ኢሳይያስ
22 ስለ ራእይ ሸለቆ* የተነገረ የፍርድ መልእክት፦+
ሁላችሁም ጣሪያ ላይ የወጣችሁት ምን ሆናችሁ ነው?
2 አንቺ ሁከት የነገሠብሽ መዲና፣ የፈንጠዝያም ከተማ፣
በትርምስ ተሞልተሻል።
ነዋሪዎችሽ ያለቁት በሰይፍ
ወይም በጦርነት ተገድለው አይደለም።+
3 አምባገነን መሪዎችሽ ሁሉ በአንድ ላይ ሸሽተዋል።+
ሆኖም ቀስት መጠቀም ሳያስፈልግ ተማርከዋል።
ወደ ሩቅ ቦታ ሸሽተው ቢሄዱም
የተገኙት ሁሉ ተማርከዋል።+
4 ስለዚህ እንዲህ አልኩ፦ “ዓይናችሁን ከእኔ ላይ አንሱ፤
እኔም አምርሬ አለቅሳለሁ።+
“አንተም በዚያ ቀን የደኑን የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት ትመለከታለህ፤ 9 እናንተም በዳዊት ከተማ ቅጥር ላይ ያሉትን በርካታ ክፍተቶች ትመለከታላችሁ።+ በታችኛውም ኩሬ ውኃ ታጠራቅማላችሁ።+ 10 የኢየሩሳሌምን ቤቶች ትቆጥራላችሁ፤ ቅጥሩንም ለማጠናከር ቤቶቹን ታፈርሳላችሁ። 11 በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በድሮው ኩሬ ላለው ውኃ የሚሆን ማጠራቀሚያ ትሠራላችሁ፤ ይሁንና ይህን ወዳደረገው ታላቅ አምላክ አትመለከቱም፤ ከዘመናት በፊት ወደሠራውም አምላክ አታዩም።
‘ነገ ስለምንሞት እንብላ፣ እንጠጣ’ ትላላችሁ።”+
14 ከዚያም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በጆሮዬ ይህን ገለጠልኝ፦ “‘እናንተ እስክትሞቱ ድረስ ይህ በደል አይሰረይላችሁም’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።”
15 ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በቤቱ* ላይ ወደተሾመው ወደ መጋቢው ወደ ሸብና+ ሄደህ እንዲህ በለው፦ 16 ‘በዚህ ለራስህ የመቃብር ቦታ የወቀርከው፣ የአንተ የሆነ ምን ነገር ቢኖርህ ነው? በዚህስ የአንተ የሆነ ማን አለ? በከፍታ ቦታ የራሱን መቃብር ወቅሯል፤ ቋጥኝ ጠርቦ ለራሱ ማረፊያ ስፍራ* አዘጋጅቷል። 17 ‘አንተ ሰው፣ እነሆ፣ ይሖዋ በኃይል አሽቀንጥሮ ይጥልሃል፤ ጨምድዶም ይይዝሃል። 18 ጠቅልሎና አጡዞ እንደ ኳስ ወደ ሰፊ ምድር ይወረውርሃል። በዚያ ትሞታለህ፤ ያማሩ ሠረገሎችህም በዚያ ለጌታህ ቤት ውርደት ይሆናሉ። 19 እኔም ከሹመትህ እሽርሃለሁ፤ ከኃላፊነትህም አባርርሃለሁ።
20 “‘በዚያም ቀን አገልጋዬን የኬልቅያስን ልጅ ኤልያቄምን+ እጠራለሁ፤ 21 ቀሚስህን አለብሰዋለሁ፤ መታጠቂያህንም በደንብ አስታጥቀዋለሁ፤+ ሥልጣንህንም* በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። እሱም ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና ለይሁዳ ቤት አባት ይሆናል። 22 የዳዊትንም ቤት ቁልፍ+ በትከሻው ላይ አደርጋለሁ። እሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋም፤ እሱ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍትም። 23 በአስተማማኝ ቦታ ላይ እንደ ማንጠልጠያ እተክለዋለሁ፤ ለአባቱም ቤት እንደ ክብር ዙፋን ይሆናል። 24 በእሱም ላይ የአባቱን ቤት ክብር* በሙሉ፣ ልጆቹንና ዘሮቹን* ይኸውም ትናንሾቹን ዕቃዎች በሙሉ፣ ጎድጓዳ ሳህኖቹንና ትላልቆቹን እንስራዎች ሁሉ ይሰቅሉበታል።
25 “‘በዚያም ቀን’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ ‘በአስተማማኝ ቦታ ላይ የተተከለው ማንጠልጠያ ይነቀላል፤+ ተቆርጦም ይወድቃል፤ በላዩ ላይ የተንጠለጠለው ሸክምም ወድቆ ይከሰከሳል፤ ይሖዋ ራሱ ተናግሯልና።’”