ምሳሌ
4 አባቴ እንዲህ ሲል አስተማረኝ፦ “ልብህ ቃሌን አጥብቆ ይያዝ።+
ትእዛዛቴን ጠብቅ፤ በሕይወትም ትኖራለህ።+
5 ጥበብን አግኝ፤ ማስተዋልንም አዳብር።+
የምናገረውን ነገር አትርሳ፤ ከእሱም ፈቀቅ አትበል።
6 ጥበብን አትተዋት፤ እሷም ትጠብቅሃለች።
ውደዳት፤ እሷም ትከልልሃለች።
8 ለጥበብ የላቀ ዋጋ ስጥ፤ እሷም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች።+
ብታቅፋት ታከብርሃለች።+
9 በራስህ ላይ የሚያምር የአበባ ጉንጉን ትደፋልሃለች፤
በውበት አክሊልም ታስጌጥሃለች።”
10 ልጄ ሆይ፣ አዳምጥ፤ የምናገረውንም ተቀበል፤
የሕይወትህም ዘመን ይረዝማል።+
12 በምትጓዝበት ጊዜ እርምጃህ አይስተጓጎልም፤
ብትሮጥም አትሰናከልም።
13 ተግሣጽን ያዛት፤ አትልቀቃትም።+
ጠብቃት፤ ሕይወትህ ናትና።+
14 ወደ ክፉዎች መንገድ አትግባ፤
በመጥፎ ሰዎች ጎዳናም አትሂድ።+
16 እነሱ ክፋት ካልሠሩ አይተኙምና።
ሰውን ለውድቀት ካልዳረጉ እንቅልፍ በዓይናቸው አይዞርም።
17 የክፋት ምግብ ይበላሉ፤
የዓመፅም ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።
18 የጻድቃን መንገድ ግን ፍንትው ብሎ እንደሚወጣ የማለዳ ብርሃን ነው፤
እንደ ቀትር ብርሃን ቦግ ብሎ እስኪበራም ድረስ እየደመቀ ይሄዳል።+
19 የክፉዎች መንገድ እንደ ጨለማ ነው፤
ምን እንደሚያሰናክላቸው አያውቁም።
20 ልጄ ሆይ፣ ቃሌን በትኩረት ተከታተል፤
ንግግሬን በጥሞና አዳምጥ።*
23 ከምንም ነገር በላይ ልብህን ጠብቅ፤+
የሕይወት ምንጭ ከእሱ ዘንድ ነውና።
24 ጠማማ አንደበትን ከአንተ አስወግድ፤+
አታላይ የሆነን ንግግርም ከአንተ አርቅ።
27 ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አትበል።+
እግርህን ከክፉ ነገር መልስ።