የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መኃልየ መኃልይ 7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መኃልየ መኃልይ የመጽሐፉ ይዘት

    • ሱላማዊቷ በኢየሩሳሌም (3:6–8:4)

መኃልየ መኃልይ 7:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 4:5

መኃልየ መኃልይ 7:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 1:10
  • +መኃ 4:4
  • +መኃ 4:1
  • +ዘኁ 21:25፤ ኢያሱ 21:8, 39

መኃልየ መኃልይ 7:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ራስሽ።”

  • *

    ወይም “ታስሮ ተይዟል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 35:2
  • +መኃ 6:5
  • +አስ 8:15

መኃልየ መኃልይ 7:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 7:3፤ 8:10

መኃልየ መኃልይ 7:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ላንቃሽም።”

መኃልየ መኃልይ 7:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 2:16፤ 6:3

መኃልየ መኃልይ 7:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 1:14

መኃልየ መኃልይ 7:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አቆጥቁጦ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 2:13
  • +መኃ 6:11
  • +መኃ 1:2፤ 4:10

መኃልየ መኃልይ 7:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እንግሊዝኛ፣ ማንድሬክ። ከድንች ዝርያ የሚመደብ ተክል ሲሆን ብርቱካንማ ቀለም ያለው ፍሬ ያፈራል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 30:14
  • +መኃ 4:16

ተዛማጅ ሐሳብ

መኃ. 7:3መኃ 4:5
መኃ. 7:4መኃ 1:10
መኃ. 7:4መኃ 4:4
መኃ. 7:4መኃ 4:1
መኃ. 7:4ዘኁ 21:25፤ ኢያሱ 21:8, 39
መኃ. 7:5ኢሳ 35:2
መኃ. 7:5መኃ 6:5
መኃ. 7:5አስ 8:15
መኃ. 7:7መኃ 7:3፤ 8:10
መኃ. 7:10መኃ 2:16፤ 6:3
መኃ. 7:11መኃ 1:14
መኃ. 7:12መኃ 2:13
መኃ. 7:12መኃ 6:11
መኃ. 7:12መኃ 1:2፤ 4:10
መኃ. 7:13መኃ 4:16
መኃ. 7:13ዘፍ 30:14
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መኃልየ መኃልይ 7:1-13

መኃልየ መኃልይ

7 “አንቺ የተከበርሽ ልጃገረድ ሆይ፣

እግሮችሽ በነጠላ ጫማሽ ውስጥ ሲታዩ እንዴት ያምራሉ!

የዳሌዎችሽ ቅርጽ

የእጅ ባለሙያ የተጠበበባቸው ጌጦች ይመስላሉ።

 2 እምብርትሽ እንደ ክብ ሳህን ነው።

የተደባለቀ ወይን ጠጅ ከእሱ አይታጣ።

ሆድሽ ዙሪያውን በአበቦች እንደታጠረ

የስንዴ ክምር ነው።

 3 ሁለቱ ጡቶችሽ ሁለት ግልገሎችን፣

የሜዳ ፍየል መንታዎችን ይመስላሉ።+

 4 አንገትሽ+ በዝሆን ጥርስ የተሠራ ማማ ይመስላል።+

ዓይኖችሽ+ በባትራቢም በር አጠገብ እንዳሉት

የሃሽቦን+ ኩሬዎች ናቸው።

አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አቅጣጫ እንደሚመለከት

የሊባኖስ ማማ ነው።

 5 ራስሽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ+ አክሊል ሆኖልሻል፤

ፀጉርሽ*+ ሐምራዊ ሱፍ+ ይመስላል።

ንጉሡ በዘንፋላው ፀጉርሽ ተማርኳል።*

 6 አንቺ የተወደድሽ ልጃገረድ ሆይ፣ ምንኛ ውብ ነሽ! እንዴትስ ደስ ታሰኛለሽ!

በጣም ከሚያስደስቱ ነገሮች ሁሉ በላይ ትማርኪያለሽ!

 7 ቁመናሽ የዘንባባ ዛፍ ይመስላል፤

ጡቶችሽ ደግሞ የቴምር ዘለላ ይመስላሉ።+

 8 እኔም እንዲህ አልኩ፦ ‘የቴምር ዘለላዎቹን መያዝ እንድችል

ዛፉ ላይ እወጣለሁ።’

ጡቶችሽ እንደ ወይን ዘለላ ይሁኑ፤

የትንፋሽሽ መዓዛ እንደ ፖም ሽታ ይሁን፤

 9 አፍሽም* እንደ ምርጥ ወይን ጠጅ ይሁን።”

“ይህ የወይን ጠጅ ለውዴ እየተንቆረቆረ ይውረድ፤

በተኙ ሰዎች ከንፈር በቀስታ ይፍሰስ።

10 እኔ የውዴ ነኝ፤+

እሱም የሚመኘው እኔን ነው።

11 ውዴ ሆይ፣ ና፤

ወደ መስክ እንሂድ፤

በሂና ተክሎች+ መካከል እንቀመጥ።

12 ወይኑ ለምልሞ፣*

አበባው ፈክቶ፣+

የሮማን ዛፎቹም አብበው እንደሆነ ለማየት+

በማለዳ ተነስተን ወደ ወይን እርሻዎቹ እንሂድ።

እኔም በዚያ ለአንተ ያለኝን ፍቅር እገልጽልሃለሁ።+

13 የዱዳይም* ፍሬዎቹ+ መዓዛቸውን ሰጥተዋል፤

በደጆቻችንም ሁሉም ዓይነት ምርጥ ፍሬዎች አሉ።+

ውዴ ሆይ፣ አዲሶቹንም ሆነ በፊት የተቀጠፉትን ፍሬዎች

ለአንተ አስቀምጬልሃለሁ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ