ኢሳይያስ
13 የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ+ በራእይ ያየው በባቢሎን ላይ የተላለፈ ፍርድ፦+
2 “በተራቆተ ዓለታማ ተራራ ላይ ምልክት* አቁሙ።+
ታላላቅ ሰዎች ወደሚገቡባቸው በሮች እንዲመጡ
ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጥሯቸው፤ እጃችሁንም አውለብልቡ።
ቁጣዬን ለመግለጥ
በኩራት ሐሴት የሚያደርጉትን ተዋጊዎቼን ጠርቻለሁ።
4 ስሙ! በተራሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ ያለ
የብዙ ሰዎች ድምፅ ይሰማል!
አዳምጡ! አንድ ላይ የተሰበሰቡ መንግሥታትና
ብሔራት+ ሁካታ ይሰማል!
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሠራዊቱን ለጦርነት አሰልፏል።+
6 የይሖዋ ቀን ቀርቧልና ዋይ ዋይ በሉ!
በዚያ ቀን ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ ዘንድ ጥፋት ይመጣል።+
7 ከዚህም የተነሳ እጆች ሁሉ ይዝላሉ፤
የሰዎችም ልብ ሁሉ በፍርሃት ይቀልጣል።+
8 ሰዎቹ እጅግ ተሸብረዋል።+
ምጥ እንደያዛት ሴት
ብርክና ሥቃይ ይዟቸዋል።
እርስ በርሳቸው በታላቅ ድንጋጤ ይተያያሉ፤
ፊታቸው በጭንቀት ቀልቷል።
11 ምድሪቱን ስለ ክፋቷ፣+
ክፉዎችንም ስለ በደላቸው እቀጣለሁ።
የእብሪተኞችን ኩራት አጠፋለሁ፤
የጨቋኞችንም ትዕቢት አዋርዳለሁ።+
15 የተገኘ ሁሉ ይወጋል፤
የተያዘም ሁሉ በሰይፍ ይወድቃል።+
20 ከዚያ በኋላ የሚቀመጥባት አይኖርም፤
እንዲሁም ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ የመኖሪያ ቦታ አትሆንም።+
በዚያም ዓረብ ድንኳኑን አይተክልም፤
እረኞችም መንጎቻቸውን በዚያ አያሳርፉም።
21 የበረሃ ፍጥረታት በዚያ ይተኛሉ፤
ቤቶቻቸው በጉጉቶች ይሞላሉ።
22 የሚያላዝኑ ፍጥረታት በማማዎቿ፣
ቀበሮዎችም በሚያማምሩ ቤተ መንግሥቶቿ ውስጥ ሆነው ይጮኻሉ።
ጊዜዋ ቀርቧል፤ ቀኖቿም አይራዘሙም።”+