መዝሙር
የዳዊት ጸሎት።
2 ለእኔ ስትል ፍትሐዊ ውሳኔ አድርግ፤+
ዓይኖችህ ትክክለኛ የሆነውን ነገር ይዩ።
4 የሰዎችን ሥራ በተመለከተ ደግሞ፣
የከንፈርህን ቃል በማክበር ከዘራፊዎች መንገድ ርቄአለሁ።+
5 እግሮቼ እንዳይደነቃቀፉ፣
አረማመዴ በመንገድህ ላይ ይጽና።+
6 አምላክ ሆይ፣ መልስ ስለምትሰጠኝ አንተን እጣራለሁ።+
12 እያንዳንዳቸው ያደነውን ለመዘነጣጠል እንደሚጓጓ አንበሳ፣
በስውር እንደሚያደባ ደቦል አንበሳ ናቸው።
13 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስተህ ፊት ለፊት ግጠመው፤+ ደግሞም ጣለው፤
በሰይፍህ ከክፉው ሰው ታደገኝ፤*
14 ይሖዋ ሆይ፣ ከዚህ ዓለም* ሰዎች በእጅህ ታደገኝ፤
እነዚህ ሰዎች ድርሻቸው አሁን ያለው ሕይወት ነው፤+
አንተ በሰጠሃቸው መልካም ነገሮች አጥግበሃቸዋል፤+
ደግሞም ለብዙ ወንዶች ልጆቻቸው ርስት ያስተላልፋሉ።
15 እኔ ግን ፊትህን በጽድቅ አያለሁ፤
በምነቃበት ጊዜ አንተን በማየት እደሰታለሁ።+