የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 25
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • አሜስያስ በይሁዳ ላይ ነገሠ (1-4)

      • ከኤዶማውያን ጋር የተደረገ ጦርነት (5-13)

      • አሜስያስ ጣዖት አመለከ (14-16)

      • አሜስያስ ከእስራኤል ንጉሥ ከኢዮዓስ ጋር ተዋጋ (17-24)

      • አሜስያስ ሞተ (25-28)

2 ዜና መዋዕል 25:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 14:1-6

2 ዜና መዋዕል 25:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 24:26

2 ዜና መዋዕል 25:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 24:16

2 ዜና መዋዕል 25:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የተመረጡ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 8:11, 12
  • +ዘኁ 1:2, 3

2 ዜና መዋዕል 25:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አንድ ታላንት 34.2 ኪሎ ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

2 ዜና መዋዕል 25:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 19:2

2 ዜና መዋዕል 25:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 14:11፤ 20:6

2 ዜና መዋዕል 25:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 2:7፤ ምሳሌ 10:22፤ ሐጌ 2:8

2 ዜና መዋዕል 25:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 8:13፤ መዝ 60:በመዝሙሩ አናት ላይ የሚገኘው መግለጫ
  • +2ነገ 14:7፤ 2ዜና 20:10, 11

2 ዜና መዋዕል 25:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 25:9
  • +1ነገ 16:29
  • +2ዜና 8:3, 5

2 ዜና መዋዕል 25:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:3, 5፤ ዘዳ 7:25፤ 2ዜና 28:22, 23

2 ዜና መዋዕል 25:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 24:20፤ መዝ 115:8፤ ኤር 2:5፤ 10:5

2 ዜና መዋዕል 25:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 16:10፤ 18:25, 26
  • +ኢሳ 30:10
  • +1ሳሙ 2:25፤ ምሳሌ 29:1

2 ዜና መዋዕል 25:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ፊት ለፊት እንገናኝ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 14:8-10

2 ዜና መዋዕል 25:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በቤተ መንግሥትህ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 25:11

2 ዜና መዋዕል 25:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 14:11-14
  • +2ዜና 25:14
  • +2ዜና 22:7

2 ዜና መዋዕል 25:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 21:8, 16፤ 1ሳሙ 6:19

2 ዜና መዋዕል 25:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ወደየድንኳናቸው።”

2 ዜና መዋዕል 25:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አካዝያስ ተብሎም ይጠራል።

  • *

    ርዝመቱም ወደ 178 ሜትር ገደማ ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 8:16፤ 12:38, 39
  • +2ዜና 26:9፤ ኤር 31:38፤ ዘካ 14:10

2 ዜና መዋዕል 25:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በኦቤድዔዶም ኃላፊነት ሥርና።”

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 7:51፤ 15:18፤ 2ነገ 24:12, 13፤ 25:13-15፤ 2ዜና 12:9

2 ዜና መዋዕል 25:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 13:10
  • +2ነገ 14:1
  • +2ነገ 14:17-20

2 ዜና መዋዕል 25:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 12:20፤ 15:8, 10፤ 21:23

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ዜና 25:12ነገ 14:1-6
2 ዜና 25:32ዜና 24:26
2 ዜና 25:4ዘዳ 24:16
2 ዜና 25:51ሳሙ 8:11, 12
2 ዜና 25:5ዘኁ 1:2, 3
2 ዜና 25:72ዜና 19:2
2 ዜና 25:82ዜና 14:11፤ 20:6
2 ዜና 25:91ሳሙ 2:7፤ ምሳሌ 10:22፤ ሐጌ 2:8
2 ዜና 25:112ሳሙ 8:13፤ መዝ 60:በመዝሙሩ አናት ላይ የሚገኘው መግለጫ
2 ዜና 25:112ነገ 14:7፤ 2ዜና 20:10, 11
2 ዜና 25:132ዜና 25:9
2 ዜና 25:131ነገ 16:29
2 ዜና 25:132ዜና 8:3, 5
2 ዜና 25:14ዘፀ 20:3, 5፤ ዘዳ 7:25፤ 2ዜና 28:22, 23
2 ዜና 25:152ዜና 24:20፤ መዝ 115:8፤ ኤር 2:5፤ 10:5
2 ዜና 25:162ዜና 16:10፤ 18:25, 26
2 ዜና 25:16ኢሳ 30:10
2 ዜና 25:161ሳሙ 2:25፤ ምሳሌ 29:1
2 ዜና 25:172ነገ 14:8-10
2 ዜና 25:192ዜና 25:11
2 ዜና 25:202ነገ 14:11-14
2 ዜና 25:202ዜና 25:14
2 ዜና 25:202ዜና 22:7
2 ዜና 25:21ኢያሱ 21:8, 16፤ 1ሳሙ 6:19
2 ዜና 25:23ነህ 8:16፤ 12:38, 39
2 ዜና 25:232ዜና 26:9፤ ኤር 31:38፤ ዘካ 14:10
2 ዜና 25:241ነገ 7:51፤ 15:18፤ 2ነገ 24:12, 13፤ 25:13-15፤ 2ዜና 12:9
2 ዜና 25:252ነገ 13:10
2 ዜና 25:252ነገ 14:1
2 ዜና 25:252ነገ 14:17-20
2 ዜና 25:272ነገ 12:20፤ 15:8, 10፤ 21:23
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ዜና መዋዕል 25:1-28

ሁለተኛ ዜና መዋዕል

25 አሜስያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 25 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ29 ዓመት ገዛ። እናቱ ዮዓዳን የተባለች የኢየሩሳሌም ተወላጅ ነበረች።+ 2 እሱም በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ፤ ሆኖም በሙሉ ልቡ አልነበረም። 3 መንግሥቱ በእጁ እንደጸናለትም ንጉሥ የነበረውን አባቱን የገደሉትን አገልጋዮቹን ገደላቸው።+ 4 ይሁንና “አባቶች በልጆቻቸው ኃጢአት መገደል የለባቸውም፤ ልጆችም በአባቶቻቸው ኃጢአት መገደል የለባቸውም፤ ይልቁንም እያንዳንዱ ሰው በገዛ ኃጢአቱ ይገደል” በሚለው በሙሴ የሕግ መጽሐፍ ላይ በተጻፈው የይሖዋ ትእዛዝ መሠረት የገዳዮቹን ልጆች አልገደላቸውም።+

5 አሜስያስም የይሁዳን ሰዎች ሰብስቦ በየአባቶቻቸው ቤት፣ በሺህ አለቆችና በመቶ አለቆች በመደልደል መላውን ይሁዳና ቢንያም ወክለው እንዲቆሙ አደረገ።+ ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን መዘገበ፤+ በጦርና በትልቅ ጋሻ መጠቀምና በሠራዊቱ ውስጥ ማገልገል የሚችሉ 300,000 የሠለጠኑ* ተዋጊዎችን አገኘ። 6 በተጨማሪም በ100 የብር ታላንት፣* 100,000 ኃያላን ተዋጊዎችን ከእስራኤል ቀጠረ። 7 ይሁንና አንድ የእውነተኛው አምላክ ሰው ወደ እሱ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ንጉሥ ሆይ፣ ይሖዋ ከእስራኤል፣ ከኤፍሬማውያን ሁሉ ጋር ስላልሆነ+ የእስራኤል ሠራዊት ከአንተ ጋር እንዲዘምት አታድርግ። 8 ይልቁንም ብቻህን ዝመት፤ ወደኋላ አትበል፤ በቆራጥነትም ተዋጋ። እንዲህ ባታደርግ ግን እውነተኛው አምላክ በጠላቶችህ ፊት ሊጥልህ ይችላል፤ አምላክ ለመርዳትም ሆነ ለመጣል ኃይል አለውና።”+ 9 በዚህ ጊዜ አሜስያስ የእውነተኛውን አምላክ ሰው “ታዲያ ለእስራኤል ወታደሮች የሰጠሁት 100 ታላንት ምን ይሁን?” አለው። የእውነተኛውም አምላክ ሰው “ይሖዋ ከዚህ እጅግ የሚበልጥ ሊሰጥህ ይችላል” ሲል መለሰለት።+ 10 በመሆኑም አሜስያስ ከኤፍሬም ወደ እሱ የመጡትን ወታደሮች ወደ ስፍራቸው እንዲመለሱ አሰናበታቸው። እነሱ ግን በይሁዳ እጅግ ተበሳጭተው በታላቅ ቁጣ ወደ ገዛ አገራቸው ተመለሱ።

11 ከዚያም አሜስያስ ተበረታታ፤ የራሱንም ወታደሮች እየመራ ወደ ጨው ሸለቆ+ ሄደ፤ ደግሞም 10,000 የሚሆኑ የሴይር ሰዎችን ገደለ።+ 12 የይሁዳም ሰዎች 10,000 የሚሆኑ ሰዎችን ማረኩ። ከዚያም ወደ ገደል አፋፍ ወስደው፣ ከአፋፉ ላይ ቁልቁል ወረወሯቸው፤ ሁሉም ተፈጥፍጠው ብትንትናቸው ወጣ። 13 ይሁንና አሜስያስ ከእሱ ጋር ወደ ጦርነት እንዳይሄዱ ያሰናበታቸው ወታደሮች+ ከሰማርያ+ አንስቶ እስከ ቤትሆሮን+ ድረስ ያሉትን የይሁዳ ከተሞች ወረሩ፤ 3,000 ሰዎችም ገደሉ፤ ብዙ ምርኮም ወሰዱ።

14 አሜስያስ ኤዶማውያንን መትቶ ከተመለሰ በኋላ የሴይርን ሰዎች አማልክት ይዞ በመምጣት ለራሱ አማልክት አድርጎ አቆማቸው፤+ በእነሱም ፊት ይሰግድ እንዲሁም የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርብላቸው ጀመር። 15 ስለሆነም የይሖዋ ቁጣ በአሜስያስ ላይ ነደደ፤ ነቢይም ልኮ “የገዛ ሕዝባቸውን ከእጅህ መታደግ ያልቻሉትን የሕዝቡን አማልክት የምትከተለው ለምንድን ነው?” አለው።+ 16 በዚህ ጊዜ ንጉሡ ነቢዩን “የንጉሡ አማካሪ አድርገን ሾመንሃል?+ ዝም በል!+ መሞት ትፈልጋለህ?” አለው። ነቢዩም ዝም አለ፤ ሆኖም “ይህን በማድረግህና ምክሬን ባለመስማትህ አምላክ ሊያጠፋህ እንደወሰነ ተረዳሁ” አለ።+

17 የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስ ከአማካሪዎቹ ጋር ከተማከረ በኋላ የእስራኤል ንጉሥ ወደሆነው ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮዓካዝ ልጅ ወደ ኢዮዓስ “ና፣ ውጊያ እንግጠም”* የሚል መልእክት ላከበት።+ 18 የእስራኤል ንጉሥ ኢዮዓስ ደግሞ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ ይህን መልእክት ላከ፦ “በሊባኖስ የሚገኘው ኩርንችት በሊባኖስ ወደሚገኘው አርዘ ሊባኖስ ‘ሴት ልጅህን ለወንድ ልጄ ዳርለት’ የሚል መልእክት ላከ። ይሁን እንጂ በሊባኖስ የነበረ አንድ የዱር አውሬ በዚያ ሲያልፍ ያን ኩርንችት ረገጠው። 19 አንተ ‘እኔ ኤዶምን መትቻለሁ’ ብለሃል።+ በመሆኑም ልብህ ክብር በመሻት ታብዮአል። አሁን ግን አርፈህ ቤትህ* ተቀመጥ። በራስህ ላይ ለምን ጥፋት ትጋብዛለህ? ደግሞስ ራስህንም ሆነ ይሁዳን ለምን ለውድቀት ትዳርጋለህ?”

20 አሜስያስ ግን አልሰማም፤+ የኤዶምን አማልክት በመከተላቸው+ እውነተኛው አምላክ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፎ ሊሰጣቸው ወስኗልና።+ 21 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ ኢዮዓስ ወጣ፤ እሱና የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስም በይሁዳ በምትገኘው በቤትሼሜሽ+ ተጋጠሙ። 22 ይሁዳ በእስራኤል ድል ተመታ፤ እያንዳንዳቸውም ወደየቤታቸው* ሸሹ። 23 የእስራኤል ንጉሥ ኢዮዓስ የኢዮአካዝ* ልጅ፣ የኢዮዓስ ልጅ የሆነውን የይሁዳን ንጉሥ አሜስያስን ቤትሼሜሽ ላይ ያዘው። ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፤ የኢየሩሳሌምን ቅጥር፣ ከኤፍሬም በር+ አንስቶ እስከ ማዕዘን በር+ ድረስ አፈረሰ፤ ርዝመቱም 400 ክንድ* ያህል ነበር። 24 በእውነተኛው አምላክ ቤት በኦቤድዔዶም እጅና* በንጉሡ ቤት* ግምጃ ቤቶች+ የተገኘውን ወርቅ፣ ብርና ዕቃ ሁሉ እንዲሁም የታገቱትን ሰዎች ወሰደ። ከዚያም ወደ ሰማርያ ተመለሰ።

25 የእስራኤል ንጉሥ የኢዮዓካዝ ልጅ ኢዮዓስ+ ከሞተ በኋላ፣ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮዓስ ልጅ አሜስያስ+ 15 ዓመት ኖረ።+ 26 ከመጀመሪያ አንስቶ እስከ መጨረሻ ድረስ ያለው የቀረው የአሜስያስ ታሪክ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ የለም? 27 አሜስያስ ይሖዋን መከተል ከተወበት ጊዜ ጀምሮ በኢየሩሳሌም በእሱ ላይ ሲያሴሩ ቆዩ፤+ እሱም ወደ ለኪሶ ሸሸ፤ እነሱ ግን ተከታትለው እንዲይዙት ሰዎችን ወደ ለኪሶ ላኩ፤ በዚያም ገደሉት። 28 ከዚያም በፈረሶች ላይ ጭነው አመጡት፤ ከአባቶቹም ጋር በይሁዳ ከተማ ቀበሩት።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ