ምሳሌ
2 ልጄ ሆይ፣ ቃሌን ብትቀበልና
ትእዛዛቴን እንደ ውድ ሀብት ብታስቀምጥ፣+
2 ይህን ለማድረግ ጆሮህን ወደ ጥበብ ብታቀና፣+
ጥልቅ ግንዛቤ ለማግኘት ልብህን ብታዘነብል፣+
3 ደግሞም ማስተዋልን ብትጣራና+
ጥልቅ ግንዛቤ ለማግኘት ድምፅህን ብታሰማ፣+
4 እንደ ብር ተግተህ ብትፈልጋት፣+
እንዲሁም እንደተሸሸገ ሀብት አጥብቀህ ብትሻት፣+
5 ያን ጊዜ ይሖዋን መፍራት ምን ማለት እንደሆነ ትረዳለህ፤+
ደግሞም ስለ አምላክ እውቀት ትቀስማለህ።+
6 ይሖዋ ራሱ ጥበብ ይሰጣልና፤+
ከአፉ እውቀትና ጥልቅ ግንዛቤ ይወጣል።
8 የፍትሕን ጎዳና ይከታተላል፤
የታማኞቹንም መንገድ ይጠብቃል።+
9 በዚህ ጊዜ ጽድቅ፣ ፍትሕና ትክክል የሆነውን ነገር
ይኸውም የጥሩነትን ጎዳና በሙሉ ትረዳለህ።+
10 ጥበብ ወደ ልብህ ስትገባና+
11 የማመዛዘን ችሎታ ምንጊዜም ይጠብቅሃል፤+
ጥልቅ ግንዛቤም ይጋርድሃል፤
12 ይህም አንተን ከክፉ መንገድ ለማዳን
እንዲሁም ጠማማ ነገር ከሚናገር ሰው፣+
13 በጨለማ መንገድ ለመጓዝ
ቀናውን ጎዳና ከሚተዉ፣+
14 መጥፎ ድርጊት በመፈጸም ሐሴት ከሚያደርጉ፣
ጠማማ በሆኑ ክፉ ነገሮች ከሚደሰቱ፣
15 መንገዳቸው ጠማማ ከሆነና
አካሄዳቸው በተንኮል ከተሞላ ሰዎች አንተን ለመታደግ ነው።
16 ጋጠወጥ* ከሆነች ሴት፣
ባለጌ* ሴት ከምትናገረው የሚያባብል* ቃል ያድንሃል፤+
17 ይህች ሴት በወጣትነቷ የነበራትን የቅርብ ወዳጇን*+ የምትተው
እንዲሁም ከአምላኳ ጋር የገባችውን ቃል ኪዳን የምትረሳ ናት፤
18 ቤቷ ሰውን ይዞ ወደ ሞት ይወርዳልና፤