የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ዜና መዋዕል 10
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • ሳኦልና ሦስት ወንዶች ልጆቹ ሞቱ (1-14)

1 ዜና መዋዕል 10:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 31:1-5፤ 2ሳሙ 1:21, 25

1 ዜና መዋዕል 10:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 8:33

1 ዜና መዋዕል 10:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 26:9, 10

1 ዜና መዋዕል 10:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እንዳያንገላቱኝ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 16:21, 23
  • +1ዜና 10:13

1 ዜና መዋዕል 10:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 31:6, 7

1 ዜና መዋዕል 10:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በረባዳማው ሜዳ የነበሩት።”

1 ዜና መዋዕል 10:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 28:4፤ 31:8-10

1 ዜና መዋዕል 10:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 16:23, 24

1 ዜና መዋዕል 10:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መቅደስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 5:2

1 ዜና መዋዕል 10:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 11:1
  • +1ሳሙ 31:11-13

1 ዜና መዋዕል 10:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 2:5፤ 21:12

1 ዜና መዋዕል 10:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 13:13፤ 15:22, 23
  • +ዘሌ 20:6፤ 1ሳሙ 28:7

1 ዜና መዋዕል 10:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሩት 4:17፤ 1ሳሙ 13:14፤ 15:27, 28፤ 2ሳሙ 5:3

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ዜና 10:11ሳሙ 31:1-5፤ 2ሳሙ 1:21, 25
1 ዜና 10:21ዜና 8:33
1 ዜና 10:31ሳሙ 26:9, 10
1 ዜና 10:4መሳ 16:21, 23
1 ዜና 10:41ዜና 10:13
1 ዜና 10:61ሳሙ 31:6, 7
1 ዜና 10:81ሳሙ 28:4፤ 31:8-10
1 ዜና 10:9መሳ 16:23, 24
1 ዜና 10:101ሳሙ 5:2
1 ዜና 10:111ሳሙ 11:1
1 ዜና 10:111ሳሙ 31:11-13
1 ዜና 10:122ሳሙ 2:5፤ 21:12
1 ዜና 10:131ሳሙ 13:13፤ 15:22, 23
1 ዜና 10:13ዘሌ 20:6፤ 1ሳሙ 28:7
1 ዜና 10:14ሩት 4:17፤ 1ሳሙ 13:14፤ 15:27, 28፤ 2ሳሙ 5:3
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ዜና መዋዕል 10:1-14

አንደኛ ዜና መዋዕል

10 ፍልስጤማውያንም ከእስራኤል ጋር እየተዋጉ ነበር። የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጤማውያን ፊት ሸሹ፤ ብዙዎቹም በጊልቦአ ተራራ ላይ ተገደሉ።+ 2 ፍልስጤማውያን ሳኦልንና ወንዶች ልጆቹን እግር በእግር ተከታተሏቸው፤ ፍልስጤማውያንም የሳኦልን ወንዶች ልጆች ዮናታንን፣ አቢናዳብንና ሜልኪሳን+ መተው ገደሏቸው። 3 ውጊያው በሳኦል ላይ በረታ፤ ቀስተኞቹም አገኙት፤ ደግሞም አቆሰሉት።+ 4 ከዚያም ሳኦል ጋሻ ጃግሬውን “እነዚህ ያልተገረዙ ሰዎች መጥተው በጭካኔ እንዳያሠቃዩኝ*+ ሰይፍህን መዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለነበር ፈቃደኛ አልሆነም። በመሆኑም ሳኦል ሰይፉን ወስዶ በላዩ ላይ ወድቆ ሞተ።+ 5 ጋሻ ጃግሬው ሳኦል መሞቱን ሲያይ እሱም በራሱ ሰይፍ ላይ ወድቆ ሞተ። 6 ስለዚህ ሳኦልም ሆነ ሦስት ወንዶች ልጆቹ ሞቱ፤ የቤቱም ሰዎች ሁሉ አብረው ሞቱ።+ 7 በሸለቆው ውስጥ የነበሩት* የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ሠራዊቱ መሸሹን እንዲሁም ሳኦልና ልጆቹ መሞታቸውን ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ጥለው ሸሹ፤ ከዚያም ፍልስጤማውያን መጥተው ከተሞቹን ያዙ።

8 በማግስቱ ፍልስጤማውያን የሞቱትን ሰዎች ልብስና ትጥቅ ለመግፈፍ ሲመጡ ሳኦልንና ወንዶች ልጆቹን በጊልቦአ ተራራ ላይ ወድቀው አገኟቸው።+ 9 ስለሆነም ሳኦልን ገፈፉት፤ ራሱን ከቆረጡና የጦር ትጥቁን ከወሰዱ በኋላ ወሬው ለጣዖቶቻቸውና+ ለሕዝቡ እንዲዳረስ ወደ ፍልስጤም ምድር ሁሉ መልእክት ላኩ። 10 ከዚያም የጦር ትጥቁን በአምላካቸው ቤት* አስቀመጡት፤ ራሱን ደግሞ በዳጎን ቤት+ ላይ ቸነከሩት።

11 በጊልያድ በምትገኘው በኢያቢስ+ የሚኖሩ ሰዎች በሙሉ ፍልስጤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን ሁሉ ሲሰሙ+ 12 ተዋጊዎቹ ሁሉ ተነሱ፤ የሳኦልንና የልጆቹንም አስከሬን ተሸክመው ወደ ኢያቢስ አመጡ። ከዚያም አፅማቸውን በኢያቢስ በሚገኝ ትልቅ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤+ ለሰባት ቀንም ጾሙ።

13 ስለዚህ ሳኦል ለይሖዋ ታማኝ ሳይሆን በመቅረቱ ሞተ፤ ምክንያቱም የይሖዋን ቃል አልታዘዘም፤+ ደግሞም መናፍስት ጠሪን አማከረ፤+ 14 ይሖዋንም አልጠየቀም። ስለሆነም ለሞት አሳልፎ ሰጠው፤ ንግሥናውም ለእሴይ ልጅ ለዳዊት እንዲተላለፍ አደረገ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ