የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 32
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘፀአት የመጽሐፉ ይዘት

      • ለአምልኮ የተሠራው የወርቅ ጥጃ (1-35)

        • ሙሴ ለየት ያለ መዝሙር ሰማ (17, 18)

        • ሙሴ ሕጉ የተጻፈባቸውን ጽላቶች ሰባበራቸው (19)

        • ሌዋውያን በታማኝነት ከይሖዋ ጎን ቆሙ (26-29)

ዘፀአት 32:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 24:18፤ ዘዳ 9:9
  • +ሥራ 7:40

ዘፀአት 32:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 12:35, 36

ዘፀአት 32:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ሐውልት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 9:16፤ ኢሳ 46:6፤ ሥራ 7:41
  • +ዘፀ 20:4፤ ነህ 9:18፤ መዝ 106:19, 20

ዘፀአት 32:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 10:7

ዘፀአት 32:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:15-18

ዘፀአት 32:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ሐውልት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 18:20፤ 20:3

ዘፀአት 32:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አንገተ ደንዳና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 34:9፤ ዘዳ 9:6፤ ሥራ 7:51

ዘፀአት 32:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 14:12፤ ዘዳ 9:14

ዘፀአት 32:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 106:23
  • +ዘዳ 9:18, 19

ዘፀአት 32:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ተጸጸት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 9:28

ዘፀአት 32:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 22:15-17፤ 35:10, 11፤ ዕብ 6:13, 14
  • +ዘፍ 13:14, 15፤ 26:3, 4

ዘፀአት 32:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በተናገረው ጥፋት ተጸጸተ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 106:45

ዘፀአት 32:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 40:20፤ ዘዳ 5:22
  • +ዘዳ 9:15

ዘፀአት 32:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 31:18፤ ዘዳ 9:10

ዘፀአት 32:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 9:18፤ መዝ 106:19, 20፤ ሥራ 7:41
  • +ዘዳ 9:16, 17

ዘፀአት 32:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 7:25
  • +ዘዳ 9:21

ዘፀአት 32:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 15:24፤ 16:2፤ 17:2፤ ዘዳ 9:7፤ 31:27

ዘፀአት 32:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 32:1፤ ሥራ 7:40

ዘፀአት 32:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 24:15፤ 2ነገ 10:15

ዘፀአት 32:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 25:5

ዘፀአት 32:29

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እጃችሁን ሙሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 25:11፤ ዘዳ 13:6-9
  • +ዘዳ 33:8, 9

ዘፀአት 32:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 16:47፤ 21:7፤ ዘዳ 9:18

ዘፀአት 32:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:23

ዘፀአት 32:32

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 14:19
  • +ፊልጵ 4:3፤ ራእይ 3:5

ዘፀአት 32:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 23:20፤ 33:2

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘፀ. 32:1ዘፀ 24:18፤ ዘዳ 9:9
ዘፀ. 32:1ሥራ 7:40
ዘፀ. 32:2ዘፀ 12:35, 36
ዘፀ. 32:4ዘዳ 9:16፤ ኢሳ 46:6፤ ሥራ 7:41
ዘፀ. 32:4ዘፀ 20:4፤ ነህ 9:18፤ መዝ 106:19, 20
ዘፀ. 32:61ቆሮ 10:7
ዘፀ. 32:7ዘዳ 4:15-18
ዘፀ. 32:8ዘፀ 18:20፤ 20:3
ዘፀ. 32:9ዘፀ 34:9፤ ዘዳ 9:6፤ ሥራ 7:51
ዘፀ. 32:10ዘኁ 14:12፤ ዘዳ 9:14
ዘፀ. 32:11መዝ 106:23
ዘፀ. 32:11ዘዳ 9:18, 19
ዘፀ. 32:12ዘዳ 9:28
ዘፀ. 32:13ዘፍ 22:15-17፤ 35:10, 11፤ ዕብ 6:13, 14
ዘፀ. 32:13ዘፍ 13:14, 15፤ 26:3, 4
ዘፀ. 32:14መዝ 106:45
ዘፀ. 32:15ዘፀ 40:20፤ ዘዳ 5:22
ዘፀ. 32:15ዘዳ 9:15
ዘፀ. 32:16ዘፀ 31:18፤ ዘዳ 9:10
ዘፀ. 32:19ነህ 9:18፤ መዝ 106:19, 20፤ ሥራ 7:41
ዘፀ. 32:19ዘዳ 9:16, 17
ዘፀ. 32:20ዘዳ 7:25
ዘፀ. 32:20ዘዳ 9:21
ዘፀ. 32:22ዘፀ 15:24፤ 16:2፤ 17:2፤ ዘዳ 9:7፤ 31:27
ዘፀ. 32:23ዘፀ 32:1፤ ሥራ 7:40
ዘፀ. 32:26ኢያሱ 24:15፤ 2ነገ 10:15
ዘፀ. 32:27ዘኁ 25:5
ዘፀ. 32:29ዘኁ 25:11፤ ዘዳ 13:6-9
ዘፀ. 32:29ዘዳ 33:8, 9
ዘፀ. 32:30ዘኁ 16:47፤ 21:7፤ ዘዳ 9:18
ዘፀ. 32:31ዘፀ 20:23
ዘፀ. 32:32ዘኁ 14:19
ዘፀ. 32:32ፊልጵ 4:3፤ ራእይ 3:5
ዘፀ. 32:34ዘፀ 23:20፤ 33:2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘፀአት 32:1-35

ዘፀአት

32 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሙሴ ከተራራው ላይ ሳይወርድ እንደቆየ አየ።+ በመሆኑም አሮንን ከበው እንዲህ አሉት፦ “እንግዲህ ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣን ያ ሙሴ ምን እንደደረሰበት ስለማናውቅ በል ተነስተህ ከፊት ከፊታችን የሚሄድ አምላክ ሥራልን።”+ 2 አሮንም “በሚስቶቻችሁ እንዲሁም በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ጆሮዎች ላይ ያሉትን የወርቅ ጉትቻዎች+ አውልቃችሁ አምጡልኝ” አላቸው። 3 በመሆኑም ሕዝቡ ሁሉ በጆሮዎቻቸው ላይ የነበሩትን የወርቅ ጉትቻዎች እያወለቁ ወደ አሮን ያመጡ ጀመር። 4 እሱም ወርቁን ከእነሱ ወስዶ በቅርጽ ማውጫ ቅርጽ አወጣለት፤ የጥጃ ሐውልትም* አድርጎ ሠራው።+ እነሱም “እስራኤል ሆይ፣ ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው” ይሉ ጀመር።+

5 አሮንም ይህን ሲያይ በምስሉ ፊት መሠዊያ ሠራ። ከዚያም ድምፁን ከፍ አድርጎ “ነገ ለይሖዋ የሚከበር በዓል አለ” ሲል ተናገረ። 6 በመሆኑም በማግስቱ በማለዳ ተነስተው የሚቃጠል መባና የኅብረት መሥዋዕት ያቀርቡ ጀመር። ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ። ከዚያም ሊጨፍሩ ተነሱ።+

7 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከግብፅ ምድር መርተህ ያወጣኸው ሕዝብህ ምግባረ ብልሹ+ ስለሆነ ሂድ፣ ውረድ። 8 እንዲሄዱበት ካዘዝኳቸው መንገድ+ ፈጥነው ዞር ብለዋል። ለራሳቸውም የጥጃ ሐውልት* ሠርተዋል፤ ለእሱም እየሰገዱና መሥዋዕት እያቀረቡ ‘እስራኤል ሆይ፣ ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው’ እያሉ ነው።” 9 ይሖዋም በመቀጠል ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ ግትር* መሆኑን ተመልክቻለሁ።+ 10 እንግዲህ አሁን ቁጣዬ እንዲነድባቸውና እንዳጠፋቸው ተወኝ፤ አንተን በእነሱ ምትክ ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ።”+

11 ሙሴም አምላኩን ይሖዋን ተማጸነ፤+ እንዲህም አለ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ በታላቅ ኃይልና በብርቱ እጅ ከግብፅ ምድር ካወጣሃቸው በኋላ በሕዝብህ ላይ ቁጣህ የሚነደው ለምንድን ነው?+ 12 ግብፃውያንስ ‘ቀድሞውንም ቢሆን መርቶ ያወጣቸው ተንኮል አስቦ ነው። በተራሮች ላይ ሊገድላቸውና ከምድር ገጽ ሊያጠፋቸው ፈልጎ ነው’ ለምን ይበሉ?+ ከሚነደው ቁጣህ ተመለስ፤ በሕዝብህ ላይ ይህን ጥፋት ለማምጣት ያደረግከውን ውሳኔ እስቲ እንደገና አስበው።* 13 ‘ዘራችሁን በሰማያት ላይ እንዳሉት ከዋክብት አበዛዋለሁ፤+ ለዘላለም ርስት አድርጎ እንዲወርሰውም ለዘራችሁ ለመስጠት ያሰብኩትን ይህን ምድር በሙሉ እሰጠዋለሁ’+ በማለት በራስህ የማልክላቸውን አገልጋዮችህን አብርሃምን፣ ይስሐቅንና እስራኤልን አስታውስ።”

14 በመሆኑም ይሖዋ በሕዝቡ ላይ እንደሚያመጣ የተናገረውን ጥፋት እንደገና አሰበበት።*+

15 ከዚያም ሙሴ ሁለቱን የምሥክር ጽላቶች+ በእጁ እንደያዘ+ ተመልሶ ከተራራው ወረደ። ጽላቶቹም በሁለቱም በኩል ተቀርጾባቸው ነበር፤ በፊትም ሆነ በጀርባ ተጽፎባቸው ነበር። 16 ጽላቶቹ የአምላክ ሥራ ነበሩ፤ በጽላቶቹ ላይ የተቀረጸው ጽሑፍም የአምላክ ጽሑፍ ነበር።+ 17 ኢያሱም ሕዝቡ ይጮኽ ስለነበር ጫጫታውን ሲሰማ ሙሴን “በሰፈሩ ውስጥ የጦርነት ሁካታ ይሰማል” አለው። 18 ሙሴ ግን እንዲህ አለው፦

“ይህ ድምፅ የድል መዝሙር አይደለም፤

ይህ ድምፅ በሽንፈት ምክንያት የሚሰማ የለቅሶ ድምፅም አይደለም፤

ይህ የምሰማው ድምፅ የተለየ መዝሙር ድምፅ ነው።”

19 ሙሴም ወደ ሰፈሩ ሲቃረብ ጥጃውንና+ ጭፈራውን አየ፤ በዚህ ጊዜ ቁጣው ነደደ። ጽላቶቹንም ከእጁ ወርውሮ በተራራው ግርጌ ሰባበራቸው።+ 20 የሠሩትንም ጥጃ ወስዶ በእሳት አቃጠለው፤ ሰባብሮም ዱቄት አደረገው፤+ ከዚያም በውኃው ላይ በመበተን እስራኤላውያን እንዲጠጡት አደረገ።+ 21 ሙሴም አሮንን “ይህን ከባድ ኃጢአት ያመጣህበት ይህ ሕዝብ ምን ቢያደርግህ ነው?” አለው። 22 በዚህ ጊዜ አሮን እንዲህ አለ፦ “ጌታዬ አትቆጣ። መቼም ይህ ሕዝብ ወደ ክፋት ያዘነበለ እንደሆነ አንተ ራስህ በሚገባ ታውቃለህ።+ 23 ስለዚህ ‘ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣን ያ ሙሴ ምን እንደደረሰበት ስለማናውቅ ከፊት ከፊታችን የሚሄድ አምላክ ሥራልን’ አሉኝ።+ 24 በመሆኑም ‘ወርቅ ያለው ሁሉ አውልቆ ይስጠኝ’ አልኳቸው። ከዚያም ወርቁን እሳቱ ውስጥ ጣልኩት፤ ይህም ጥጃ ወጣ።”

25 በተቃዋሚዎቻቸው ፊት መሳለቂያ እንዲሆኑ አሮን ሕዝቡን መረን ስለለቀቃቸው ሙሴ ሕዝቡ መረን እንደተለቀቀ አስተዋለ። 26 ከዚያም ሙሴ በሰፈሩ መግቢያ ላይ ቆሞ “ከይሖዋ ጎን የሚቆም ማን ነው? ወደ እኔ ይምጣ!”+ አለ። በዚህ ጊዜ ሌዋውያን በሙሉ በዙሪያው ተሰበሰቡ። 27 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እያንዳንዳችሁ ሰይፋችሁን ታጠቁ፤ ከአንዱ በር ወደ ሌላው በር በመሄድና በሰፈሩ ውስጥ በማለፍ እያንዳንዱ ሰው ወንድሙን፣ ጎረቤቱንና የቅርብ ጓደኛውን ይግደል።’”+ 28 ሌዋውያኑም ሙሴ እንዳላቸው አደረጉ። በመሆኑም በዚያ ዕለት 3,000 ገደማ የሚሆኑ ወንዶች ተገደሉ። 29 ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለ፦ “እያንዳንዳችሁ በገዛ ልጃችሁና በገዛ ወንድማችሁ ላይ ስለተነሳችሁ+ ዛሬ ራሳችሁን ለይሖዋ ለዩ፤* እሱም ዛሬ በረከትን ያፈስላችኋል።”+

30 በማግስቱም ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “ከባድ ኃጢአት ሠርታችኋል፤ እንግዲህ አሁን ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ አንድ ነገር ማድረግ እችል እንደሆነ ለማየት ወደ ይሖዋ እወጣለሁ።”+ 31 በመሆኑም ሙሴ ወደ ይሖዋ ተመልሶ እንዲህ አለ፦ “ይህ ሕዝብ የፈጸመው ኃጢአት ምንኛ ከባድ ነው! የወርቅ አምላክ ሠርተዋል።+ 32 ሆኖም አሁን ፈቃድህ ከሆነ ኃጢአታቸውን ይቅር በል፤+ ካልሆነ ግን እባክህ እኔን ከጻፍከው መጽሐፍህ ላይ ደምስሰኝ።”+ 33 ይሁንና ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በእኔ ላይ ኃጢአት የሠራውን ሁሉ ከመጽሐፌ ላይ እደመስሰዋለሁ። 34 በል አሁን ሄደህ ሕዝቡን ወደነገርኩህ ስፍራ እየመራህ ውሰዳቸው። እነሆ መልአኬ ከፊት ከፊትህ ይሄዳል፤+ ሕዝቡን በምመረምርበትም ቀን ስለሠሩት ኃጢአት ቅጣት አመጣባቸዋለሁ።” 35 ከዚያም ይሖዋ፣ በሠሩት ጥጃ ይኸውም አሮን በሠራላቸው ጥጃ ምክንያት ሕዝቡን በመቅሰፍት መታ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ