ኢሳይያስ
41 “እናንተ ደሴቶች፣ ዝም ብላችሁ አዳምጡኝ፤*
ብሔራትም ኃይላቸውን ያድሱ።
በመጀመሪያ ይቅረቡ፤ ከዚያም ይናገሩ።+
ለፍርድ አንድ ላይ እንሰብሰብ።
በሰይፉ ፊት አቧራ የሚያደርጋቸው፣
በቀስቱ ፊት በነፋስ እንደተወሰደ ገለባ የሚያደርጋቸው ማን ነው?
3 እግሩ ባልረገጠው መንገድ በመጓዝ
ምንም ነገር ሳያግደው እነሱን ያሳድዳል።
4 ይህን የሠራና ያደረገ፣
ትውልዶቹንም ከመጀመሪያ አንስቶ የጠራ ማን ነው?
5 ደሴቶች አይተው ፈሩ።
የምድር ዳርቻዎች ተንቀጠቀጡ።
ቀረቡ፤ ወደ ፊትም መጡ።
6 እያንዳንዱም ባልንጀራውን ይረዳል፤
ወንድሙንም “አይዞህ፣ በርታ” ይለዋል።
ብየዳውን በተመለከተ “ጥሩ ነው” ይላል።
ከዚያም ጣዖቱ እንዳይወድቅ አንድ ሰው በምስማር ይቸነክረዋል።
8 “እስራኤል ሆይ፣ አንተ ግን አገልጋዬ ነህ፤+
ያዕቆብ ሆይ፣ አንተን መርጬሃለሁ፤+
የወዳጄ የአብርሃም ዘር ነህ፤+
9 አንተን ከምድር ዳርቻዎች ወሰድኩህ፤+
እጅግ ርቀው ከሚገኙ ቦታዎችም ጠራሁህ።
10 እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ።+
እኔ አምላክህ ነኝና አትጨነቅ።+
አበረታሃለሁ፤ አዎ እረዳሃለሁ፤+
በጽድቅ ቀኝ እጄ አጥብቄ እይዝሃለሁ።’
11 እነሆ፣ በአንተ ላይ የተቆጡ ሁሉ ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉም።+
ከአንተ ጋር የሚጣሉ ሁሉ እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ ይጠፋሉም።+
12 ከአንተ ጋር የሚፋለሙትን ሰዎች ትፈልጋቸዋለህ፤ ሆኖም አታገኛቸውም፤
ከአንተ ጋር የሚዋጉ ሰዎች እንደሌሉና ፈጽሞ እንዳልነበሩ ያህል ይሆናሉ።+
13 ‘አትፍራ። እረዳሃለሁ’ የምልህ
እኔ፣ አምላክህ ይሖዋ ቀኝ እጅህን ይዣለሁና።+
15 “እነሆ፣ ማሄጃ፣ በሁለቱም በኩል የተሳሉ ጥርሶች ያሉት
አዲስ የመውቂያ መሣሪያ አድርጌሃለሁ።+
አንተም ተራሮቹን ረግጠህ ታደቃቸዋለህ፤
ኮረብቶቹንም እንደ ገለባ ታደርጋቸዋለህ።
16 ወደ ላይ ትበትናቸዋለህ፤
ነፋስም ይወስዳቸዋል፤
አውሎ ነፋስ ይበትናቸዋል።
17 “ችግረኞችና ድሆች ውኃ ይፈልጋሉ፤ ሆኖም አያገኙም።
ከመጠማታቸው የተነሳ ምላሳቸው ደርቋል።+
እኔ ይሖዋ እመልስላቸዋለሁ።+
እኔ የእስራኤል አምላክ አልተዋቸውም።+
ምድረ በዳውን ቄጠማ የሞላበት ኩሬ፣
ውኃ የሌለበትንም ምድር የውኃ ምንጭ አደርጋለሁ።+
19 በበረሃ አርዘ ሊባኖስ፣
ግራር፣ አደስና ዘይት የሚሰጥ ዛፍ እተክላለሁ።+
በበረሃማ ሜዳ የጥድ ዛፍ፣
የአሽ ዛፍና* የፈረንጅ ጥድ በአንድነት እተክላለሁ፤+
20 ይህም የሚሆነው የይሖዋ እጅ ይህን እንዳደረገና
የእስራኤል ቅዱስ ይህን እንደፈጠረ
ሰዎች ሁሉ እንዲያዩና እንዲያውቁ፣
ልብ እንዲሉና በጥልቅ እንዲያስተውሉ ነው።”+
21 “ሙግታችሁን አቅርቡ” ይላል ይሖዋ።
“የመከራከሪያ ሐሳባችሁን አሰሙ” ይላል የያዕቆብ ንጉሥ።
22 “ማስረጃ አቅርቡ፤ እንዲሁም ወደፊት የሚሆኑትን ነገሮች ንገሩን።
ወይም የሚመጡትን ነገሮች አሳውቁን።+
23 አማልክት መሆናችሁን እንድናውቅ
ወደፊት የሚሆነውን ነገር ንገሩን።+
አዎ፣ አይተን በአድናቆት እንድንዋጥ
መልካምም ሆነ ክፉ፣ የሆነ ነገር አድርጉ።+
24 እነሆ፣ እናንተ ጨርሶ ሕልውና የሌላችሁ ናችሁ፤
ምንም የምታከናውኑት ነገር የለም።+
እናንተን የሚመርጥ ሁሉ አስጸያፊ ነው።+
26 እኛ እናውቅ ዘንድ ስለዚህ ነገር ከመጀመሪያው የተናገረ
ወይም ‘እሱ ትክክል ነው’ እንድንል ከጥንት ጀምሮ የተናገረ ማን ነው?+
በእርግጥ የተናገረ የለም!
ያሳወቀም የለም!
ከእናንተ አንዳች ነገር የሰማ የለም!”+
27 ከማንም በፊት ጽዮንን “ወደፊት የሚሆነውን ነገር ተመልከቺ!” ያልኩት እኔ ነኝ፤+
ለኢየሩሳሌምም ምሥራች ነጋሪ እልካለሁ።+
28 ሆኖም እኔ መመልከቴን ቀጠልኩ፤ አንድም ሰው አልነበረም፤
ከእነሱ መካከል ምክር የሚሰጥ አልነበረም።
እኔም መልስ እንዲሰጡ መጠየቄን ቀጠልኩ።
29 እነሆ፣ ሁሉም ቅዠት* ናቸው።
ሥራቸው ከንቱ ነው።