የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 15
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • አሳ ያካሄደው ተሃድሶ (1-19)

2 ዜና መዋዕል 15:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ያዕ 4:8
  • +ኢሳ 55:6
  • +1ዜና 28:9፤ ዕብ 10:38

2 ዜና መዋዕል 15:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ብዙ ቀናት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 33:8, 10፤ 2ዜና 17:8, 9፤ ሚል 2:7

2 ዜና መዋዕል 15:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 106:43, 44፤ ኢሳ 55:7

2 ዜና መዋዕል 15:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የሚወጣውም ሆነ የሚገባው ሰላም አልነበረውም።”

2 ዜና መዋዕል 15:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:15, 48

2 ዜና መዋዕል 15:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እጆቻችሁ አይዛሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 1:9፤ 1ዜና 28:20

2 ዜና መዋዕል 15:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 23:24
  • +2ዜና 8:12

2 ዜና መዋዕል 15:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 11:16፤ 30:25

2 ዜና መዋዕል 15:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:29፤ 2ነገ 23:3፤ ነህ 10:28, 29

2 ዜና መዋዕል 15:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 22:20

2 ዜና መዋዕል 15:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 15:2
  • +ምሳሌ 16:7

2 ዜና መዋዕል 15:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

  • *

    ወይም “እንደ ንጉሡ እናት ተቆጥራ ከተሰጣት ቦታ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 15:9, 10
  • +ዘዳ 13:6-9
  • +1ነገ 15:13, 14

2 ዜና መዋዕል 15:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በቀናቱ።”

  • *

    ወይም “ሙሉ በሙሉ ለአምላክ ያደረ ነበር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 14:22, 23፤ 22:43፤ 2ነገ 14:3, 4፤ 23:19, 20
  • +1ነገ 8:61

2 ዜና መዋዕል 15:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 7:51፤ 15:15፤ 1ዜና 26:26

2 ዜና መዋዕል 15:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 14:1

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ዜና 15:2ያዕ 4:8
2 ዜና 15:2ኢሳ 55:6
2 ዜና 15:21ዜና 28:9፤ ዕብ 10:38
2 ዜና 15:3ዘዳ 33:8, 10፤ 2ዜና 17:8, 9፤ ሚል 2:7
2 ዜና 15:4መዝ 106:43, 44፤ ኢሳ 55:7
2 ዜና 15:6ዘዳ 28:15, 48
2 ዜና 15:7ኢያሱ 1:9፤ 1ዜና 28:20
2 ዜና 15:82ነገ 23:24
2 ዜና 15:82ዜና 8:12
2 ዜና 15:92ዜና 11:16፤ 30:25
2 ዜና 15:12ዘዳ 4:29፤ 2ነገ 23:3፤ ነህ 10:28, 29
2 ዜና 15:13ዘፀ 22:20
2 ዜና 15:152ዜና 15:2
2 ዜና 15:15ምሳሌ 16:7
2 ዜና 15:161ነገ 15:9, 10
2 ዜና 15:16ዘዳ 13:6-9
2 ዜና 15:161ነገ 15:13, 14
2 ዜና 15:171ነገ 14:22, 23፤ 22:43፤ 2ነገ 14:3, 4፤ 23:19, 20
2 ዜና 15:171ነገ 8:61
2 ዜና 15:181ነገ 7:51፤ 15:15፤ 1ዜና 26:26
2 ዜና 15:192ዜና 14:1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ዜና መዋዕል 15:1-19

ሁለተኛ ዜና መዋዕል

15 የአምላክ መንፈስ በኦዴድ ልጅ በአዛርያስ ላይ ወረደ። 2 እሱም ከአሳ ጋር ለመገናኘት ወጥቶ እንዲህ አለው፦ “አሳ ሆይ፣ ይሁዳና ቢንያም ሁሉ ስሙኝ! እናንተ ከእሱ ጋር እስከሆናችሁ ድረስ ይሖዋ ከእናንተ ጋር ይሆናል፤+ ብትፈልጉት ይገኝላችኋል፤+ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል።+ 3 እስራኤል ያለእውነተኛው አምላክ፣ ያለአስተማሪ ካህንና ያለሕግ ብዙ ዘመን* አሳልፏል።+ 4 በተጨነቁ ጊዜ ግን ወደ እስራኤል አምላክ ወደ ይሖዋ ተመልሰው ፈለጉት፤ እሱም ተገኘላቸው።+ 5 በዚያ ዘመን በሰላም መጓዝ የሚችል ሰው አልነበረም፤* ምክንያቱም በየክልሉ በሚኖሩት ሰዎች ሁሉ መካከል ከፍተኛ ሁከት ነበር። 6 አምላክ በተለያየ ችግር ያውካቸው ስለነበር አንዱ ብሔር ሌላውን ብሔር፣ አንዱ ከተማም ሌላውን ከተማ ያደቅ ነበር።+ 7 እናንተ ግን የድካማችሁን ዋጋ ስለምታገኙ በርቱ፤ ተስፋም አትቁረጡ።”*+

8 አሳ ይህን ቃልና ነቢዩ ኦዴድ የተናገረውን ትንቢት ሲሰማ ተበረታታ፤ አስጸያፊ የሆኑትን ጣዖቶችም ከይሁዳና ከቢንያም ምድር ሁሉ እንዲሁም በተራራማው የኤፍሬም ክልል ከያዛቸው ከተሞች አስወገደ፤+ ከይሖዋ ቤት በረንዳ ፊት ለፊት የነበረውን የይሖዋን መሠዊያም አደሰ።+ 9 እሱም ይሁዳንና ቢንያምን ሁሉ እንዲሁም ከኤፍሬም፣ ከምናሴና ከስምዖን መጥተው ከእነሱ ጋር የተቀመጡትን የባዕድ አገር ሰዎች ሰበሰበ፤+ አምላኩ ይሖዋ ከእሱ ጋር እንደሆነ ባዩ ጊዜ በርካታ የባዕድ አገር ሰዎች እስራኤልን ትተው ወደ እሱ መጥተው ነበር። 10 በመሆኑም አሳ በነገሠ በ15ኛው ዓመት፣ በሦስተኛው ወር በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። 11 በዚያም ቀን፣ ካመጡት ምርኮ ላይ 700 ከብቶችንና 7,000 በጎችን ለይሖዋ መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ። 12 በተጨማሪም የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው* ለመፈለግ ቃል ኪዳን ገቡ።+ 13 የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን የማይፈልግ ማንኛውም ሰው ትንሽም ሆነ ትልቅ፣ ወንድም ሆነ ሴት እንዲገደል ተስማሙ።+ 14 በታላቅ ድምፅ፣ በእልልታ፣ በመለከትና በቀንደ መለከት ለይሖዋ ማሉ። 15 የይሁዳ ሰዎች ሁሉ በሙሉ ልባቸው ስለማሉ በመሐላው ሐሴት አደረጉ፤ አምላክንም ከልባቸው ፈለጉት፤ እሱም ተገኘላቸው፤+ ይሖዋም በዙሪያቸው ካሉት ጠላቶቻቸው እረፍት ሰጣቸው።+

16 ሌላው ቀርቶ ንጉሥ አሳ አያቱ ማአካ+ ለማምለኪያ ግንዱ* አምልኮ ጸያፍ ጣዖት ሠርታ ስለነበር ከእመቤትነቷ* ሻራት።+ ከዚያም አሳ፣ አያቱ የሠራችውን ጸያፍ ጣዖት ቆርጦ በማድቀቅ በቄድሮን ሸለቆ አቃጠለው።+ 17 ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች ግን ከእስራኤል አልተወገዱም ነበር።+ ይሁንና አሳ በሕይወት ዘመኑ* ሁሉ በሙሉ ልቡ ተመላልሷል።*+ 18 እሱና አባቱ የቀደሷቸውን ነገሮች ይኸውም ብሩን፣ ወርቁንና ልዩ ልዩ ዕቃዎችን ወደ እውነተኛው አምላክ ቤት አስገባ።+ 19 እስከ 35ኛው የአሳ ዘመነ መንግሥት ድረስ ጦርነት አልነበረም።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ