የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 30
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘፀአት የመጽሐፉ ይዘት

      • የዕጣን መሠዊያ (1-10)

      • የሕዝብ ቆጠራና ለማስተሰረያ የሚሆን ገንዘብ (11-16)

      • ለመታጠቢያ የሚያገለግለው የመዳብ ገንዳ (17-21)

      • በብልሃት የተቀመመ የቅብዓት ዘይት (22-33)

      • የቅዱሱ ዕጣን አቀማመም (34-38)

ዘፀአት 30:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 40:5
  • +ዘፀ 37:25-28

ዘፀአት 30:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አንድ ክንድ 44.5 ሴንቲ ሜትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 27:1, 2፤ ዘሌ 4:7

ዘፀአት 30:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 25:22
  • +ዘፀ 26:33፤ ዕብ 9:3

ዘፀአት 30:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 23:13
  • +ዘፀ 30:34, 35
  • +ዘኁ 16:39, 40፤ 1ሳሙ 2:27, 28፤ ሉቃስ 1:9
  • +ዘፀ 27:20

ዘፀአት 30:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በሁለቱ ምሽቶች መካከል።”

ዘፀአት 30:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 10:1፤ 2ዜና 26:18፤ ሕዝ 8:11, 12

ዘፀአት 30:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 23:27፤ ዕብ 9:7
  • +ዘሌ 16:5, 6, 18, 19

ዘፀአት 30:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሱ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 38:25፤ ዘኁ 1:2፤ 2ሳሙ 24:10, 15

ዘፀአት 30:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በቅዱሱ ሰቅል።”

  • *

    አንድ ሰቅል 11.4 ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

  • *

    አንድ ጌራ 0.57 ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 27:25
  • +2ዜና 24:9፤ ማቴ 17:24

ዘፀአት 30:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 38:26፤ ዘኁ 1:3፤ 26:1, 2

ዘፀአት 30:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለነፍሳችሁ።”

  • *

    አንድ ሰቅል 11.4 ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ዘፀአት 30:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለነፍሳችሁ።”

ዘፀአት 30:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 38:8፤ ዘሌ 8:11፤ 1ነገ 7:38
  • +ዘፀ 40:7

ዘፀአት 30:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 40:30, 31፤ ዕብ 10:22

ዘፀአት 30:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 4:6

ዘፀአት 30:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በቅዱሱ ሰቅል።”

  • *

    ከቀረፋ ዛፍ ጋር የሚዛመድ ዛፍ ነው።

  • *

    አንድ ሂን 3.67 ሊትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 3:47

ዘፀአት 30:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 37:29

ዘፀአት 30:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 40:9፤ ዘኁ 7:1

ዘፀአት 30:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 8:10
  • +ዘፀ 29:37

ዘፀአት 30:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 8:12፤ ዘኁ 3:2, 3
  • +ዘፀ 40:15

ዘፀአት 30:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 37:29፤ 1ነገ 1:39፤ መዝ 89:20

ዘፀአት 30:33

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ባዕዱን ሰው።” ከአሮን ወገን ያልሆነን ሰው ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 30:37, 38

ዘፀአት 30:34

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የዚህ ቅመም ምንነት በውል አይታወቅም። ከሚሸት ተክል ወይም ከዛጎል ውስጥ የሚገኝ ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 25:3, 6

ዘፀአት 30:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 37:29፤ መዝ 141:2፤ ራእይ 5:8
  • +ዘሌ 2:13

ዘፀአት 30:37

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 30:31, 32

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘፀ. 30:1ዘፀ 40:5
ዘፀ. 30:1ዘፀ 37:25-28
ዘፀ. 30:2ዘፀ 27:1, 2፤ ዘሌ 4:7
ዘፀ. 30:6ዘፀ 25:22
ዘፀ. 30:6ዘፀ 26:33፤ ዕብ 9:3
ዘፀ. 30:71ዜና 23:13
ዘፀ. 30:7ዘፀ 30:34, 35
ዘፀ. 30:7ዘኁ 16:39, 40፤ 1ሳሙ 2:27, 28፤ ሉቃስ 1:9
ዘፀ. 30:7ዘፀ 27:20
ዘፀ. 30:9ዘሌ 10:1፤ 2ዜና 26:18፤ ሕዝ 8:11, 12
ዘፀ. 30:10ዘሌ 23:27፤ ዕብ 9:7
ዘፀ. 30:10ዘሌ 16:5, 6, 18, 19
ዘፀ. 30:12ዘፀ 38:25፤ ዘኁ 1:2፤ 2ሳሙ 24:10, 15
ዘፀ. 30:13ዘሌ 27:25
ዘፀ. 30:132ዜና 24:9፤ ማቴ 17:24
ዘፀ. 30:14ዘፀ 38:26፤ ዘኁ 1:3፤ 26:1, 2
ዘፀ. 30:18ዘፀ 38:8፤ ዘሌ 8:11፤ 1ነገ 7:38
ዘፀ. 30:18ዘፀ 40:7
ዘፀ. 30:19ዘፀ 40:30, 31፤ ዕብ 10:22
ዘፀ. 30:212ዜና 4:6
ዘፀ. 30:24ዘኁ 3:47
ዘፀ. 30:25ዘፀ 37:29
ዘፀ. 30:26ዘፀ 40:9፤ ዘኁ 7:1
ዘፀ. 30:29ዘሌ 8:10
ዘፀ. 30:29ዘፀ 29:37
ዘፀ. 30:30ዘሌ 8:12፤ ዘኁ 3:2, 3
ዘፀ. 30:30ዘፀ 40:15
ዘፀ. 30:31ዘፀ 37:29፤ 1ነገ 1:39፤ መዝ 89:20
ዘፀ. 30:33ዘፀ 30:37, 38
ዘፀ. 30:34ዘፀ 25:3, 6
ዘፀ. 30:35ዘፀ 37:29፤ መዝ 141:2፤ ራእይ 5:8
ዘፀ. 30:35ዘሌ 2:13
ዘፀ. 30:37ዘፀ 30:31, 32
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
  • 38
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘፀአት 30:1-38

ዘፀአት

30 “ዕጣን የሚጨስበት መሠዊያ ትሠራለህ፤+ ከግራር እንጨትም ትሠራዋለህ።+ 2 ርዝመቱ አንድ ክንድ፣* ወርዱ አንድ ክንድ ሆኖ አራቱም ጎኖቹ እኩል ይሁኑ፤ ቁመቱ ደግሞ ሁለት ክንድ ይሁን። ቀንዶቹም ከዚያው ወጥ ሆነው የተሠሩ ይሆናሉ።+ 3 ላዩን፣ ሁሉንም ጎኖቹን እንዲሁም ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ትለብጠዋለህ፤ ዙሪያውንም የወርቅ ክፈፍ ትሠራለታለህ። 4 በተጨማሪም በሁለቱ ተቃራኒ ጎኖቹ ላይ ከክፈፉ በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ትሠራለታለህ፤ ቀለበቶቹም መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉት መሎጊያዎች የሚገቡባቸው ይሆናሉ። 5 መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው። 6 ራሴን ለአንተ ከምገልጥበት+ ከምሥክሩ ታቦት+ አጠገብ ካለው መጋረጃ በፊት ይኸውም ምሥክሩን ከሚጋርደው መከለያ በፊት ታስቀምጠዋለህ።

7 “አሮንም+ ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን+ ያጨስበታል፤+ በየማለዳው መብራቶቹን+ በሚያዘገጃጅበት ጊዜም ዕጣኑ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርጋል። 8 በተጨማሪም አሮን አመሻሹ ላይ* መብራቶቹን በሚያበራበት ጊዜ ዕጣኑን ያጨሰዋል። ይህም በትውልዶቻችሁ ሁሉ ዘወትር በይሖዋ ፊት የሚቀርብ የዕጣን መባ ነው። 9 በዚህ መሠዊያ ላይ ያልተፈቀደ ዕጣን+ ወይም የሚቃጠል መባ አሊያም የእህል መባ አታቅርቡ፤ እንዲሁም በላዩ ላይ የመጠጥ መባ አታፍስሱ። 10 አሮንም በዓመት አንድ ጊዜ በቀንዶቹ ላይ ማስተሰረያ ያድርግ።+ ለማስተሰረያ ከቀረበው የኃጢአት መባ ላይ የተወሰነ ደም ወስዶ+ በዓመት አንድ ጊዜ ለመሠዊያው ማስተሰረያ ያደርጋል፤ ይህም በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይደረጋል። ይህ ለይሖዋ እጅግ የተቀደሰ ነው።”

11 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 12 “የሕዝብ ቆጠራ በማካሄድ የእስራኤልን ልጆች በምትቆጥርበት+ ጊዜ ሁሉ እያንዳንዱ ሰው በቆጠራው ወቅት ለይሖዋ ስለ ሕይወቱ* ቤዛ መስጠት አለበት። ይህን የሚያደርጉት በሚመዘገቡበት ጊዜ መቅሰፍት እንዳይመጣባቸው ነው። 13 የተመዘገቡት ሁሉ የሚሰጡት ይህን ነው፦ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል* መሠረት+ ግማሽ ሰቅል* ይሰጣሉ። አንድ ሰቅል ሃያ ጌራ* ነው። ለይሖዋ የሚሰጠው መዋጮ ግማሽ ሰቅል ነው።+ 14 ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ሆኗቸው የተመዘገቡት ሁሉ ለይሖዋ መዋጮ ይሰጣሉ።+ 15 ለሕይወታችሁ* ማስተሰረያ እንዲሆን ለይሖዋ መዋጮ በምትሰጡበት ጊዜ ባለጸጋው ከግማሽ ሰቅል* አብልጦ፣ ችግረኛውም ከግማሽ ሰቅል አሳንሶ አይስጥ። 16 ለሕይወታችሁ* ማስተሰረያ በመሆን በይሖዋ ፊት ለእስራኤላውያን እንደ መታሰቢያ ሆኖ እንዲያገለግል ለማስተሰረያ የቀረበውን የብር ገንዘብ ከእስራኤላውያን ወስደህ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ለሚቀርበው አገልግሎት ትሰጠዋለህ።”

17 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 18 “ለመታጠቢያ እንዲሆን ከመዳብ ገንዳና ማስቀመጫውን ሥራ፤+ በመገናኛ ድንኳኑና በመሠዊያው መካከል አስቀምጠው፤ ውኃም ጨምርበት።+ 19 አሮንና ወንዶች ልጆቹም እጃቸውንና እግራቸውን ይታጠቡበታል።+ 20 ወደ መገናኛ ድንኳኑ በሚገቡበት ወይም ለማገልገልና በእሳት የሚቀርብ መባ ለይሖዋ ለማቅረብ ወደ መሠዊያው በሚቀርቡበት ጊዜ እንዳይሞቱ በውኃ ይታጠባሉ። 21 እንዳይሞቱ እጃቸውንና እግራቸውን ይታጠቡ፤ ይህም ለእሱና ለዘሮቹ በትውልዶቻቸው ሁሉ ዘላለማዊ ሥርዓት ሆኖ ያገልግል።”+

22 ይሖዋም እንዲህ በማለት ሙሴን ማነጋገሩን ቀጠለ፦ 23 “አንተም ጥሩ መዓዛ ያላቸውን የሚከተሉትን ምርጥ ቅመሞች ውሰድ፦ 500 ሰቅል የረጋ ከርቤ፣ የዚህን ግማሽ ይኸውም 250 ሰቅል ጣፋጭ ቀረፋ፣ 250 ሰቅል ጥሩ መዓዛ ያለው ጠጅ ሣር፣ 24 እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል* መሠረት+ 500 ሰቅል ብርጉድ* እንዲሁም አንድ ሂን* የወይራ ዘይት። 25 ከእነዚህም ቅዱስ የቅብዓት ዘይት አዘጋጅ፤ በብልሃት የተቀመመ መሆን ይኖርበታል።+ ይህም ቅዱስ የቅብዓት ዘይት ይሆናል።

26 “አንተም የመገናኛ ድንኳኑንና+ የምሥክሩን ታቦት 27 እንዲሁም ጠረጴዛውንና ዕቃዎቹን በሙሉ፣ መቅረዙንና ዕቃዎቹን፣ የዕጣን መሠዊያውን፣ 28 የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያና ዕቃዎቹን በሙሉ እንዲሁም የውኃ ገንዳውንና ማስቀመጫውን በዘይቱ ትቀባለህ። 29 እጅግ ቅዱስ እንዲሆኑም ቀድሳቸው።+ የሚነካቸው ማንኛውም ሰው ቅዱስ መሆን አለበት።+ 30 አንተም አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ትቀባቸዋለህ፤+ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝም+ ትቀድሳቸዋለህ።

31 “አንተም ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ትነግራቸዋለህ፦ ‘በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህ ምንጊዜም ለእኔ ቅዱስ የቅብዓት ዘይት ይሆናል።+ 32 ይህ ማንም ሰው ሰውነቱን የሚቀባው አይደለም፤ እንዲሁም በተመሳሳይ መንገድ በመቀመም እንዲህ ያለ ቅባት ማዘጋጀት የለባችሁም። ይህ የተቀደሰ ነገር ነው። ለእናንተም ምንጊዜም የተቀደሰ ይሆናል። 33 ይህን የመሰለ ቅባት የሚሠራና ያልተፈቀደለትን ሰው* የሚቀባ ማንኛውም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ።’”+

34 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንተም ጥሩ መዓዛ ካላቸው ቅመሞች+ ይኸውም ከሚንጠባጠብ ሙጫ፣ ከኦኒካ፣* ከሚሸት ሙጫ እንዲሁም ከንጹሕ ነጭ ዕጣን እኩል መጠን ውሰድ። 35 ከዚያም ዕጣን አድርገህ አዘጋጀው፤+ ይህም ዕጣን በብልሃት የተቀመመ፣ ጨው የተጨመረበት፣+ ንጹሕና ቅዱስ መሆን ይኖርበታል። 36 ከእሱም የተወሰነውን ወቅጠህ በማላም ራሴን ለአንተ በምገልጥበት በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ባለው ምሥክር ፊት ታስቀምጠዋለህ። ይህም ለእናንተ እጅግ ቅዱስ መሆን ይኖርበታል። 37 በተመሳሳይ መንገድ የተቀመመ ዕጣን ለራስህ ማዘጋጀት የለብህም።+ ለይሖዋ የተቀደሰ እንደሆነ አድርገህ ልትመለከተው ይገባል። 38 በመዓዛው ለመደሰት ሲል ይህን የመሰለ ዕጣን የሚያዘጋጅ ማንኛውም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ።”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ