የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 21
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • ኢዮራም በይሁዳ ላይ ነገሠ (1-11)

      • ኤልያስ የላከው የጽሑፍ መልእክት (12-15)

      • የኢዮራም መጥፎ አወዳደቅ (16-20)

2 ዜና መዋዕል 21:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 22:50

2 ዜና መዋዕል 21:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 11:5, 23
  • +2ነገ 8:16

2 ዜና መዋዕል 21:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 9:5, 6

2 ዜና መዋዕል 21:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 8:17-19

2 ዜና መዋዕል 21:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 22:2፤ ነህ 13:26
  • +1ነገ 14:7, 9፤ ሆሴዕ 4:1

2 ዜና መዋዕል 21:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “መብራት” የሚለው ቃል ከዳዊት ቤት የሆነን ንጉሥ ወይም የእሱን ሥርወ መንግሥት ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 23:5፤ መዝ 89:20, 28፤ ኤር 33:20, 21
  • +2ሳሙ 7:12, 16፤ 1ነገ 11:36፤ መዝ 132:11

2 ዜና መዋዕል 21:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 27:40
  • +1ነገ 22:47፤ 2ነገ 8:20-22

2 ዜና መዋዕል 21:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 21:13፤ 2ነገ 19:8
  • +2ዜና 15:2፤ ኤር 2:13

2 ዜና መዋዕል 21:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 12:2

2 ዜና መዋዕል 21:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 2:1, 11
  • +2ዜና 17:3
  • +1ነገ 15:11፤ 2ዜና 14:2, 5

2 ዜና መዋዕል 21:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 16:25, 33
  • +2ነገ 9:22
  • +ዘፀ 34:15፤ ኤር 3:8
  • +2ዜና 21:4

2 ዜና መዋዕል 21:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የፍልስጤማውያንንና በኢትዮጵያውያን አቅራቢያ የሚኖሩትን ዓረቦች መንፈስ በኢዮራም ላይ አነሳሳ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 13:1, 2፤ 2ሳሙ 8:1
  • +2ዜና 17:11
  • +1ነገ 11:14፤ 2ዜና 33:11፤ ኢሳ 10:5

2 ዜና መዋዕል 21:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

  • *

    አካዝያስ ተብሎም ይጠራል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 14:25, 26
  • +2ዜና 22:1

2 ዜና መዋዕል 21:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 12:21-23

2 ዜና መዋዕል 21:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 16:13, 14፤ ኤር 34:4, 5

2 ዜና መዋዕል 21:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 24:24, 25፤ 28:27
  • +1ነገ 2:10

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ዜና 21:11ነገ 22:50
2 ዜና 21:32ዜና 11:5, 23
2 ዜና 21:32ነገ 8:16
2 ዜና 21:4መሳ 9:5, 6
2 ዜና 21:52ነገ 8:17-19
2 ዜና 21:62ዜና 22:2፤ ነህ 13:26
2 ዜና 21:61ነገ 14:7, 9፤ ሆሴዕ 4:1
2 ዜና 21:72ሳሙ 23:5፤ መዝ 89:20, 28፤ ኤር 33:20, 21
2 ዜና 21:72ሳሙ 7:12, 16፤ 1ነገ 11:36፤ መዝ 132:11
2 ዜና 21:8ዘፍ 27:40
2 ዜና 21:81ነገ 22:47፤ 2ነገ 8:20-22
2 ዜና 21:10ኢያሱ 21:13፤ 2ነገ 19:8
2 ዜና 21:102ዜና 15:2፤ ኤር 2:13
2 ዜና 21:11ዘዳ 12:2
2 ዜና 21:122ነገ 2:1, 11
2 ዜና 21:122ዜና 17:3
2 ዜና 21:121ነገ 15:11፤ 2ዜና 14:2, 5
2 ዜና 21:131ነገ 16:25, 33
2 ዜና 21:132ነገ 9:22
2 ዜና 21:13ዘፀ 34:15፤ ኤር 3:8
2 ዜና 21:132ዜና 21:4
2 ዜና 21:16ኢያሱ 13:1, 2፤ 2ሳሙ 8:1
2 ዜና 21:162ዜና 17:11
2 ዜና 21:161ነገ 11:14፤ 2ዜና 33:11፤ ኢሳ 10:5
2 ዜና 21:171ነገ 14:25, 26
2 ዜና 21:172ዜና 22:1
2 ዜና 21:18ሥራ 12:21-23
2 ዜና 21:192ዜና 16:13, 14፤ ኤር 34:4, 5
2 ዜና 21:202ዜና 24:24, 25፤ 28:27
2 ዜና 21:201ነገ 2:10
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ዜና መዋዕል 21:1-20

ሁለተኛ ዜና መዋዕል

21 በመጨረሻም ኢዮሳፍጥ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማም ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ፤ በእሱም ምትክ ልጁ ኢዮራም ነገሠ።+ 2 የኢዮሳፍጥ ልጆች የሆኑት ወንድሞቹ አዛርያስ፣ የሂኤል፣ ዘካርያስ፣ አዛርያስ፣ ሚካኤል እና ሰፋጥያህ ነበሩ፤ እነዚህ ሁሉ የእስራኤል ንጉሥ የኢዮሳፍጥ ወንዶች ልጆች ናቸው። 3 አባታቸውም ብዙ ብር፣ ወርቅና ውድ የሆኑ ነገሮች ስጦታ አድርጎ የሰጣቸው ከመሆኑም በላይ በይሁዳ የተመሸጉ ከተሞችን ሰጣቸው፤+ መንግሥቱን ግን የበኩር ልጁ ለነበረው ለኢዮራም+ ሰጠው።

4 ኢዮራም በአባቱ መንግሥት ላይ ተደላድሎ በተቀመጠ ጊዜ ወንድሞቹን በሙሉ እንዲሁም ከእስራኤል መኳንንት መካከል የተወሰኑትን በሰይፍ በመግደል ሥልጣኑን አጠናከረ።+ 5 ኢዮራም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 32 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ስምንት ዓመት ገዛ።+ 6 የአክዓብን ልጅ አግብቶ+ ስለነበር ከአክዓብ ቤት የሆኑት እንዳደረጉት ሁሉ እሱም በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤+ በይሖዋም ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ። 7 ሆኖም ይሖዋ ከዳዊት ጋር ለገባው ቃል ኪዳን ሲል የዳዊትን ቤት ማጥፋት አልፈለገም፤+ ምክንያቱም ለእሱና ለልጆቹ ለሁልጊዜ የሚኖር መብራት* እንደሚሰጥ ቃል ገብቶ ነበር።+

8 በእሱ ዘመን ኤዶም በይሁዳ ላይ ዓምፆ+ የራሱን ንጉሥ አነገሠ።+ 9 በመሆኑም ኢዮራም ከአዛዦቹ ጋር ሠረገሎቹን ሁሉ ይዞ ተሻገረ፤ በሌሊትም ተነስቶ እሱንና የሠረገሎቹን አዛዦች ከበው የነበሩትን ኤዶማውያን ድል አደረገ። 10 ሆኖም ኤዶም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ላይ እንዳመፀ ነው። ሊብናም+ በዚሁ ጊዜ በእሱ ላይ ዓመፀ፤ ምክንያቱም ኢዮራም የአባቶቹን አምላክ ይሖዋን ትቶ ነበር።+ 11 ደግሞም በይሁዳ ተራሮች ላይ ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችን ሠርቶ+ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች መንፈሳዊ ምንዝር እንዲፈጽሙ አደረገ፤ ይሁዳንም አሳተ።

12 በመጨረሻም ነቢዩ ኤልያስ እንዲህ የሚል መልእክት በጽሑፍ ላከለት፦+ “የአባትህ የዳዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በአባትህ በኢዮሳፍጥ+ ወይም በይሁዳ ንጉሥ በአሳ+ መንገድ አልሄድክም። 13 ይልቁንም በእስራኤል ነገሥታት መንገድ በመሄድ፣+ ይሁዳና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የአክዓብ ቤት የፈጸመውን ምንዝር+ የሚመስል መንፈሳዊ ምንዝር እንዲፈጽሙ አድርገሃል፤+ ከዚህም በላይ ከአንተ ይሻሉ የነበሩትን የአባትህ ቤት ልጆች የሆኑትን የገዛ ወንድሞችህን ገድለሃል።+ 14 ስለዚህ ይሖዋ ሕዝብህን፣ ልጆችህን፣ ሚስቶችህንና ንብረትህን ሁሉ በታላቅ መቅሰፍት ይመታል። 15 አንተም የአንጀት በሽታን ጨምሮ በብዙ ሕመም ትሠቃያለህ፤ ከበሽታው የተነሳ አንጀትህ እስኪወጣ ድረስ ሕመሙ ዕለት ተዕለት እየጠናብህ ይሄዳል።’”

16 ከዚያም ይሖዋ ፍልስጤማውያንና+ በኢትዮጵያውያን አቅራቢያ የሚኖሩት ዓረቦች+ በኢዮራም ላይ እንዲነሱ አደረገ።*+ 17 እነሱም ይሁዳን ወረሩ፤ በኃይል ጥሰው በመግባትም በንጉሡ ቤት* ያገኙትን ንብረት ሁሉ+ እንዲሁም ልጆቹንና ሚስቶቹን ማርከው ወሰዱ፤ ከመጨረሻው ልጁ ከኢዮዓካዝ*+ በቀር አንድም ልጅ አልቀረለትም። 18 ከዚህ ሁሉ በኋላ ይሖዋ በማይድን የአንጀት በሽታ ቀሰፈው።+ 19 ድፍን ሁለት ዓመት ከታመመ በኋላም ሕመሙ ጠንቶበት አንጀቱ ወጣ፤ በበሽታውም እጅግ ሲሠቃይ ቆይቶ በመጨረሻ ሞተ፤ ሕዝቡም ለአባቶቹ ያደርጉት እንደነበረው ለእሱ ክብር እሳት አላነደዱም።+ 20 በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 32 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ለስምንት ዓመት ገዛ። ሲሞት ማንም አላዘነለትም። በመሆኑም በነገሥታቱ የመቃብር ስፍራ ሳይሆን+ በዳዊት ከተማ+ ቀበሩት።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ