ምሳሌ
28 ክፉዎች ማንም ሳያሳድዳቸው ይሸሻሉ፤
ጻድቃን ግን እንደ አንበሳ ልበ ሙሉ ናቸው።+
2 በአንድ አገር ውስጥ ሕግ ተላላፊነት* ሲነግሥ ብዙ ገዢዎች ይፈራረቁበታል፤+
ይሁንና ጥልቅ ግንዛቤና እውቀት ያለው ሰው በሚያበረክተው እርዳታ ገዢ* ለረጅም ዘመን ይቆያል።+
3 ችግረኞችን የሚበዘብዝ ድሃ፣+
እህሉን ሁሉ ጠራርጎ እንደሚወስድ ዝናብ ነው።
4 ሕግን የሚተዉ ሰዎች ክፉዎችን ያወድሳሉ፤
ሕግን የሚጠብቁ ሰዎች ግን በእነሱ ላይ ይቆጣሉ።+
5 ክፉዎች ፍትሕን መረዳት አይችሉም፤
ይሖዋን የሚፈልጉ ግን ሁሉን ነገር መረዳት ይችላሉ።+
7 አስተዋይ ልጅ ሕግን ይጠብቃል፤
ከሆዳሞች ጋር የሚወዳጅ ግን አባቱን ያዋርዳል።+
9 ሕግን ለመስማት አሻፈረኝ የሚል ሰው፣
ጸሎቱ እንኳ አስጸያፊ ነው።+
12 ጻድቃን ድል ሲያደርጉ ታላቅ ክብር ይሆናል፤
ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ግን ሰዎች ይሸሸጋሉ።+
15 ምስኪን በሆነ ሕዝብ ላይ የተሾመ ክፉ ገዢ፣
እንደሚያገሳ አንበሳና ተንደርድሮ እንደሚመጣ ድብ ነው።+
17 የሰው ሕይወት በማጥፋቱ የደም* ባለ ዕዳ የሆነ ሰው መቃብር* እስኪገባ ድረስ ሲሸሽ ይኖራል።+
እንዲህ ያለውን ሰው ማንም አይርዳው።
19 መሬቱን የሚያርስ ሰው የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፤
ከንቱ የሆኑ ነገሮችን የሚያሳድድ ግን እጅግ ይደኸያል።+
21 አድልዎ ማድረግ መልካም አይደለም፤+
ሆኖም ሰው ለቁራሽ ዳቦ ብሎ ስህተት ሊፈጽም ይችላል።
22 ቀናተኛ* ሰው ሀብት ለማግኘት ይጓጓል፤
ድህነት ላይ እንደሚወድቅ አያውቅም።
24 አባቱንና እናቱን እየዘረፈ “ምንም ጥፋት የለበትም” የሚል ሁሉ+
የአጥፊ ተባባሪ ነው።+
27 ለድሃ የሚሰጥ ሁሉ አይቸገርም፤+
እነሱን ላለማየት ዓይኖቹን የሚከድን ግን ብዙ እርግማን ይደርስበታል።
28 ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ሰው ራሱን ይሸሽጋል፤
ክፉዎች ሲጠፉ ግን ጻድቃን ይበዛሉ።+