የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 22
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ነገሥት የመጽሐፉ ይዘት

      • ኢዮስያስ በይሁዳ ላይ ነገሠ (1, 2)

      • ቤተ መቅደሱ እንዲጠገን መመሪያ ሰጠ (3-7)

      • የሕጉ መጽሐፍ ተገኘ (8-13)

      • ሕልዳና ጥፋት እንደሚመጣ ትንቢት ተናገረች (14-20)

2 ነገሥት 22:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 13:2፤ ኤር 1:2፤ ሶፎ 1:1
  • +2ዜና 34:1, 2
  • +ኢያሱ 15:20, 39

2 ነገሥት 22:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 15:5

2 ነገሥት 22:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 34:8

2 ነገሥት 22:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 6:13
  • +2ነገ 12:4, 5, 9፤ 2ዜና 24:8፤ 34:9

2 ነገሥት 22:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ያሉትን ስንጥቆች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 12:11, 12፤ 2ዜና 34:10

2 ነገሥት 22:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 34:11

2 ነገሥት 22:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 12:15፤ 2ዜና 34:12

2 ነገሥት 22:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 22:3
  • +ዘዳ 31:24-26
  • +2ዜና 34:14, 15

2 ነገሥት 22:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 34:16-18

2 ነገሥት 22:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 31:9

2 ነገሥት 22:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 34:19-21፤ ኢዩ 2:13

2 ነገሥት 22:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:22፤ ኤር 26:24

2 ነገሥት 22:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:24፤ 29:27፤ 31:17

2 ነገሥት 22:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 15:20፤ መሳ 4:4፤ ነህ 6:14፤ ሉቃስ 2:36፤ ሥራ 21:8, 9
  • +2ዜና 34:22-28

2 ነገሥት 22:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 22:8

2 ነገሥት 22:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 2:8
  • +ዘፀ 20:3፤ ዘዳ 32:17፤ መሳ 2:12፤ ኤር 2:11
  • +ዘዳ 32:22፤ ኢሳ 33:14፤ ኤር 7:20፤ ሕዝ 20:48

2 ነገሥት 22:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ልብህ ስለለሰለሰ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 21:29፤ ያዕ 4:6
  • +2ነገ 22:11

2 ነገሥት 22:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ይህ ሞትን የሚያመለክት ቅኔያዊ አነጋገር ነው።

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ነገ. 22:11ነገ 13:2፤ ኤር 1:2፤ ሶፎ 1:1
2 ነገ. 22:12ዜና 34:1, 2
2 ነገ. 22:1ኢያሱ 15:20, 39
2 ነገ. 22:21ነገ 15:5
2 ነገ. 22:32ዜና 34:8
2 ነገ. 22:41ዜና 6:13
2 ነገ. 22:42ነገ 12:4, 5, 9፤ 2ዜና 24:8፤ 34:9
2 ነገ. 22:52ነገ 12:11, 12፤ 2ዜና 34:10
2 ነገ. 22:62ዜና 34:11
2 ነገ. 22:72ነገ 12:15፤ 2ዜና 34:12
2 ነገ. 22:82ነገ 22:3
2 ነገ. 22:8ዘዳ 31:24-26
2 ነገ. 22:82ዜና 34:14, 15
2 ነገ. 22:92ዜና 34:16-18
2 ነገ. 22:10ዘዳ 31:9
2 ነገ. 22:112ዜና 34:19-21፤ ኢዩ 2:13
2 ነገ. 22:122ነገ 25:22፤ ኤር 26:24
2 ነገ. 22:13ዘዳ 4:24፤ 29:27፤ 31:17
2 ነገ. 22:14ዘፀ 15:20፤ መሳ 4:4፤ ነህ 6:14፤ ሉቃስ 2:36፤ ሥራ 21:8, 9
2 ነገ. 22:142ዜና 34:22-28
2 ነገ. 22:162ነገ 22:8
2 ነገ. 22:17ኢሳ 2:8
2 ነገ. 22:17ዘፀ 20:3፤ ዘዳ 32:17፤ መሳ 2:12፤ ኤር 2:11
2 ነገ. 22:17ዘዳ 32:22፤ ኢሳ 33:14፤ ኤር 7:20፤ ሕዝ 20:48
2 ነገ. 22:191ነገ 21:29፤ ያዕ 4:6
2 ነገ. 22:192ነገ 22:11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ነገሥት 22:1-20

ሁለተኛ ነገሥት

22 ኢዮስያስ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ31 ዓመት ገዛ።+ እናቱ ይዲዳ ትባል ነበር፤ እሷም የቦጽቃት+ ሰው የሆነው የአዳያህ ልጅ ነበረች። 2 ኢዮስያስም በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ፤ በአባቱም በዳዊት መንገድ ሄደ፤+ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አላለም።

3 ንጉሥ ኢዮስያስ፣ በነገሠ በ18ኛው ዓመት የመሹላም ልጅ፣ የአዜልያ ልጅ የሆነውን ጸሐፊውን ሳፋንን እንዲህ ሲል ወደ ይሖዋ ቤት ላከው፦+ 4 “ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ኬልቅያስ+ ሂድ፤ በር ጠባቂዎቹ ከሕዝቡ ላይ የሰበሰቡትንና ወደ ይሖዋ ቤት የገባውን ገንዘብ በአጠቃላይ እንዲሰበስብ አድርግ።+ 5 ገንዘቡን በይሖዋ ቤት የሚከናወነውን ሥራ እንዲቆጣጠሩ ለተሾሙት ሰዎች ይስጧቸው፤ እነሱ ደግሞ በይሖዋ ቤት ውስጥ የፈረሰውን* ለሚጠግኑት ሠራተኞች ይስጡ፤+ 6 ይኸውም ለእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹ፣ ለግንባታ ባለሙያዎቹና ለግንበኞቹ ያስረክቡ፤ እነሱም ገንዘቡን ለቤቱ ጥገና የሚያስፈልጉትን ሳንቃዎችና ጥርብ ድንጋዮች ለመግዛት ይጠቀሙበታል።+ 7 ነገር ግን ሰዎቹ እምነት የሚጣልባቸው ስለሆኑ ለተሰጣቸው ገንዘብ ስሌት እንዲያቀርቡ መጠየቅ አያስፈልግም።”+

8 በኋላም ሊቀ ካህናቱ ኬልቅያስ ጸሐፊውን ሳፋንን+ “የሕጉን መጽሐፍ+ በይሖዋ ቤት ውስጥ አገኘሁት” አለው። ኬልቅያስም መጽሐፉን ለሳፋን ሰጠው፤ እሱም ያነበው ጀመር።+ 9 ከዚያም ጸሐፊው ሳፋን ወደ ንጉሡ ሄዶ “አገልጋዮችህ በቤቱ ውስጥ የተገኘውን ገንዘብ በሙሉ አውጥተው በይሖዋ ቤት የሚከናወነውን ሥራ እንዲቆጣጠሩ ለተሾሙት ሰዎች አስረክበዋል” አለው።+ 10 በተጨማሪም ጸሐፊው ሳፋን ንጉሡን “ካህኑ ኬልቅያስ የሰጠኝ አንድ መጽሐፍ+ አለ” አለው። ከዚያም ሳፋን መጽሐፉን በንጉሡ ፊት ማንበብ ጀመረ።

11 ንጉሡ የሕጉን መጽሐፍ ቃል ሲሰማ ልብሱን ቀደደ።+ 12 ከዚያም ንጉሡ ካህኑን ኬልቅያስን፣ የሳፋንን ልጅ አኪቃምን፣+ የሚካያህን ልጅ አክቦርን፣ ጸሐፊውን ሳፋንን እና የንጉሡን አገልጋይ አሳያህን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ 13 “ሄዳችሁ በተገኘው በዚህ መጽሐፍ ላይ የሰፈረውን ቃል በተመለከተ እኔን፣ ሕዝቡንና መላውን ይሁዳ ወክላችሁ ይሖዋን ጠይቁ፤ ምክንያቱም አባቶቻችን በዚህ መጽሐፍ ላይ እኛን አስመልክቶ የሰፈረውን ቃል ስላልታዘዙ የይሖዋ ታላቅ ቁጣ በእኛ ላይ ነዷል።”+

14 በመሆኑም ካህኑ ኬልቅያስ፣ አኪቃም፣ አክቦር፣ ሳፋንና አሳያህ ወደ ነቢዪቱ ሕልዳና+ ሄዱ። ሕልዳና የሃርሐስ ልጅ፣ የቲቅዋ ልጅ፣ የአልባሳት ጠባቂው የሻሉም ሚስት ስትሆን ኢየሩሳሌም ውስጥ በሁለተኛው ክፍል ትኖር ነበር፤ እነሱም በዚያ አነጋገሯት።+ 15 እሷም እንዲህ አለቻቸው፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ወደ እኔ የላካችሁን ሰው እንዲህ በሉት፦ 16 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚህ ቦታና በነዋሪዎቹ ላይ መከራ አመጣለሁ፤ የይሁዳ ንጉሥ ባነበበው መጽሐፍ+ ላይ የሰፈረውን ቃል ሁሉ እፈጽማለሁ። 17 እኔን በመተው በእጆቻቸው ሥራ+ ሁሉ ያስቆጡኝ ዘንድ ለሌሎች አማልክት የሚጨስ መሥዋዕት ስለሚያቀርቡ+ ቁጣዬ በዚህ ቦታ ላይ ይነዳል፤ ደግሞም አይጠፋም።’”+ 18 ይሖዋን እንድትጠይቁ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ ግን እንዲህ በሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የሰማኸውን ቃል በተመለከተ፣ 19 ይህን ቦታም ሆነ ነዋሪዎቹን መቀጣጫ እንደማደርግና እንደምረግም የተናገርኩትን ነገር ስትሰማ ልብህ ስለተነካ፣* በይሖዋም ፊት ራስህን ስላዋረድክ+ እንዲሁም ልብስህን ስለቀደድክና+ በፊቴ ስላለቀስክ እኔም ሰምቼሃለሁ ይላል ይሖዋ። 20 ወደ አባቶችህ የምሰበስብህ* በዚህ የተነሳ ነው፤ አንተም በሰላም በመቃብርህ ታርፋለህ፤ በዚህ ቦታ ላይ የማመጣውን መከራ ሁሉ ዓይኖችህ አያዩም።’”’” ከዚያም ሰዎቹ መልሱን ለንጉሡ አመጡለት።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ