መዝሙር
የዳዊት መዝሙር።
138 በሙሉ ልቤ አወድስሃለሁ።+
በሌሎች አማልክት ፊት
የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።*
ቃልህና ስምህ ከሁሉም ነገር በላይ ጎልቶ እንዲታይ አድርገሃልና።*
4 ይሖዋ ሆይ፣ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያወድሱሃል፤+
የተናገርካቸውን የተስፋ ቃሎች ይሰማሉና።
5 ስለ ይሖዋ መንገዶች ይዘምራሉ፤
የይሖዋ ክብር ታላቅ ነውና።+
7 አደገኛ በሆነ አካባቢ ባልፍም እንኳ አንተ ሕይወቴን ትጠብቃለህ።+
በጠላቶቼ ቁጣ ላይ እጅህን ትዘረጋለህ፤
ቀኝ እጅህ ያድነኛል።
8 ይሖዋ ለእኔ ሲል ሁሉንም ነገር ይፈጽማል።