ኢሳይያስ
1 የይሁዳ ነገሥታት+ በሆኑት በዖዝያ፣+ በኢዮዓታም፣+ በአካዝና+ በሕዝቅያስ+ ዘመን የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ* ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ፦+
2 ሰማያት ሆይ፣ ስሙ፤ ምድር ሆይ፣ አድምጪ፤+
ይሖዋ እንዲህ ሲል ተናግሯልና፦
5 በዓመፅ ላይ ዓመፅ የምትጨምሩት፣ አሁን ደግሞ ምናችሁ ላይ መመታት ፈልጋችሁ ነው?+
መላው ራስ ታሟል፤
መላው ልብም በበሽታ ተይዟል።+
6 ከእግር ጥፍር አንስቶ እስከ ራስ ፀጉር ድረስ አንድም ጤነኛ የአካል ክፍል የለም።
7 ምድራችሁ ባድማ ሆኗል።
ከተሞቻችሁ በእሳት ጋይተዋል።
የባዕድ አገር ሰዎች ዓይናችሁ እያየ ምድራችሁን ይውጣሉ።+
ባዕዳን እንዳወደሙት ጠፍ መሬት ሆኗል።+
10 እናንተ የሰዶም+ አምባገነኖች፣* የይሖዋን ቃል ስሙ።
እናንተ የገሞራ+ ሰዎች፣ የአምላካችንን ሕግ* አዳምጡ።
11 “የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምን ይጠቅመኛል?”+ ይላል ይሖዋ።
13 ከንቱ የሆኑትን የእህል መባዎች ከዚህ በኋላ አታምጡ።
ዕጣናችሁ በፊቴ አስጸያፊ ነው።+
የአዲስ ጨረቃ+ በዓልንና ሰንበትን+ ታከብራላችሁ፤ ስብሰባም+ ትጠራላችሁ።
በአንድ በኩል የተቀደሱ ጉባኤዎችን እያከበራችሁ በሌላ በኩል የምትፈጽሙትን አስማታዊ ድርጊት+ መታገሥ አልችልም።
14 የአዲስ ጨረቃ በዓሎቻችሁንና ሌሎች በዓሎቻችሁን ጠልቻለሁ።*
ለእኔ ሸክም ሆነውብኛል፤
እነሱንም ከመሸከሜ የተነሳ ዝያለሁ።
15 እጆቻችሁን ስትዘረጉ
ዓይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ።+
18 “ኑና በመካከላችን የተፈጠረውን ችግር ተወያይተን እንፍታ” ይላል ይሖዋ።+
19 እሺ ብትሉና ብትታዘዙ
የምድሪቱን መልካም ፍሬ ትበላላችሁ።+
21 ታማኝ የነበረችው ከተማ+ እንዴት ዝሙት አዳሪ ሆነች!+
23 አለቆችሽ ግትሮችና የሌባ ግብረ አበሮች ናቸው።+
ሁሉም ጉቦ የሚወዱና እጅ መንሻ የሚያሳድዱ ናቸው።+
24 ስለዚህ እውነተኛው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣
የእስራኤል ኃያል አምላክ እንዲህ ይላል፦
“እንግዲያው ስሙ! ባላጋራዎቼን አጠፋለሁ፤
ጠላቶቼንም እበቀላለሁ።+
26 መጀመሪያ ላይ እንደነበረው ፈራጆችሽን፣
እንደቀድሞውም አማካሪዎችሽን መልሼ አመጣለሁ።+
ከዚያ በኋላ የጽድቅ መዲና፣ የታመነች ከተማ ተብለሽ ትጠሪያለሽ።+
27 ጽዮን በፍትሕ፣
የሚመለሱት ነዋሪዎቿም በጽድቅ ይቤዣሉ።+
30 ቅጠሉ እንደጠወለገ ትልቅ ዛፍ፣+
ውኃም እንደሌለው የአትክልት ቦታ ትሆናላችሁና።