የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ዜና መዋዕል 24
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • ዳዊት፣ ካህናቱ በ24 ቡድኖች እንዲደራጁ አደረገ (1-19)

      • የቀሩት ሌዋውያን (20-31)

1 ዜና መዋዕል 24:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 10:1
  • +ዘፀ 6:23፤ 28:1

1 ዜና መዋዕል 24:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 26:61
  • +ዘኁ 16:39, 40

1 ዜና መዋዕል 24:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 8:17

1 ዜና መዋዕል 24:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 16:33

1 ዜና መዋዕል 24:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 2:35
  • +2ሳሙ 19:11፤ 1ነገ 1:5, 7
  • +2ሳሙ 8:17

1 ዜና መዋዕል 24:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 1:5

1 ዜና መዋዕል 24:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 11:9፤ ሉቃስ 1:8, 23

1 ዜና መዋዕል 24:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 6:18
  • +1ዜና 23:16፤ 26:24

1 ዜና መዋዕል 24:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 23:17

1 ዜና መዋዕል 24:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 23:18

1 ዜና መዋዕል 24:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 26:31

1 ዜና መዋዕል 24:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 46:11

1 ዜና መዋዕል 24:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 23:22

1 ዜና መዋዕል 24:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 16:33

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ዜና 24:1ዘሌ 10:1
1 ዜና 24:1ዘፀ 6:23፤ 28:1
1 ዜና 24:2ዘኁ 26:61
1 ዜና 24:2ዘኁ 16:39, 40
1 ዜና 24:32ሳሙ 8:17
1 ዜና 24:5ምሳሌ 16:33
1 ዜና 24:61ነገ 2:35
1 ዜና 24:62ሳሙ 19:11፤ 1ነገ 1:5, 7
1 ዜና 24:62ሳሙ 8:17
1 ዜና 24:10ሉቃስ 1:5
1 ዜና 24:192ነገ 11:9፤ ሉቃስ 1:8, 23
1 ዜና 24:20ዘፀ 6:18
1 ዜና 24:201ዜና 23:16፤ 26:24
1 ዜና 24:211ዜና 23:17
1 ዜና 24:221ዜና 23:18
1 ዜና 24:231ዜና 26:31
1 ዜና 24:26ዘፍ 46:11
1 ዜና 24:281ዜና 23:22
1 ዜና 24:31ምሳሌ 16:33
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ዜና መዋዕል 24:1-31

አንደኛ ዜና መዋዕል

24 የአሮን ዘሮች ምድብ ይህ ነበር፦ የአሮን ወንዶች ልጆች ናዳብ፣ አቢሁ፣+ አልዓዛር እና ኢታምር+ ነበሩ። 2 ይሁንና ናዳብ እና አቢሁ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤+ ወንዶች ልጆችም አልነበሯቸውም፤ አልዓዛር+ እና ኢታምር ግን ካህናት ሆነው ማገልገላቸውን ቀጠሉ። 3 ዳዊት፣ ከአልዓዛር ወንዶች ልጆች አንዱ ከሆነው ከሳዶቅ+ እንዲሁም ከኢታምር ወንዶች ልጆች አንዱ ከሆነው ከአሂሜሌክ ጋር ሆኖ የአሮንን ዘሮች በተሰጣቸው የአገልግሎት ኃላፊነት መሠረት መደባቸው። 4 የአልዓዛር ወንዶች ልጆች፣ ከኢታምር ወንዶች ልጆች ይልቅ ብዙ መሪዎች ስለነበሯቸው መሪዎቹን በዚሁ መሠረት መደቧቸው፦ የአልዓዛር ወንዶች ልጆች የየአባቶቻቸው ቤት መሪዎች የሆኑ 16 መሪዎች፣ የኢታምር ወንዶች ልጆች ደግሞ የየአባቶቻቸው ቤት መሪዎች የሆኑ 8 መሪዎች ነበሯቸው።

5 በተጨማሪም ከአልዓዛር ወንዶች ልጆችም ሆነ ከኢታምር ወንዶች ልጆች መካከል በቅዱሱ ስፍራ የሚያገለግሉ አለቆችና እውነተኛውን አምላክ የሚያገለግሉ አለቆች ስለነበሩ አንደኛውን ቡድን ከሌላው ቡድን ጋር በዕጣ+ መደቧቸው። 6 ከዚያም የሌዋውያን ጸሐፊ የሆነው የናትናኤል ልጅ ሸማያህ በንጉሡ፣ በመኳንንቱ፣ በካህኑ በሳዶቅ፣+ በአብያታር+ ልጅ በአሂሜሌክ+ እንዲሁም በካህናቱና በሌዋውያኑ አባቶች ቤት መሪዎች ፊት ስማቸውን መዘገበ፤ አንድ የአባቶች ቤት ከአልዓዛር ወገን ሲመረጥ፣ አንድ የአባቶች ቤት ደግሞ ከኢታምር ወገን ተመረጠ።

7 የመጀመሪያው ዕጣ ለየሆያሪብ ወጣ፤ ሁለተኛው ለየዳያህ፣ 8 ሦስተኛው ለሃሪም፣ አራተኛው ለሰኦሪም፣ 9 አምስተኛው ለማልኪያህ፣ ስድስተኛው ለሚያሚን፣ 10 ሰባተኛው ለሃቆጽ፣ ስምንተኛው ለአቢያህ፣+ 11 ዘጠነኛው ለየሹዋ፣ አሥረኛው ለሸካንያህ፣ 12 አሥራ አንደኛው ለኤልያሺብ፣ አሥራ ሁለተኛው ለያቂም፣ 13 አሥራ ሦስተኛው ለሁፓ፣ አሥራ አራተኛው ለየሼብአብ፣ 14 አሥራ አምስተኛው ለቢልጋ፣ አሥራ ስድስተኛው ለኢሜር፣ 15 አሥራ ሰባተኛው ለሄዚር፣ አሥራ ስምንተኛው ለሃፒጼጽ፣ 16 አሥራ ዘጠነኛው ለፐታያህ፣ ሃያኛው ለየሄዝቄል፣ 17 ሃያ አንደኛው ለያኪን፣ ሃያ ሁለተኛው ለጋሙል፣ 18 ሃያ ሦስተኛው ለደላያህ እና ሃያ አራተኛው ለማአዝያህ ወጣ።

19 የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት አባታቸው አሮን ወደ ይሖዋ ቤት ሲገቡ የአገልግሎት ኃላፊነታቸውን+ የሚያከናውኑበትን ሥርዓት በተመለከተ ያወጣው ደንብ ይህ ነበር።

20 ከቀሩት ሌዋውያን መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ ከአምራም+ ወንዶች ልጆች መካከል ሹባኤል፤+ ከሹባኤል ወንዶች ልጆች መካከል የህድያ፤ 21 ከረሃቢያህ፦+ ከረሃቢያህ ወንዶች ልጆች መካከል፣ መሪ የሆነው ይሽሺያህ፤ 22 ከይጽሃራውያን መካከል ሸሎሞት፤+ ከሸሎሞት ወንዶች ልጆች መካከል ያሃት፤ 23 ከኬብሮን ወንዶች ልጆች መካከል፣ መሪ የሆነው የሪያ፣+ ሁለተኛው አማርያህ፣ ሦስተኛው ያሃዚኤል እና አራተኛው የቃምአም፤ 24 ከዑዚኤል ወንዶች ልጆች መካከል ሚክያስ፤ ከሚክያስ ወንዶች ልጆች መካከል ሻሚር። 25 ይሽሺያህ የሚክያስ ወንድም ነበር፤ ከይሽሺያህ ወንዶች ልጆች መካከል ዘካርያስ።

26 የሜራሪ+ ወንዶች ልጆች ማህሊ እና ሙሺ ነበሩ፤ የያአዚያሁ ልጅ ቤኖ። 27 የሜራሪ ወንዶች ልጆች፦ ከያአዚያሁ ልጆች መካከል ቤኖ፣ ሾሃም፣ ዛኩር እና ኢብሪ፤ 28 ከማህሊ ልጆች መካከል አልዓዛር፤ እሱ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤+ 29 ከቂስ፦ የቂስ ልጅ የራህምኤል፤ 30 የሙሺ ወንዶች ልጆች ማህሊ፣ ኤዴር እና የሪሞት ነበሩ።

በአባቶቻቸው ቤት መሠረት የተዘረዘሩት የሌዊ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ። 31 እነሱም ወንድሞቻቸው የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆች እንዳደረጉት በንጉሥ ዳዊት፣ በሳዶቅ፣ በአሂሜሌክ እንዲሁም በካህናቱና በሌዋውያኑ አባቶች ቤት መሪዎች ፊት ዕጣ+ ጣሉ። በዚህ ረገድ በመሪው አባት ቤት ወይም በትልቁ ቤተሰብ መሪና በታናሽ ወንድሙ አባት ቤት ወይም በአነስተኛው ቤተሰብ መሪ መካከል ምንም ልዩነት አልነበረም።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ