የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 44
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኢሳይያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • አምላክ የመረጠው ሕዝብ የሚያገኘው በረከት (1-5)

      • ከይሖዋ በቀር ሌላ አምላክ የለም (6-8)

      • ሰው ሠራሽ ጣዖታት ከንቱ ናቸው (9-20)

      • እስራኤልን የሚቤዠው ይሖዋ (21-23)

      • በቂሮስ አማካኝነት ቀድሞ ወደነበሩበት ሁኔታ ይመለሳሉ (24-28)

ኢሳይያስ 44:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 17:1, 7፤ 35:10, 11፤ ኢሳ 41:8

ኢሳይያስ 44:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከተወለድክበት ጊዜ።”

  • *

    “ቅን የሆነ” የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን ለእስራኤል የተሰጠ የማዕረግ ስም ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 43:1፤ 44:21
  • +ዘዳ 32:15፤ 33:5, 26
  • +ኢሳ 41:10፤ ኤር 30:10

ኢሳይያስ 44:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለተጠማው ምድር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 41:17
  • +ኢሳ 32:14, 15

ኢሳይያስ 44:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 61:11

ኢሳይያስ 44:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘካ 13:9

ኢሳይያስ 44:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 33:5፤ ኢሳ 33:22
  • +ዘፀ 6:6፤ ኤር 50:34
  • +ኢሳ 41:4፤ 48:12፤ ራእይ 22:13
  • +ዘዳ 4:35, 39፤ ኢሳ 43:10

ኢሳይያስ 44:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 46:9
  • +ኢሳ 43:9፤ 45:21

ኢሳይያስ 44:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 41:10
  • +ኢሳ 43:10
  • +ዘዳ 32:4፤ 2ሳሙ 22:32

ኢሳይያስ 44:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ምስሎቹን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 10:14፤ 1ነገ 18:26፤ 1ቆሮ 8:4
  • +መዝ 115:4, 5
  • +ኤር 51:17

ኢሳይያስ 44:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቀልጦ የተሠራ ሐውልት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 10:5፤ ሥራ 19:26

ኢሳይያስ 44:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 5:3, 7

ኢሳይያስ 44:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በገጀራው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 40:19፤ 41:7፤ 46:6

ኢሳይያስ 44:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በአምልኮ ቦታው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:4፤ ዘዳ 4:15, 16፤ ሥራ 17:29
  • +ዘዳ 27:15

ኢሳይያስ 44:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 40:20፤ ኤር 10:3

ኢሳይያስ 44:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:4, 5፤ ዘሌ 26:1፤ ዕን 2:18, 19

ኢሳይያስ 44:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 37:37, 38፤ 45:20፤ 46:7

ኢሳይያስ 44:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 10:8, 14፤ ሮም 1:21-23

ኢሳይያስ 44:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከዛፍ ተቆርጦ ለደረቀ ጉማጅ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 27:15

ኢሳይያስ 44:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሱን።”

ኢሳይያስ 44:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 43:1፤ 44:1
  • +ኢሳ 49:15

ኢሳይያስ 44:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 51:1፤ 103:12፤ ኢሳ 1:18፤ 43:25፤ ኤር 33:8፤ ሥራ 3:19
  • +ኢሳ 1:27፤ 48:20፤ 59:20

ኢሳይያስ 44:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 49:13፤ 55:12
  • +ኢሳ 60:21

ኢሳይያስ 44:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 44:6
  • +ኢዮብ 26:7፤ ኢሳ 40:22
  • +ኢሳ 42:5፤ 48:13

ኢሳይያስ 44:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሐሰተኛ ነቢያትን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሆሴዕ 9:7
  • +2ሳሙ 15:31፤ ኢሳ 29:14

ኢሳይያስ 44:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 23:14፤ ኢሳ 55:10, 11፤ ዘካ 1:6
  • +መዝ 147:2
  • +ኢሳ 60:10
  • +ኢሳ 61:4

ኢሳይያስ 44:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 42:15፤ ኤር 50:38፤ ራእይ 16:12

ኢሳይያስ 44:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 1:1, 2፤ ኢሳ 41:25፤ 45:1፤ 46:11፤ ዳን 10:1
  • +ኢሳ 48:14
  • +2ዜና 36:22, 23፤ ዕዝራ 6:3፤ ኢሳ 45:13

ተዛማጅ ሐሳብ

ኢሳ. 44:1ዘፍ 17:1, 7፤ 35:10, 11፤ ኢሳ 41:8
ኢሳ. 44:2ኢሳ 43:1፤ 44:21
ኢሳ. 44:2ዘዳ 32:15፤ 33:5, 26
ኢሳ. 44:2ኢሳ 41:10፤ ኤር 30:10
ኢሳ. 44:3ኢሳ 41:17
ኢሳ. 44:3ኢሳ 32:14, 15
ኢሳ. 44:4ኢሳ 61:11
ኢሳ. 44:5ዘካ 13:9
ኢሳ. 44:6ዘዳ 33:5፤ ኢሳ 33:22
ኢሳ. 44:6ዘፀ 6:6፤ ኤር 50:34
ኢሳ. 44:6ኢሳ 41:4፤ 48:12፤ ራእይ 22:13
ኢሳ. 44:6ዘዳ 4:35, 39፤ ኢሳ 43:10
ኢሳ. 44:7ኢሳ 46:9
ኢሳ. 44:7ኢሳ 43:9፤ 45:21
ኢሳ. 44:8ኢሳ 41:10
ኢሳ. 44:8ኢሳ 43:10
ኢሳ. 44:8ዘዳ 32:4፤ 2ሳሙ 22:32
ኢሳ. 44:9መሳ 10:14፤ 1ነገ 18:26፤ 1ቆሮ 8:4
ኢሳ. 44:9መዝ 115:4, 5
ኢሳ. 44:9ኤር 51:17
ኢሳ. 44:10ኤር 10:5፤ ሥራ 19:26
ኢሳ. 44:111ሳሙ 5:3, 7
ኢሳ. 44:12ኢሳ 40:19፤ 41:7፤ 46:6
ኢሳ. 44:13ዘፀ 20:4፤ ዘዳ 4:15, 16፤ ሥራ 17:29
ኢሳ. 44:13ዘዳ 27:15
ኢሳ. 44:14ኢሳ 40:20፤ ኤር 10:3
ኢሳ. 44:15ዘፀ 20:4, 5፤ ዘሌ 26:1፤ ዕን 2:18, 19
ኢሳ. 44:17ኢሳ 37:37, 38፤ 45:20፤ 46:7
ኢሳ. 44:18ኤር 10:8, 14፤ ሮም 1:21-23
ኢሳ. 44:19ዘዳ 27:15
ኢሳ. 44:21ኢሳ 43:1፤ 44:1
ኢሳ. 44:21ኢሳ 49:15
ኢሳ. 44:22መዝ 51:1፤ 103:12፤ ኢሳ 1:18፤ 43:25፤ ኤር 33:8፤ ሥራ 3:19
ኢሳ. 44:22ኢሳ 1:27፤ 48:20፤ 59:20
ኢሳ. 44:23ኢሳ 49:13፤ 55:12
ኢሳ. 44:23ኢሳ 60:21
ኢሳ. 44:24ኢሳ 44:6
ኢሳ. 44:24ኢዮብ 26:7፤ ኢሳ 40:22
ኢሳ. 44:24ኢሳ 42:5፤ 48:13
ኢሳ. 44:25ሆሴዕ 9:7
ኢሳ. 44:252ሳሙ 15:31፤ ኢሳ 29:14
ኢሳ. 44:26ኢያሱ 23:14፤ ኢሳ 55:10, 11፤ ዘካ 1:6
ኢሳ. 44:26መዝ 147:2
ኢሳ. 44:26ኢሳ 60:10
ኢሳ. 44:26ኢሳ 61:4
ኢሳ. 44:27ኢሳ 42:15፤ ኤር 50:38፤ ራእይ 16:12
ኢሳ. 44:28ዕዝራ 1:1, 2፤ ኢሳ 41:25፤ 45:1፤ 46:11፤ ዳን 10:1
ኢሳ. 44:28ኢሳ 48:14
ኢሳ. 44:282ዜና 36:22, 23፤ ዕዝራ 6:3፤ ኢሳ 45:13
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኢሳይያስ 44:1-28

ኢሳይያስ

44 “አሁን ግን፣ አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣

የመረጥኩህም እስራኤል ሆይ፣+ ስማ።

 2 የሠራህና ያበጀህ፣+

ከማህፀን* ጀምሮ የረዳህ

ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

‘አገልጋዬ ያዕቆብ፣

የመረጥኩህም የሹሩን*+ ሆይ፣ አትፍራ።+

 3 ለተጠማው* ውኃ አፈሳለሁና፤+

በደረቁ ምድርም ላይ ጅረቶች እንዲፈስሱ አደርጋለሁ።

መንፈሴን በዘርህ ላይ፣

በረከቴንም በልጅ ልጆችህ ላይ አፈሳለሁ።+

 4 እነሱም በለምለም ሣር መካከል፣

በጅረቶችም ዳር እንዳሉ የአኻያ ዛፎች ይበቅላሉ።+

 5 አንዱ “እኔ የይሖዋ ነኝ” ይላል።+

ሌላውም ራሱን በያዕቆብ ስም ይጠራል፤

ሌላው ደግሞ በእጁ ላይ “የይሖዋ ነኝ” ብሎ ይጽፋል።

ደግሞም ራሱን በእስራኤል ስም ይጠራል።’

 6 የእስራኤል ንጉሥ+ የሆነውና እስራኤልን የተቤዠው+ ይሖዋ፣

የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

‘የመጀመሪያው እኔ ነኝ፤ የመጨረሻውም እኔ ነኝ።+

ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም።+

 7 እንደ እኔ ያለ ማን ነው?+

በድፍረት ይናገር፤ ያሳውቅም፤ ማስረጃውንም ለእኔ ያቅርብ!+

የጥንቱን ሕዝብ ካቋቋምኩበት ጊዜ ጀምሮ፣

በቅርቡ የሚከሰቱትንና

ወደፊት የሚሆኑትን ነገሮች ይናገሩ።

 8 ስጋት አይደርባችሁ፤

በፍርሃትም አትሽመድመዱ።+

አስቀድሜ ለእያንዳንዳችሁ አልነገርኳችሁም? ደግሞስ አላሳወቅኳችሁም?

እናንተ ምሥክሮቼ ናችሁ።+

ከእኔ ሌላ አምላክ አለ?

በፍጹም፣ ሌላ ዓለት የለም፤+ እኔ የማውቀው አንድም የለም።’”

 9 የተቀረጹ ምስሎችን የሚሠሩ ሁሉ ከንቱ ናቸው፤

የሚወዷቸውም ጣዖቶች ምንም ጥቅም የላቸውም።+

እንደ ምሥክሮቻቸው እነሱም* ምንም አያዩም፤ ምንም አያውቁም፤+

በመሆኑም ሠሪዎቻቸው ለኀፍረት ይዳረጋሉ።+

10 ለምንም የማይጠቅም አምላክ የሚሠራ

ወይም የብረት ምስል* የሚያበጅ ማን ነው?+

11 እነሆ፣ ባልደረቦቹ ሁሉ ያፍራሉ!+

የእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹ ተራ ሰዎች ናቸው።

ሁሉም ተሰብስበው ይቁሙ።

በፍርሃት ይዋጣሉ፤ ሁሉም ያፍራሉ።

12 አንጥረኛ በመሣሪያው* ተጠቅሞ ብረቱን በከሰል ፍም ላይ ይሠራዋል።

ብርቱ በሆነው ክንዱ

በመዶሻ ቅርጽ ይሰጠዋል።+

ከዚያም ይርበዋል፤ ጉልበትም ያጣል፤

ውኃ ስለማይጠጣ ይደክማል።

13 እንጨት ጠራቢው በገመድ ይለካል፤ በቀይ ጠመኔም ንድፍ ያወጣል።

በመሮም ይጠርበዋል፤ በማክበቢያም ምልክት ያደርግበታል።

በሰው አምሳል ይቀርጸዋል፤+

የሰውንም ውበት ያላብሰዋል፤

ከዚያም ቤት ውስጥ* ያስቀምጠዋል።+

14 አርዘ ሊባኖስ የሚቆርጥ ሰው አለ።

እሱም አንድ የዛፍ ዝርያ ይኸውም የባሉጥ ዛፍ ይመርጣል፤

እስኪጠነክርለት ድረስ በጫካው ውስጥ ባሉት ዛፎች መካከል ይተወዋል።+

የላውሮ ዛፍ ይተክላል፤ ዝናብም ያሳድገዋል።

15 ከዚያም ሰው ለማገዶ ይጠቀምበታል።

የተወሰነውን እንጨት ወስዶ በማንደድ እሳት ይሞቃል፤

እሳት አያይዞም ዳቦ ይጋግራል።

ይሁንና አምላክ ሠርቶም ያመልከዋል።

የተቀረጸ ምስል ሠርቶበት በፊቱ ይደፋል።+

16 ግማሹን በእሳት ያነደዋል፤

በዚያም ላይ የሚበላውን ሥጋ ይጠብሳል፤ በልቶም ይጠግባል።

እሳቱንም እየሞቀ

“እሰይ! እሳቱን እያየሁ ሞቅኩ” ይላል።

17 የቀረውን ግን ምስል ይቀርጽበታል፤ አምላክ አድርጎም ይሠራዋል።

በፊቱም ተደፍቶ ይሰግድለታል።

“አንተ አምላኬ ነህና አድነኝ” ብሎ

ወደ እሱ ይጸልያል።+

18 ምንም አያውቁም እንዲሁም አያስተውሉም፤+

ምክንያቱም ዓይኖቻቸው ተጨፍነዋል፤ ማየትም አይችሉም፤

ልባቸውም ማስተዋል ጎድሎታል።

19 ቆም ብሎ በልቡ ያሰበ

ወይም እውቀትም ሆነ ማስተዋል ኖሮት እንዲህ ብሎ የተናገረ የለም፦

“ግማሹን እሳት አንድጄበታለሁ፤

በፍሙም ላይ ዳቦ ጋግሬአለሁ፤ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ።

ታዲያ በቀረው እንጨት አስጸያፊ ነገር መሥራቴ ተገቢ ነው?+

ከዛፍ ለተቆረጠ እንጨት* መስገድ ይገባኛል?”

20 እሱ አመድ ይበላል።

የተታለለው የገዛ ልቡ አስቶታል።

ራሱን* ሊያድን አይችልም፤

ደግሞም “በቀኝ እጄ ያለው ውሸት አይደለም?” አይልም።

21 “ያዕቆብ ሆይ፣ አንተም እስራኤል ሆይ፣

አገልጋዬ ስለሆንክ እነዚህን ነገሮች አስታውስ።

እኔ ሠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ አገልጋይ ነህ።+

እስራኤል ሆይ፣ አልረሳህም።+

22 በደልህን በደመና፣

ኃጢአትህንም ጥቅጥቅ ባለ ደመና እሸፍነዋለሁ።+

ወደ እኔ ተመለስ፤ እኔም እቤዥሃለሁ።+

23 እናንተ ሰማያት በደስታ እልል በሉ!

ይሖዋ እርምጃ ወስዷልና።

እናንተ ጥልቅ የምድር ክፍሎች በድል አድራጊነት ጩኹ!

እናንተ ተራሮች፣ አንተም ደን ሆይ፣

በውስጡም ያላችሁ ዛፎች ሁሉ በደስታ እልል በሉ!+

ይሖዋ ያዕቆብን ተቤዥቷልና፤

በእስራኤልም ላይ ግርማውን ገልጧል።”+

24 የተቤዠህና+ ከማህፀን ጀምሮ የሠራህ

ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“ሁሉንም ነገር የሠራሁ እኔ ይሖዋ ነኝ።

ብቻዬን ሰማያትን ዘረጋሁ፤+

ምድርንም ሠራሁ።+

ያኔ ከእኔ ጋር ማን ነበር?

25 የሆነ ያልሆነውን የሚቀባጥሩ ሰዎችን* ምልክቶች አከሽፋለሁ፤

ሟርተኞችንም ነፈዝ አደርጋለሁ፤+

ጥበበኞቹንም ግራ አጋባለሁ፤

እውቀታቸውንም ሞኝነት አደርጋለሁ፤+

26 የአገልጋዬን ቃል እውን አደርጋለሁ፤

የመልእክተኞቼንም ትንቢት ሙሉ በሙሉ እፈጽማለሁ፤+

ስለ ኢየሩሳሌም ‘የሰው መኖሪያ ትሆናለች’፤+

ስለ ይሁዳ ከተሞችም ‘ዳግም ይገነባሉ፤+

ፍርስራሾቿንም መልሼ እሠራለሁ’+ እላለሁ፤

27 ጥልቁን ውኃ ‘ደረቅ ሁን፤

ወንዞችህንም ሁሉ አደርቃለሁ’+ እላለሁ፤

28 ስለ ቂሮስ+ ‘እሱ እረኛዬ ነው፤

ፈቃዴንም ሁሉ ሙሉ በሙሉ ይፈጽማል’+ እላለሁ፤

ስለ ኢየሩሳሌም ‘ዳግም ትገነባለች’፤

ስለ ቤተ መቅደሱም ‘መሠረትህ ይጣላል’+ እላለሁ።”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ