የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መኃልየ መኃልይ 2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መኃልየ መኃልይ የመጽሐፉ ይዘት

    • ሱላማዊቷ ልጃገረድ በንጉሥ ሰለሞን ሰፈር (1:1–3:5)

መኃልየ መኃልይ 2:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ሳፍሮን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 2:16

መኃልየ መኃልይ 2:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ወይን ጠጅ ቤት።”

መኃልየ መኃልይ 2:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 30:11, 12

መኃልየ መኃልይ 2:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 8:3

መኃልየ መኃልይ 2:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 2:18
  • +መኃ 3:5፤ 8:4

መኃልየ መኃልይ 2:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 2:17፤ 8:14

መኃልየ መኃልይ 2:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 6:11
  • +ኢሳ 18:5፤ ዮሐ 15:2
  • +ኤር 8:7

መኃልየ መኃልይ 2:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 28:4፤ ናሆም 3:12

መኃልየ መኃልይ 2:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 5:2፤ ኤር 48:28
  • +መኃ 8:13
  • +መኃ 1:5፤ 6:10

መኃልየ መኃልይ 2:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 7:10
  • +መኃ 1:7፤ 2:1፤ 6:3

መኃልየ መኃልይ 2:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ክፍተት ባላቸው ተራሮች” ማለትም ሊሆን ይችላል። ወይም “በቤተር ተራሮች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 2:18፤ መኃ 2:9፤ 8:14

ተዛማጅ ሐሳብ

መኃ. 2:1መኃ 2:16
መኃ. 2:51ሳሙ 30:11, 12
መኃ. 2:6መኃ 8:3
መኃ. 2:72ሳሙ 2:18
መኃ. 2:7መኃ 3:5፤ 8:4
መኃ. 2:9መኃ 2:17፤ 8:14
መኃ. 2:12መኃ 6:11
መኃ. 2:12ኢሳ 18:5፤ ዮሐ 15:2
መኃ. 2:12ኤር 8:7
መኃ. 2:13ኢሳ 28:4፤ ናሆም 3:12
መኃ. 2:14መኃ 5:2፤ ኤር 48:28
መኃ. 2:14መኃ 8:13
መኃ. 2:14መኃ 1:5፤ 6:10
መኃ. 2:16መኃ 7:10
መኃ. 2:16መኃ 1:7፤ 2:1፤ 6:3
መኃ. 2:172ሳሙ 2:18፤ መኃ 2:9፤ 8:14
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መኃልየ መኃልይ 2:1-17

መኃልየ መኃልይ

2 “እኔ ግን በባሕር ዳርቻ ላይ የሚበቅል የሳሮን አበባ* ነኝ፤

የሸለቆም አበባ ነኝ።”+

 2 “ፍቅሬ በሴቶች መካከል ስትታይ

በእሾህ መካከል እንዳለ አበባ ናት።”

 3 “ውዴ በወንዶች መካከል ሲታይ

በዱር ዛፎች መካከል እንዳለ የፖም ዛፍ ነው።

በጥላው ሥር ለመቀመጥ እጅግ እጓጓለሁ፤

ፍሬውም ለአፌ ጣፋጭ ነው።

 4 ወደ ግብዣ ቤት* ወሰደኝ፤

የፍቅር ዓርማውንም በእኔ ላይ አውለበለበ።

 5 በዘቢብ ቂጣ ኃይሌን አድሱልኝ፤+

በፖም አበረታቱኝ፤

በፍቅሩ ተይዤ ታምሜአለሁና።

 6 ግራ እጁን ተንተርሻለሁ፤

ቀኝ እጁም አቅፎኛል።+

 7 የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ በራሱ እስኪነሳሳ ድረስ

ፍቅርን በውስጤ እንዳትቀሰቅሱ ወይም እንዳታነሳሱ፣

በሜዳ ፍየሎችና+ በመስክ ላይ ባሉ አጋዘኖች አምላችኋለሁ።+

 8 እነሆ፣ ውዴ ተራሮቹን እየወጣና

በኮረብቶቹ ላይ እየዘለለ ሲመጣ

ድምፁ ይሰማኛል!

 9 ውዴ፣ የሜዳ ፍየል ወይም የአጋዘን ግልገል+ ይመስላል።

በመስኮት በኩል ትኩር ብሎ እየተመለከተ፣

በፍርግርጉ በኩል አጮልቆ እያየ

ከግድግዳችን ጀርባ ቆሟል።

10 ውዴ እንዲህ አለኝ፦

‘ፍቅሬ ሆይ፣ ተነሽ፤

የእኔ ቆንጆ፣ ነይ አብረን እንሂድ።

11 እነሆ፣ ክረምቱ አልፏል።

ዝናቡ ቆሟል፤ ደግሞም ጠፍቷል።

12 በምድሩ ላይ አበቦች አብበዋል፤+

ተክሎች የሚገረዙበት ጊዜ ደርሷል፤+

በምድራችንም ላይ የዋኖስ ዝማሬ ተሰምቷል።+

13 የበለስ ዛፏ መጀመሪያ ላይ ያፈራቻቸው ፍሬዎች በስለዋል፤+

የወይን ተክሎቹም አብበው መዓዛቸውን ሰጥተዋል።

ፍቅሬ ሆይ፣ ተነሽና ነይ፤

የእኔ ቆንጆ፣ ነይ አብረን እንሂድ።

14 በዓለቶች መሃል በሚገኝ መሸሸጊያ፣

በገደላማ ስፍራ ባለ ሰዋራ ቦታ ያለሽ ርግቤ ሆይ፣+

እስቲ ልይሽ፤ ድምፅሽንም ልስማው፤+

ድምፅሽ ማራኪ፣ ቁመናሽም ያማረ ነውና።’”+

15 “ቀበሮዎቹን ይኸውም የወይን እርሻዎቹን የሚያበላሹትን

ትናንሽ ቀበሮዎች ያዙልን፤

የወይን እርሻችን አብቧልና።”

16 “ውዴ የእኔ ነው፤ እኔም የእሱ ነኝ።+

መንጋውን በአበቦች መካከል እየጠበቀ ነው።+

17 የቀኑ ነፋስ መንፈስ ከመጀመሩና ጥላው ከመሸሹ በፊት

ውዴ ሆይ፣ እንደ ሜዳ ፍየል

ወይም በመካከላችን ባሉት ተራሮች* ላይ እንደሚገኝ የአጋዘን ግልገል በፍጥነት ተመለስ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ