የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 27
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኢሳይያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ይሖዋ ሌዋታንን ይገድለዋል (1)

      • በወይን እርሻ ለተመሰለችው እስራኤል የተዘመረ መዝሙር (2-13)

ኢሳይያስ 27:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 32:41፤ ኤር 47:6

ኢሳይያስ 27:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እዚህ ላይ በአንስታይ ፆታ የተገለጸችውና በወይን እርሻ የተመሰለችው እስራኤል ልትሆን ትችላለች።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 80:8፤ ኢሳ 5:1፤ ኤር 2:21

ኢሳይያስ 27:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 33:29
  • +ኢሳ 35:6፤ 41:18፤ 58:11
  • +መዝ 121:4፤ ኢሳ 46:3, 4

ኢሳይያስ 27:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 85:2, 3፤ ኢሳ 12:1

ኢሳይያስ 27:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 39:25፤ ሆሴዕ 14:5
  • +ኢሳ 60:21, 22፤ ኤር 30:18, 19

ኢሳይያስ 27:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 4:11፤ ሕዝ 13:13

ኢሳይያስ 27:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 4:4፤ 48:10
  • +ሚክ 5:13, 14

ኢሳይያስ 27:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 6:11, 12፤ ኤር 26:18፤ ሰቆ 2:5፤ ሕዝ 36:4
  • +ኢሳ 32:14

ኢሳይያስ 27:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 32:28፤ ኢሳ 1:3፤ ኤር 4:22፤ ሆሴዕ 4:6
  • +2ዜና 36:15, 16፤ ሕዝ 9:9, 10

ኢሳይያስ 27:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ኤፍራጥስን ያመለክታል።

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 34:2, 5
  • +ዘዳ 30:3፤ ነህ 1:9፤ ኢሳ 11:11, 12፤ አሞጽ 9:14

ኢሳይያስ 27:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 49:22፤ 62:10
  • +2ነገ 17:6፤ ኢሳ 11:16፤ ሆሴዕ 9:3
  • +ኤር 43:4, 7፤ ዘካ 10:10
  • +ኢሳ 2:3፤ 25:6፤ 52:1፤ ኤር 3:17

ተዛማጅ ሐሳብ

ኢሳ. 27:1ዘዳ 32:41፤ ኤር 47:6
ኢሳ. 27:2መዝ 80:8፤ ኢሳ 5:1፤ ኤር 2:21
ኢሳ. 27:3ዘዳ 33:29
ኢሳ. 27:3ኢሳ 35:6፤ 41:18፤ 58:11
ኢሳ. 27:3መዝ 121:4፤ ኢሳ 46:3, 4
ኢሳ. 27:4መዝ 85:2, 3፤ ኢሳ 12:1
ኢሳ. 27:6ሕዝ 39:25፤ ሆሴዕ 14:5
ኢሳ. 27:6ኢሳ 60:21, 22፤ ኤር 30:18, 19
ኢሳ. 27:8ኤር 4:11፤ ሕዝ 13:13
ኢሳ. 27:9ኢሳ 4:4፤ 48:10
ኢሳ. 27:9ሚክ 5:13, 14
ኢሳ. 27:10ኢሳ 6:11, 12፤ ኤር 26:18፤ ሰቆ 2:5፤ ሕዝ 36:4
ኢሳ. 27:10ኢሳ 32:14
ኢሳ. 27:11ዘዳ 32:28፤ ኢሳ 1:3፤ ኤር 4:22፤ ሆሴዕ 4:6
ኢሳ. 27:112ዜና 36:15, 16፤ ሕዝ 9:9, 10
ኢሳ. 27:12ዘኁ 34:2, 5
ኢሳ. 27:12ዘዳ 30:3፤ ነህ 1:9፤ ኢሳ 11:11, 12፤ አሞጽ 9:14
ኢሳ. 27:13ኢሳ 49:22፤ 62:10
ኢሳ. 27:132ነገ 17:6፤ ኢሳ 11:16፤ ሆሴዕ 9:3
ኢሳ. 27:13ኤር 43:4, 7፤ ዘካ 10:10
ኢሳ. 27:13ኢሳ 2:3፤ 25:6፤ 52:1፤ ኤር 3:17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኢሳይያስ 27:1-13

ኢሳይያስ

27 በዚያን ቀን ይሖዋ፣ በፍጥነት እየተሳበ የሚሄደውን እባብ ሌዋታንን፣*

ደግሞም እየተጥመለመለ የሚጓዘውን እባብ ሌዋታንን

ትልቅ፣ ኃይለኛና ምሕረት የለሽ በሆነው ሰይፉ ይቀጣዋል፤+

በባሕር ውስጥ ያለውንም ግዙፍ ፍጥረት ይገድለዋል።

 2 በዚያ ቀን ለእሷ* እንዲህ ብላችሁ ዘምሩ፦

“የሚፈላ የወይን ጠጅ የሚመረትባት የወይን እርሻ!+

 3 እኔ ይሖዋ እጠብቃታለሁ።+

በየጊዜው ውኃ አጠጣታለሁ።+

ማንም ጉዳት እንዳያደርስባት

ሌት ተቀን እጠብቃታለሁ።+

 4 ከእንግዲህ አልቆጣትም።+

በውጊያው ላይ ቁጥቋጦና አረም ይዞ የሚገጥመኝ ማን ነው?

ሁሉንም በአንድ ላይ እረግጣቸዋለሁ፤ በእሳትም አቃጥላቸዋለሁ።

 5 አለዚያ ምሽጌን የሙጥኝ ይበል።

ከእኔ ጋር ሰላም ይፍጠር፤

አዎ፣ ከእኔ ጋር ሰላም ይፍጠር።”

 6 በመጪዎቹ ቀናት ያዕቆብ ሥር ይሰዳል፤

እስራኤል ያብባል እንዲሁም ይለመልማል፤+

ምድሩንም በምርት ይሞሉታል።+

 7 እሱ አሁን በተመታበት ሁኔታ መመታቱ ተገቢ ነው?

ወይስ የተገደሉበት ሰዎች በተፈጁበት መንገድ መገደሉ አስፈላጊ ነው?

 8 እሷን በምትልካት ጊዜ በአስደንጋጭ ጩኸት ትፋለማታለህ።

የምሥራቅ ነፋስ በሚነፍስበት ቀን በኃይለኛ አውሎ ነፋሱ ያስወግዳታል።+

 9 በመሆኑም የያዕቆብ በደል በዚህ መንገድ ይሰረይለታል፤+

ኃጢአቱ በሚወገድበት ጊዜ ፍሬው በሙሉ ይህ ይሆናል፦

የመሠዊያ ድንጋዮቹን ሁሉ

እንደደቀቀ የኖራ ድንጋይ ያደርጋል፤

የማምለኪያ ግንዶቹም* ሆኑ የዕጣን ማጨሻዎቹ አይተርፉም።+

10 የተመሸገችው ከተማ ትተዋለችና፤

የግጦሽ መሬቱም ወና ይሆናል፤ እንደ ምድረ በዳም የተተወ ይሆናል።+

በዚያ ጥጃ ይግጣል፤ ይተኛልም፤

ቅርንጫፎቿንም ይበላል።+

11 ቀንበጦቿ በሚደርቁበት ጊዜ

ሴቶች መጥተው ይሰብሯቸዋል፤

ከዚያም ማገዶ ያደርጓቸዋል።

ይህ ሕዝብ ማስተዋል ይጎድለዋልና።+

በዚህም ምክንያት ፈጣሪያቸው ምንም ምሕረት አያደርግላቸውም፤

ሠሪያቸውም ምንም ዓይነት ሞገስ አያሳያቸውም።+

12 በዚያም ቀን የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ሰው ዛፍ ላይ ያሉ ፍሬዎችን አርግፎ አንድ በአንድ እንደሚለቅም ሁሉ፣ ይሖዋም ከታላቁ ወንዝ* አንስቶ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝ*+ ድረስ ባለው ቦታ ሁሉ የተበተናችሁትን ይሰበስባችኋል።+ 13 በዚያም ቀን ትልቅ ቀንደ መለከት ይነፋል፤+ በአሦር ምድር+ የጠፉትና በግብፅ ምድር+ የተበተኑት መጥተው በኢየሩሳሌም በሚገኘው ቅዱስ ተራራ ላይ ለይሖዋ ይሰግዳሉ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ