ነገ. 22:442ዜና 18:1፤ 19:2
1 ነገ. 22:461ነገ 15:11, 12
1 ነገ. 22:46ዘዳ 23:17, 18፤ 1ነገ 14:24
1 ነገ. 22:47ዘፍ 36:1, 9
1 ነገ. 22:472ሳሙ 8:14፤ 2ነገ 8:20-22፤ መዝ 108:9
1 ነገ. 22:481ነገ 10:22
1 ነገ. 22:481ነገ 9:26፤ 2ዜና 20:35-37
1 ነገ. 22:501ነገ 2:10
1 ነገ. 22:502ነገ 8:16፤ 2ዜና 21:1, 5
1 ነገ. 22:512ነገ 1:2
1 ነገ. 22:521ነገ 16:30
1 ነገ. 22:521ነገ 21:25
1 ነገ. 22:521ነገ 12:28-30፤ 13:33
1 ነገ. 22:531ነገ 16:31, 32፤ 2ነገ 1:2
1 ነገ. 22:53ዘፀ 20:3፤ 34:14
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
  • 38
  • 39
  • 40
  • 41
  • 42
  • 43
  • 44
  • 45
  • 46
  • 47
  • 48
  • 49
  • 50
  • 51
  • 52
  • 53
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ነገሥት 22:1-53

አንደኛ ነገሥት

22 በሶርያና በእስራኤል መካከል ለሦስት ዓመት ጦርነት አልነበረም። 2 በሦስተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ+ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወረደ።+ 3 የእስራኤልም ንጉሥ አገልጋዮቹን “ራሞትጊልያድ+ የእኛ እንደሆነች ታውቃላችሁ አይደል? ሆኖም እሷን ከሶርያ ንጉሥ እጅ ለማስመለስ እያመነታን ነው” አላቸው። 4 ከዚያም ኢዮሳፍጥን “በራሞትጊልያድ ለመዋጋት ከእኔ ጋር አብረህ ትሄዳለህ?” አለው። በዚህ ጊዜ ኢዮሳፍጥ ለእስራኤል ንጉሥ “እኔ ማለት እኮ አንተ ማለት ነህ። ሕዝቤ ሕዝብህ ነው። የእኔ ፈረሶችም የአንተ ፈረሶች ናቸው” በማለት መለሰለት።+

5 ሆኖም ኢዮሳፍጥ የእስራኤልን ንጉሥ “እባክህ፣ በመጀመሪያ ይሖዋ ምን እንደሚል+ ጠይቅ”+ አለው። 6 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ 400 ገደማ የሚሆኑ ነቢያትን አንድ ላይ ሰብስቦ “ራሞትጊልያድን ለመውጋት ልዝመት ወይስ ይቅርብኝ?” አላቸው። እነሱም “ዝመት፤ ይሖዋ በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል” አሉት።

7 ከዚያም ኢዮሳፍጥ “በዚህ ቦታ የይሖዋ ነቢይ የለም? ካለ በእሱም አማካኝነት እንጠይቅ” አለ።+ 8 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮሳፍጥን “በእሱ አማካኝነት ይሖዋን ልንጠይቅ የምንችልበት አንድ ሰው ይቀራል፤+ ሆኖም ስለ እኔ መጥፎ ነገር ብቻ እንጂ መልካም ነገር ፈጽሞ ስለማይተነብይ በጣም እጠላዋለሁ።+ እሱም የይምላ ልጅ ሚካያህ ነው” አለው። ኢዮሳፍጥ ግን “ንጉሡ እንዲህ ሊል አይገባም” አለ።

9 ስለሆነም የእስራኤል ንጉሥ አንድ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣን ጠርቶ “የይምላን ልጅ ሚካያህን በአስቸኳይ ይዘኸው ና” አለው።+ 10 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ የንግሥና ልብሳቸውን ለብሰው በሰማርያ መግቢያ በር ላይ በሚገኘው አውድማ ላይ በየዙፋናቸው ተቀምጠው ነበር፤ ነቢያቱም ሁሉ በፊታቸው ትንቢት ይናገሩ ነበር።+ 11 ከዚያም የኬናአና ልጅ ሴዴቅያስ የብረት ቀንዶች ሠርቶ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሶርያውያንን እስክታጠፋቸው ድረስ በእነዚህ ትወጋቸዋለህ’”* አለ። 12 ሌሎቹ ነቢያትም ሁሉ “ወደ ራሞትጊልያድ ውጣ፤ ይሳካልሃል፤ ይሖዋም እሷን በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል” በማለት ተመሳሳይ ትንቢት ይናገሩ ነበር።

13 ሚካያህን ለመጥራት የሄደው መልእክተኛም “እነሆ፣ ነቢያቱ ሁሉ በአንድ ድምፅ ለንጉሡ የተናገሩት ነገር ጥሩ ነው። እባክህ፣ የአንተም ቃል እንደ እነሱ ይሁን፤ አንተም ጥሩ ነገር ተናገር” አለው።+ 14 ሚካያህ ግን “ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ የምናገረው ይሖዋ የሚለኝን ብቻ ነው” አለ። 15 ከዚያም ወደ ንጉሡ ገባ፤ ንጉሡም “ሚካያህ፣ ራሞትጊልያድን ለመውጋት እንዝመት ወይስ ይቅርብን?” ሲል ጠየቀው። እሱም ወዲያውኑ “ውጡ፤ ይቀናችኋል፤ ይሖዋ በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል” በማለት መለሰለት። 16 በዚህ ጊዜ ንጉሡ “በይሖዋ ስም ከእውነት በስተቀር ሌላ አንዳች ነገር እንዳትነግረኝ የማስምልህ ስንት ጊዜ ነው?” አለው። 17 በመሆኑም ሚካያህ እንዲህ በማለት ተናገረ፦ “እስራኤላውያን ሁሉ እረኛ እንደሌላቸው በጎች በተራሮች ላይ ተበታትነው አያለሁ።+ ይሖዋም ‘እነዚህ ጌታ የላቸውም። እያንዳንዳቸው በሰላም ወደየቤታቸው ይመለሱ’ ብሏል።”

18 ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ ኢዮሳፍጥን “‘ስለ እኔ መጥፎ ነገር ብቻ እንጂ ጥሩ ነገር አይተነብይም’ ብዬህ አልነበረም?” አለው።+

19 በዚህ ጊዜ ሚካያህ እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ የይሖዋን ቃል ስማ፦ ይሖዋ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ+ የሰማያት ሠራዊትም ሁሉ በቀኙና በግራው አጠገቡ ቆመው+ አየሁ። 20 ከዚያም ይሖዋ ‘በራሞትጊልያድ ላይ ዘምቶ እዚያው እንዲሞት አክዓብን ማን ያሞኘዋል?’ አለ። በዚህ ጊዜ አንዱ አንድ ነገር፣ ሌላው ደግሞ ሌላ ነገር ተናገረ። 21 ከዚያም አንድ መንፈስ*+ ወደ ፊት ወጥቶ ይሖዋ ፊት በመቆም ‘እኔ አሞኘዋለሁ’ አለ። ይሖዋም ‘እንዴት አድርገህ?’ አለው። 22 ‘እኔ እወጣና በነቢያቱ ሁሉ አፍ ላይ አሳሳች መንፈስ እሆናለሁ’ አለ።+ እሱም ‘እንግዲያው ታሞኘዋለህ፤ ደግሞም ይሳካልሃል። ውጣና እንዳልከው አድርግ’ አለው። 23 ይሖዋም በእነዚህ ነቢያትህ ሁሉ አፍ ላይ አሳሳች መንፈስ አኑሯል፤+ ሆኖም ይሖዋ ጥፋት እንደሚመጣብህ ተናግሯል።”+

24 የኬናአና ልጅ ሴዴቅያስም ወደ ሚካያህ ቀርቦ በጥፊ መታውና “ለመሆኑ የይሖዋ መንፈስ እኔን በየት በኩል አልፎ ነው አንተን ያናገረህ?” አለው።+ 25 ሚካያህም “በየት በኩል እንዳለፈማ፣ ለመደበቅ ወደ ውስጠኛው ክፍል በምትገባበት ቀን ታውቀዋለህ” አለው። 26 ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ እንዲህ አለ፦ “ሚካያህን ወስዳችሁ ለከተማው አለቃ ለአምዖን እና የንጉሡ ልጅ ለሆነው ለዮአስ አስረክቡት። 27 እንዲህም በሏቸው፦ ‘ንጉሡ “በሰላም ተመልሼ እስክመጣ ድረስ ይህን ሰው እስር ቤት አቆዩት፤+ ጥቂት ምግብና ውኃ ብቻ ስጡት” ብሏል።’” 28 ሚካያህ ግን “እውነት አንተ በሰላም ከተመለስክ ይሖዋ በእኔ አልተናገረም ማለት ነው!” አለ።+ ከዚያም “እናንተ ሰዎች፣ ሁላችሁም ልብ በሉ” አለ።

29 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ወደ ራሞትጊልያድ+ ወጡ። 30 የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሳፍጥን “እኔ ማንነቴ እንዳይታወቅ ራሴን ለውጬ ወደ ውጊያው እገባለሁ፤ አንተ ግን ንጉሣዊ ልብስህን ልበስ” አለው። ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ ማንነቱ እንዳይታወቅ ራሱን ለውጦ+ ወደ ውጊያው ገባ። 31 በዚህ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ 32ቱን የሠረገላ አዛዦች+ “ከእስራኤል ንጉሥ በስተቀር ከትንሹም ሆነ ከትልቁ፣ ከማንም ጋር እንዳትዋጉ” በማለት አዟቸው ነበር። 32 የሠረገሎቹ አዛዦችም ኢዮሳፍጥን ባዩት ጊዜ “ያለጥርጥር ይህ የእስራኤል ንጉሥ ነው” ብለው አሰቡ። በመሆኑም ሊወጉት ወደ እሱ ዞሩ፤ በዚህ ጊዜ ኢዮሳፍጥ እርዳታ ለማግኘት ጮኸ። 33 የሠረገሎቹ አዛዦችም የእስራኤል ንጉሥ አለመሆኑን ሲያዩ ወዲያውኑ እሱን ማሳደዳቸውን ትተው ተመለሱ።

34 ይሁንና አንድ ሰው በነሲብ* ቀስቱን ሲያስወነጭፍ የእስራኤልን ንጉሥ የጥሩሩ መጋጠሚያ ላይ ወጋው። ስለሆነም ንጉሡ ሠረገላ ነጂውን “ክፉኛ ስለቆሰልኩ ሠረገላውን አዙረህ ከጦርነቱ* ይዘኸኝ ውጣ” አለው።+ 35 ያን ቀን ሙሉ የተፋፋመ ውጊያ ተካሄደ፤ ንጉሡንም ሠረገላው ውስጥ እንዳለ ፊቱን ወደ ሶርያውያን አዙረው ደግፈው አቆሙት። ከቁስሉ የሚወጣውም ደም በጦር ሠረገላው ውስጥ ይፈስ ነበር፤ አመሻሹም ላይ ሞተ።+ 36 ፀሐይ ልትጠልቅም ስትል በሰፈሩ መካከል “እያንዳንዱ ሰው ወደ ከተማው፣ እያንዳንዱም ሰው ወደ ምድሩ ይመለስ!” የሚል ጥሪ አስተጋባ።+ 37 በዚህ መንገድ ንጉሡ ሞተ፤ ወደ ሰማርያም ተወሰደ፤ ንጉሡንም በሰማርያ ቀበሩት። 38 እነሱም የጦር ሠረገላውን በሰማርያ ኩሬ ባጠቡት ጊዜ ይሖዋ በተናገረው መሠረት ውሾች ደሙን ላሱት፤ ዝሙት አዳሪዎችም በዚያ ገላቸውን እየታጠቡ ነበር።*+

39 ስለቀረው የአክዓብ ታሪክ፣ ስላደረጋቸው ነገሮች ሁሉ፣ በዝሆን ጥርስ ስለሠራው ቤትና*+ ስለገነባቸው ከተሞች ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ ይገኝ የለም? 40 በመጨረሻም አክዓብ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤+ በእሱም ምትክ ልጁ አካዝያስ+ ነገሠ።

41 የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ በነገሠ በአራተኛው ዓመት የአሳ ልጅ ኢዮሳፍጥ+ በይሁዳ ላይ ነገሠ። 42 ኢዮሳፍጥ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 35 ዓመት የነበረ ሲሆን በኢየሩሳሌም 25 ዓመት ገዛ። እናቱ የሺልሂ ልጅ አዙባ ነበረች። 43 እሱም በአባቱ በአሳ+ መንገድ ሁሉ ሄደ። ከዚያ ፈቀቅ አላለም፤ በይሖዋም ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ።+ ይሁን እንጂ ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች አልተወገዱም ነበር፤ ሕዝቡም ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች ላይ መሠዋቱንና የሚጨስ መሥዋዕት ማቅረቡን አልተወም ነበር።+ 44 ኢዮሳፍጥ ከእስራኤል ንጉሥ ጋር ሰላማዊ ግንኙነት ነበረው።+ 45 የቀረው የኢዮሳፍጥ ታሪክ፣ በኃያልነቱ የፈጸማቸው ጀብዱዎችና ያደረጋቸው ውጊያዎች በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? 46 ኢዮሳፍጥ ከአባቱ ከአሳ+ ዘመን የተረፉትን የቤተ መቅደስ ቀላጮች*+ ከምድሪቱ ላይ አስወግዶ ነበር።

47 በዚያ ዘመን በኤዶም+ ንጉሥ አልነበረም፤ እንደ ንጉሥ ሆኖ የሚገዛው አስተዳዳሪው ነበር።+

48 በተጨማሪም ኢዮሳፍጥ ወርቅ ለማምጣት ወደ ኦፊር የሚሄዱ የተርሴስ መርከቦች* ሠርቶ ነበር፤+ ሆኖም መርከቦቹ በዔጽዮንጋብር+ ስለተሰበሩ ወደዚያ አልሄዱም። 49 የአክዓብ ልጅ አካዝያስ ኢዮሳፍጥን “አገልጋዮቼ ከአገልጋዮችህ ጋር በመርከቦቹ ይሂዱ” ያለው በዚህ ጊዜ ነበር፤ ኢዮሳፍጥ ግን በዚህ አልተስማማም።

50 በመጨረሻም ኢዮሳፍጥ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤+ በአባቱ በዳዊት ከተማም ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ፤ በእሱም ምትክ ልጁ ኢዮራም+ ነገሠ።

51 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ በነገሠ በ17ኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ አካዝያስ+ በሰማርያ ሆኖ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ በእስራኤልም ላይ ሁለት ዓመት ገዛ። 52 እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ማድረጉን ቀጠለ፤ በአባቱና+ በእናቱ+ መንገድ እንዲሁም እስራኤላውያን ኃጢአት እንዲፈጽሙ ባደረጋቸው በናባጥ ልጅ በኢዮርብዓም መንገድ ሄደ።+ 53 ባአልን ማገልገሉንና+ ለእሱ መስገዱን ቀጠለ፤ አባቱም እንዳደረገው ሁሉ የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን አስቆጣ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ