የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • ሰለሞን ጥበብ እንዲሰጠው ጠየቀ (1-12)

      • የሰለሞን ሀብት (13-17)

2 ዜና መዋዕል 1:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 29:25፤ መክ 2:9፤ ማቴ 6:28, 29፤ 12:42

2 ዜና መዋዕል 1:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 3:4፤ 1ዜና 21:29

2 ዜና መዋዕል 1:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 13:5
  • +1ዜና 16:1

2 ዜና መዋዕል 1:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በዚያ አምላክን ይጠይቁ ነበር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 31:2-5
  • +ዘፀ 38:1, 2

2 ዜና መዋዕል 1:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 3:4

2 ዜና መዋዕል 1:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 3:5-9

2 ዜና መዋዕል 1:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 7:8
  • +1ዜና 28:5፤ መዝ 89:28, 29

2 ዜና መዋዕል 1:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 7:12፤ 1ዜና 28:6፤ መዝ 132:11
  • +ዘፍ 13:14, 16

2 ዜና መዋዕል 1:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በዚህ ሕዝብ ፊት መውጣትና መግባት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 2:6፤ ያዕ 1:5
  • +መዝ 72:1, 2

2 ዜና መዋዕል 1:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

  • *

    ቃል በቃል “ብዙ ቀናት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 3:10-13, 28

2 ዜና መዋዕል 1:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 29:25፤ 2ዜና 9:22፤ መክ 2:9

2 ዜና መዋዕል 1:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 3:4

2 ዜና መዋዕል 1:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ፈረሰኞችን።”

  • *

    ወይም “ፈረሰኞች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 17:16፤ 1ነገ 4:26
  • +2ዜና 8:5, 6
  • +2ዜና 9:25

2 ዜና መዋዕል 1:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 10:21
  • +1ነገ 10:27፤ 2ዜና 9:27

2 ዜና መዋዕል 1:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ከግብፅና ከቀዌ ያስመጣቸው ነበሩ፤ የንጉሡ ነጋዴዎች ከቀዌ አንዴ በተተመነው ዋጋ ይገዟቸው ነበር” ማለትም ሊሆን ይችላል። ቀዌ ኪልቅያን ልታመለክት ትችላለች።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 9:28
  • +1ነገ 10:28, 29

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ዜና 1:11ዜና 29:25፤ መክ 2:9፤ ማቴ 6:28, 29፤ 12:42
2 ዜና 1:31ነገ 3:4፤ 1ዜና 21:29
2 ዜና 1:41ዜና 13:5
2 ዜና 1:41ዜና 16:1
2 ዜና 1:5ዘፀ 31:2-5
2 ዜና 1:5ዘፀ 38:1, 2
2 ዜና 1:61ነገ 3:4
2 ዜና 1:71ነገ 3:5-9
2 ዜና 1:82ሳሙ 7:8
2 ዜና 1:81ዜና 28:5፤ መዝ 89:28, 29
2 ዜና 1:92ሳሙ 7:12፤ 1ዜና 28:6፤ መዝ 132:11
2 ዜና 1:9ዘፍ 13:14, 16
2 ዜና 1:10ምሳሌ 2:6፤ ያዕ 1:5
2 ዜና 1:10መዝ 72:1, 2
2 ዜና 1:111ነገ 3:10-13, 28
2 ዜና 1:121ዜና 29:25፤ 2ዜና 9:22፤ መክ 2:9
2 ዜና 1:131ነገ 3:4
2 ዜና 1:14ዘዳ 17:16፤ 1ነገ 4:26
2 ዜና 1:142ዜና 8:5, 6
2 ዜና 1:142ዜና 9:25
2 ዜና 1:151ነገ 10:21
2 ዜና 1:151ነገ 10:27፤ 2ዜና 9:27
2 ዜና 1:162ዜና 9:28
2 ዜና 1:161ነገ 10:28, 29
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ዜና መዋዕል 1:1-17

ሁለተኛ ዜና መዋዕል

1 የዳዊት ልጅ ሰለሞን ንግሥናውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጠናከረ ሄደ፤ አምላኩ ይሖዋም ከእሱ ጋር ስለነበር እጅግ ገናና አደረገው።+

2 ሰለሞን ለእስራኤል ሁሉ፣ ለሺህ አለቆች፣ ለመቶ አለቆች፣ ለፈራጆችና የአባቶች ቤቶች መሪዎች ለሆኑት በመላው እስራኤል ለሚገኙት አለቆች ሁሉ መልእክት ላከ። 3 ከዚያም ሰለሞንና መላው ጉባኤ በገባኦን+ ወደሚገኘው ኮረብታ ሄዱ፤ ምክንያቱም የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የእውነተኛው አምላክ የመገናኛ ድንኳን የሚገኘው በዚያ ነበር። 4 ይሁን እንጂ ዳዊት የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ከቂርያትየአሪም+ እሱ ወዳዘጋጀለት ስፍራ አምጥቶት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ድንኳን ተክሎለት ነበር።+ 5 የሁር ልጅ የዖሪ ልጅ ባስልኤል+ የሠራው የመዳብ መሠዊያ+ በይሖዋ የማደሪያ ድንኳን ፊት ይገኝ ነበር፤ ሰለሞንና ጉባኤውም በመሠዊያው ፊት ይጸልዩ ነበር።* 6 ሰለሞንም በዚያ በይሖዋ ፊት መባ አቀረበ፤ በመገናኛው ድንኳን በሚገኘው የመዳብ መሠዊያ ላይ 1,000 የሚቃጠሉ መባዎችን አቀረበ።+

7 በዚያ ሌሊት አምላክ ለሰለሞን ተገልጦ “እንድሰጥህ የምትፈልገውን ጠይቅ” አለው።+ 8 በዚህ ጊዜ ሰለሞን አምላክን እንዲህ አለው፦ “ለአባቴ ለዳዊት ጥልቅ የሆነ ታማኝ ፍቅር አሳይተኸዋል፤+ በእሱም ምትክ አንግሠኸኛል።+ 9 አሁንም ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ ለአባቴ ለዳዊት የገባኸው ቃል ይፈጸም፤+ እንደ ምድር አፈር እጅግ ብዙ በሆነ ሕዝብ+ ላይ አንግሠኸኛልና። 10 ይህን ሕዝብ መምራት* እንድችል ጥበብና እውቀት ስጠኝ፤+ አለዚያማ ይህን ታላቅ ሕዝብህን ማን ሊዳኝ ይችላል?”+

11 ከዚያም አምላክ ሰለሞንን እንዲህ አለው፦ “የልብህ መሻት ይህ ስለሆነ ደግሞም ብልጽግና፣ ሀብትና ክብር ወይም የሚጠሉህን ሰዎች ሞት* አሊያም ረጅም ዕድሜ* ስላልተመኘህ፣ ይልቁንም አንተን ንጉሥ አድርጌ የሾምኩበትን ሕዝቤን ማስተዳደር እንድትችል ጥበብና እውቀት ስለጠየቅክ፣+ 12 ጥበብና እውቀት ይሰጥሃል፤ ከዚህም ሌላ ከአንተ በፊት የነበረ ማንኛውም ንጉሥ ያላገኘውን፣ ከአንተም በኋላ የሚነሳ የትኛውም ንጉሥ የማያገኘውን ብልጽግና፣ ሀብትና ክብር እሰጥሃለሁ።”+

13 ሰለሞንም በገባኦን+ ኮረብታ ከሚገኘው ከመገናኛው ድንኳን ፊት ወጥቶ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ በእስራኤልም ላይ ነገሠ። 14 ሰለሞን ሠረገሎችንና ፈረሶችን* መሰብሰቡን ቀጠለ፤ እሱም 1,400 ሠረገሎችና 12,000 ፈረሶች* ነበሩት፤+ እነሱንም በሠረገላ ከተሞችና+ በኢየሩሳሌም በንጉሡ አቅራቢያ አኖራቸው።+ 15 ንጉሡ ብርና ወርቅ በየቦታው እንደሚገኝ ድንጋይ እስኪሆን ድረስ በኢየሩሳሌም እንዲበዛ አደረገ፤+ አርዘ ሊባኖሱንም ከብዛቱ የተነሳ በሸፌላ እንደሚገኘው የሾላ ዛፍ አደረገው።+ 16 የሰለሞን ፈረሶች ከግብፅ ያስመጣቸው ነበሩ፤+ የንጉሡ ነጋዴዎችም የፈረሶቹን መንጋ አንዴ በተተመነው ዋጋ ይገዙ ነበር።*+ 17 ከግብፅ የሚመጣው እያንዳንዱ ሠረገላ 600 የብር ሰቅል ያወጣ ነበር፤ አንድ ፈረስ ደግሞ 150 ሰቅል ያወጣል፤ እነሱ ደግሞ በተራቸው ለሂታውያን ነገሥታትና ለሶርያ ነገሥታት ሁሉ ሠረገሎችንና ፈረሶችን ይሸጡ ነበር።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ