የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 20
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ነገሥት የመጽሐፉ ይዘት

      • ሕዝቅያስ በጠና ታሞ ዳነ (1-11)

      • ከባቢሎን የመጡ መልእክተኞች (12-19)

      • ሕዝቅያስ ሞተ (20, 21)

2 ነገሥት 20:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 32:24
  • +ኢሳ 38:1-3

2 ነገሥት 20:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 31:20, 21፤ መዝ 25:7፤ 119:49

2 ነገሥት 20:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 38:4-6

2 ነገሥት 20:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 39:12
  • +ዘዳ 32:39፤ መዝ 41:3፤ 103:3፤ 147:3
  • +መዝ 66:13፤ 116:12-14

2 ነገሥት 20:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በቀኖችህ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 32:22፤ ኢሳ 10:24
  • +2ነገ 19:34፤ ኢሳ 37:35

2 ነገሥት 20:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 38:21, 22

2 ነገሥት 20:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 6:17፤ ኢሳ 7:11

2 ነገሥት 20:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እነዚህ ደረጃዎች በፀሐይ ጥላ አማካኝነት ሰዓትን ለመቁጠር ያገለግሉ የነበረ ይመስላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 38:7, 8

2 ነገሥት 20:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 10:12፤ 2ዜና 32:31

2 ነገሥት 20:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 39:1, 2

2 ነገሥት 20:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መልእክተኞቹን ሰማቸው።”

  • *

    ወይም “በቤተ መንግሥቱም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 32:27

2 ነገሥት 20:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 39:3, 4

2 ነገሥት 20:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በቤተ መንግሥትህ።”

  • *

    ወይም “በቤተ መንግሥቴ።”

2 ነገሥት 20:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 39:5-7

2 ነገሥት 20:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በቤተ መንግሥትህ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 24:12, 13፤ 25:13፤ 2ዜና 36:7, 18፤ ኤር 27:21, 22፤ ዳን 1:2

2 ነገሥት 20:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 24:12
  • +ዳን 1:19፤ 2:49

2 ነገሥት 20:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በቀኖቼ።”

  • *

    ወይም “እውነት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 141:5
  • +ኢሳ 39:8

2 ነገሥት 20:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 9:11
  • +2ዜና 32:30

2 ነገሥት 20:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 2:10
  • +2ነገ 21:16፤ 23:26፤ 2ዜና 33:11-13
  • +2ዜና 32:33

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ነገ. 20:12ዜና 32:24
2 ነገ. 20:1ኢሳ 38:1-3
2 ነገ. 20:32ዜና 31:20, 21፤ መዝ 25:7፤ 119:49
2 ነገ. 20:4ኢሳ 38:4-6
2 ነገ. 20:5መዝ 39:12
2 ነገ. 20:5ዘዳ 32:39፤ መዝ 41:3፤ 103:3፤ 147:3
2 ነገ. 20:5መዝ 66:13፤ 116:12-14
2 ነገ. 20:62ዜና 32:22፤ ኢሳ 10:24
2 ነገ. 20:62ነገ 19:34፤ ኢሳ 37:35
2 ነገ. 20:7ኢሳ 38:21, 22
2 ነገ. 20:8መሳ 6:17፤ ኢሳ 7:11
2 ነገ. 20:9ኢሳ 38:7, 8
2 ነገ. 20:11ኢያሱ 10:12፤ 2ዜና 32:31
2 ነገ. 20:12ኢሳ 39:1, 2
2 ነገ. 20:132ዜና 32:27
2 ነገ. 20:14ኢሳ 39:3, 4
2 ነገ. 20:16ኢሳ 39:5-7
2 ነገ. 20:172ነገ 24:12, 13፤ 25:13፤ 2ዜና 36:7, 18፤ ኤር 27:21, 22፤ ዳን 1:2
2 ነገ. 20:182ነገ 24:12
2 ነገ. 20:18ዳን 1:19፤ 2:49
2 ነገ. 20:19መዝ 141:5
2 ነገ. 20:19ኢሳ 39:8
2 ነገ. 20:20ዮሐ 9:11
2 ነገ. 20:202ዜና 32:30
2 ነገ. 20:211ነገ 2:10
2 ነገ. 20:212ነገ 21:16፤ 23:26፤ 2ዜና 33:11-13
2 ነገ. 20:212ዜና 32:33
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ነገሥት 20:1-21

ሁለተኛ ነገሥት

20 በዚያ ጊዜ ሕዝቅያስ በጠና ታሞ ሞት አፋፍ ደርሶ ነበር።+ የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከሕመምህ አትድንም፤ መሞትህ ስለማይቀር ለቤተሰብህ መመሪያ ስጥ።’”+ 2 በዚህ ጊዜ ፊቱን ወደ ግድግዳው አዙሮ ወደ ይሖዋ መጸለይ ጀመረ፦ 3 “እባክህ ይሖዋ ሆይ፣ በታማኝነትና በሙሉ ልብ በፊትህ እንዴት እንደተመላለስኩ እንዲሁም በዓይኖችህ ፊት መልካም የሆነውን ነገር እንዳደረግኩ እንድታስታውስ አጥብቄ እለምንሃለሁ።”+ ሕዝቅያስም ምርር ብሎ አለቀሰ።

4 ኢሳይያስ ገና ወደ መካከለኛው ግቢ ሳይወጣ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እሱ መጣ፦+ 5 “ተመልሰህ ሂድና የሕዝቤ መሪ የሆነውን ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦ ‘የአባትህ የዳዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ጸሎትህን ሰምቻለሁ። እንባህንም አይቻለሁ።+ ስለሆነም እፈውስሃለሁ።+ በሦስተኛው ቀን ወደ ይሖዋ ቤት ትወጣለህ።+ 6 እኔም በዕድሜህ* ላይ 15 ዓመት እጨምርልሃለሁ፤ ደግሞም አንተንና ይህችን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፤+ ስለ ራሴና ስለ አገልጋዬ ስለ ዳዊት ስል ከተማዋን እጠብቃታለሁ።”’”+

7 ከዚያም ኢሳይያስ “የደረቀ የበለስ ጥፍጥፍ አምጡ” አለ። ጥፍጥፉንም አምጥተው እባጩ ላይ አደረጉለት፤ እሱም ቀስ በቀስ እየተሻለው ሄደ።+

8 ሕዝቅያስ ኢሳይያስን “ይሖዋ እንደሚፈውሰኝና በሦስተኛው ቀን ወደ ይሖዋ ቤት እንደምወጣ ማወቅ የምችልበት ምልክት ምንድን ነው?”+ ሲል ጠየቀው። 9 ኢሳይያስም መልሶ “ይሖዋ የተናገረውን ቃል እንደሚፈጽም የሚያሳየው ይሖዋ የሰጠህ ምልክት ይህ ነው፦ ጥላው በደረጃው* ላይ አሥር ደረጃ ወደ ፊት እንዲሄድ ትፈልጋለህ ወይስ አሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ?” አለው።+ 10 ሕዝቅያስም “ጥላው አሥር ደረጃ ወደ ፊት መሄዱ ቀላል ነገር ነው፤ አሥር ደረጃ ወደ ኋላ መመለሱ ግን ቀላል አይደለም” አለ። 11 ስለዚህ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ይሖዋ ጮኸ፤ እሱም በአካዝ ደረጃ ላይ ወደ ታች ወርዶ የነበረው ጥላ አሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደረገ።+

12 በዚያን ጊዜ የባላዳን ልጅ የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ቤሮዳክባላዳን ሕዝቅያስ መታመሙን ሰምቶ ስለነበር ደብዳቤና ስጦታ ላከለት።+ 13 ሕዝቅያስም ለመልእክተኞቹ ጥሩ አቀባበል አደረገላቸው፤* ከዚያም ግምጃ ቤቱን ሁሉ ይኸውም ብሩን፣ ወርቁን፣ የበለሳን ዘይቱን፣ ሌላውን ምርጥ ዘይት፣ የጦር መሣሪያውንና በግምጃ ቤቶቹ ውስጥ ያለውን ንብረት በሙሉ አሳያቸው።+ ሕዝቅያስ በቤቱም* ሆነ በግዛቱ ሁሉ ያላሳያቸው ምንም ነገር አልነበረም።

14 ከዚያ በኋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ መጥቶ “እነዚህ ሰዎች ምን አሉ? የመጡትስ ከየት ነው?” ሲል ጠየቀው። ሕዝቅያስም “የመጡት ከሩቅ አገር፣ ከባቢሎን ነው” አለው።+ 15 ቀጥሎም “በቤትህ* ያዩት ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ሕዝቅያስም “በቤቴ* ያለውን ነገር ሁሉ አይተዋል። በግምጃ ቤቶቼ ውስጥ ካለው ንብረት ሁሉ ያላሳየኋቸው ምንም ነገር የለም” ሲል መለሰለት።

16 በዚህ ጊዜ ኢሳይያስ ሕዝቅያስን እንዲህ አለው፦ “የይሖዋን ቃል ስማ፦+ 17 ‘እነሆ፣ በቤትህ* ያለው ሁሉና አባቶችህ እስካሁን ድረስ ያከማቹት ነገር ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚጋዝበት ቀን ይመጣል።+ አንድም የሚቀር ነገር አይኖርም’ ይላል ይሖዋ። 18 ‘ከአንተ ከሚወለዱት ከገዛ ልጆችህ መካከልም አንዳንዶቹ ይወሰዳሉ፤+ በባቢሎን ንጉሥ ቤተ መንግሥትም ባለሥልጣናት ይሆናሉ።’”+

19 በዚህ ጊዜ ሕዝቅያስ ኢሳይያስን “የተናገርከው የይሖዋ ቃል መልካም ነው”+ አለው። አክሎም “በእኔ የሕይወት ዘመን* ሰላምና መረጋጋት* መኖሩ መልካም ነው” አለ።+

20 የቀረው የሕዝቅያስ ታሪክ፣ ኃያልነቱ ሁሉ እንዲሁም ኩሬውንና+ ቦዩን ሠርቶ ውኃው ወደ ከተማዋ እንዲመጣ ያደረገበት መንገድ+ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ ይገኝ የለም? 21 በመጨረሻም ሕዝቅያስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤+ በእሱም ምትክ ልጁ ምናሴ+ ነገሠ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ